SermonsTeachingsUncategorized

Tell Your Story

ሉቃ. 8፡26-39

²⁶፤ በገሊላም አንጻር ወዳለችው ወደ ጌርጌሴኖን አገር በታንኳ ደረሱ።
²⁷፤ ወደ ምድርም በወጣ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፥ ከብዙ ዘመንም ጀምሮ ልብስ ሳይለብስ በመቃብር እንጂ በቤት አይኖርም ነበር።
²⁸፤ ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ በታላቅ ድምፅም፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳትሣቀየኝ እለምንሃለሁ አለ።
²⁹፤ ርኵሱን መንፈስ ከሰውዬው እንዲወጣ ያዘው ነበርና። ብዙ ዘመንም ይዞት ነበርና፥ በሰንሰለትና በእግር ብረትም ታስሮ ይጠበቅ ነበር፤ እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይነዳ ነበር።
³⁰፤ ኢየሱስም፦ ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙዎች አጋንንት ገብተውበት ነበርና፦ ሌጌዎን አለው።
³¹፤ ወደ ጥልቁም ሊሄዱ እንዳያዛቸው ለመኑት።
³²፤ በዚያም በተራራው የብዙ እሪያ መንጋ ይሰማሩ ነበር፤ ወደ እነርሱም ሊገቡ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ ፈቀደላቸውም።
³³፤ አጋንንትም ከሰውዬው ወጥተው ወደ እሪያዎች ገቡ፥ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና ሰጠሙ።
³⁴፤ እረኞችም የሆነውን ባዩ ጊዜ ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩት።
³⁵፤ የሆነውን ነገር ሊያዩ ወጥተውም ወደ ኢየሱስ መጡ፥ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ ልቡም ተመልሶ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።
³⁶፤ ያዩትም ደግሞ አጋንንት ያደሩበት ሰው እንዴት እንደ ዳነ አወሩላቸው።
³⁷፤ በዙሪያውም በጌርጌሴኖን አገር ያሉት ሕዝብ ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ይዞአቸዋልና ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት በታንኳም ገብቶ ተመለሰ።
³⁸፤ አጋንንት የወጡለት ሰውም ከእርሱ ጋር ይኖር ዘንድ ለመነው፤

³⁹፤ ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ ተመለስ፥ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ንገር ብሎ አሰናበተው። ኢየሱስም እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት በከተማው ሁሉ እየሰበከ ሄደ።”


ኢየሱስ ከዴቀ መዛሙርቱ ጋር የገሊላን ባህር ለመሻገር ፈለጌ፡፡ “እንሻገር” ብሎም ጠየቃቸው፡፡ በባህሩ ላይ ግን ክፉ ንፋስና ማዕል ገጠማቸው፡፡ (ቁ 22-15)፡፡ ኢየሱስ ግን ንፋሱንም ባህሩንም ገሥጾ ጸጥ አደረገው፡፡ ከዚያም ወደ ማዶው ተሻገሩ፡፡ ልክ ኢየሱስ ከጀልባው እንደ ወረደ፣ አንድ ሰው ሊገናኘው ወጣ፡፡

ይህ ሰው ለረዥም ግዜ በክፉ መንፈስ ተሠቃዬ፡፡ ለብዙ ዘመን እርቃኑን የኖረ ሰው ነው፡፡ ክፉው መንፈስ ልብስ ለብሶ እንዲሄድ አይፈቅለትም ነበር ማለት ነው፡፡ እንዲህም ሆኖ በቤቱ ሳይሆን በመቃብር ቦታ ይኖር ነበረ፡፡ ከዘመድ፣ ከቤተሰብ፣ ከወዳጅ፣ ተለይቶ በክፉ መንፈስ ተገፍቶ በመቃብር ቦታ ይኖር ነበረ፡፡

በጥንትም ሆነ በአሁን ዘመን እንደምንሰማው የመቃብር ቦታ ብዙ የጥንቆላና የክፉ መናፍስት አሰራር ልምምዶች የሚደረጉበት ቦታ ነው፡፡ ስለዚህ በአይሁድ ዘንድ እንደ እርኩስ ቦታ ይታያል። በጠንቋዮችና እና በመናፍስት ጠሪዎች ዘንድ ደግሞ ጋነኖችን ለክፉ ሥራቸው የሚያድኑበት ቦታ እንደሆነ ይነገራል፡፡
የሀገሩ ሰዎችና ዘመዶቹ፣ ይህንን በርኩስ መንፈስ የሚሰቃየውን ሰው ለመርዳት ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡ በቤት ለማቆየት፣ ርቆ መሄዱንና ጎጂ ተግባሩንም ለመገደብ ስባል በመጠበቅ፣ በሰንሰለትና በእግር ብረት በማሰር ብዙ ጊዜ ሞክረዋል፡፡

ቢሆንም ግን ከመንፈሱ ብርታት የተነሳ፣ ማህበረሰቡ ያንን በክፉ መንፈስ የሚሳቅየውን ሰውዬ ለመቆጣጠር አልቻሉም፡፡ “እስራቱንም ሰብሮ በጋኔኑ ወደ ምድረ በዳ ይነዳ ነበር።” ይላልና፡፡

ኢየሱስ ሲመጣ ግን መንፈሱ ያለበት ሰውዬ “ማንም ሳያዘውና ሳያስገድደው መጥቶ “በኢየሱስ እግር ስር ተደፋ”፡፡ ሰዎችን ማባረር፣ ማዋረድና ማሳፈር እንጂ መደፋት ልማዱ አልነበረም። በኢየሱስ ፊት ግን መደፋት ነበረበት።

ኢየሱስም መንፈሱ ከሰውየው ተለይቶ እንዲወጣ ያዝ ነበርና ታላቅ ድምጽም እየጮሄ ኢየሱስ እንዳሰቅየው እለምን ነበረ፡፡

ዛሬም አልደፈር ያለውን የጠላትን ጉልበት ጌታችን ኢየሱስ በመገኘቱና በቃሉ ሃይል ይሰብረዋል። ለዘመናት ነፍስን ያሰቃዬ፣ እርቃን ያስከደ፣ ያስጨነቀና ከሕያዋን መካከል ለይቶ በሞት ሰፈር ያኖረው ሠይጣን ከኢየሱስ የተነሳ ይደፋል፡፡

ሠይጣን በእግዚአብሄር ልጅ “መጠሊያ” የሌሉትን፣ የብዙዎችን ልብና አእምሮ ተቆጣጥሮ ለዘመናት አሰቃይቶአቸዋል፡፡ ብዙዎች በህይወት እያሉ ከሕያዋን መንደር ተለይቶአል፡፡ ከተያዙበት ክፉ መንፈስ የተነሳ ብዙዎች ከእግዚአብሄር የጸጋ ሽፋን ወጥተው ራሳቸውን በብዙ እየጎዱ ይኖራሉ፡፡
ብዙዎችን የወንድም/የእህት/ የቤተሰብ ወይም የቤተ ክርስቲያን ምክርና እርዳታ በቤታቸው በትዳራቸው ወይም በወገኖች መካከል ሊያቆያቸው አልቻሉም፡፡

አንዳንዶች ብዙ አይነት የቃል ክዳን ማሠሪያዎችንና ጠንካራ የእግር ብረቶችን በክፉው ጉልበት ሰባብረው ከጽድቅ ኑሮ ነጻ ወጥተው አጋንንት በነጻነት ወደሚያሰቃያቸው የሙታን መንደር ተጠልለዋል፡፡
የጠፉትን ፍለጋ የመጣው ኢየሱስ ግን ዛሬም ለብዙዎች ይደርሳል፡፡ እየደረሰም ነው። በተለይ ከእኔ እና ከእናንቴ ጋር ሆኖ ሊደርስላቸው ይፈልጋል። ኑ እርሱን ይዘን እንሻገር። እርሱ ጨርሶ ተስፋ አልቆረጠላቸውምና።

ከቁ30 እንደምናየው የብዙ የክፋት ሰራዊት ማደሪያ ሆኖአል ሰውየው፡፡ ክፉ መንፈስ አንዱ ራሱ ክፉ ነው፡፡ ብዙ ሆኖ በሰው ሲያድር ደግሞ ምንኛ ያሰቃዬው?

የስቃዩ ዘመን ግን አሁን ያበቃል፡፡ ምክንያቱም ብቻውን ሆኖ ሰራዊትን ሁሉ ሊያንበረክክ የሚችል፣ መለኮታዊ ሥልጣን ያለው ኢየሱስ መጥቶአልና፡፡

ወዳጆቼ፣ ሰይጣን በክፋቱና በብዛቱ አስደንግጦአችሁ ይሆን? በዚህ ስትሉ በዚያ ነገሮቻችሁን እያበላሸ፣ አንዱን አሸነፍኩ ስትሉ በሌላ አስፈራርቶአቸሁኋል?
አይዞአችሁ፡፡ ኢየሱስ በሃይሉ በዚህ አለ፡፡ ኢየሱስ ያድናል፡፡

ከቁ31-33 ስናንብ አጋንንት ኢየሱስን ስለምኑት እናያለን፡፡ ይህ ሥልጣኑንና ሓይሉን ያሳያል፡፡ በተጨማሪም፣ ምንም ብርቱና ብዙ ቢሆንም ሀይሉ በኢየሱስ እንደተሸነፈ ያረጋግጥልናል፡፡ ሥልጣን በሰማይና በምድር የኢየሱስ ነው፡፡

በዚያን ዘመን እሪያ ማርባትም መብላትም በአይውዶች ዘንድ የተከለከለ ቢሆንም፣ ይህ ኢየሱስ ሰውዬውን ያገኘበት ሀገር የአሕዛብ አከባቢ እንደ ነበር የተለያዩ ጻሓፊዎች ያስቀምጣሉ፡፡ አይውዳውያንም በብዛት ያሉበት አከባቢ ነው፡፡ እሪያዎቹም የማን እንደሆነ በግልፅ መናገር አንችልም፡፡
ኢየሱስ ግን በድንበር ሳይከለከል የታሰረውን ለመፍታት ተሻግሮ መጥቶ ነበረ፡፡

ለተመልካቾች እየውሆነ ያለውን መንፈሳዊ ጦሪነትና የአጋንንት መሸነፍ በግልፅ ያሳይ ዘንድ ወደ እሪያው እንዲገቡ በለመኑት መሠረት ፈቀደላቸው፡፡ አጋንንቱም እረኞቹ እያዩ መንጋውን ወደ ባህር ጣሉአቸው፡፡

በዚያ የነበሩ ኣሳሞች እስከ 2000 ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገምተዋል፡፡ እነዚህን ሁሉ የሚጠብቁ እረኞች አንድ ወይም ሁሌት ሰው ብቻ እንዳልሆነ መገመት እንችላለን፡፡ ከከተማውም ከገጠሩም እየመጡ ይብቋቸው ነበርና ሁላቸውም በሆነው ነገር ተደናገጡና ወደ ከተማውና ወደየሰፈራቸው ሮጡ፡፡

ቁ 34 “እረኞችም የሆነውን ባዩ ጊዜ ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩት።”
እረኞቹ ሸሽተው ወደ ከተማውና ወደ ገጠሩ ሲሄዱ ያዩትን ሁሉ እንደተናገሩ እናነባለን፡፡ ይንን ሲያድርጉ ግን ባላቸው መረዳት ልክ፣ ኢየሱስ ካዳነው ሰውዬ በበለጠ አደገኛ አድርገው መሳላቸው አልቀረም ብዬ አስባለሁ፡፡ ምናልባት ሰዎቹ ከያሉበት ተሰብስበው የመጡት የሰጠሙትን እርያዎች ለመዳት፣ ወይም ኢየሱስ ከዚህ በበለጠ አልፎ ወደ ከተማቸው እንዳይገባና ብዙ ነገራቸውን እዳያቃውስባቸው ሊሆን ይችላል፤ ፈርተዋልና፡፡

ቁ35-36 “የሆነውን ነገር ሊያዩ ወጥተውም ወደ ኢየሱስ መጡ፥ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ ልቡም ተመልሶ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ። ያዩትም ደግሞ አጋንንት ያደሩበት ሰው እንዴት እንደ ዳነ አወሩላቸው።”

የደረሳቸውን ወሬ ሰምተው እየተንጋጋ የመጣው ሕዝብ የታዘባቸውን ነገሮች ተመልከቱ፡፡

ሀ. አጋንን የወጡለት ሰውም ለብሶ አገኙት፡፡ በዚያ ላሉት ሰዎች ሁሉ፣ ለወንዶችም፣ ለሴቶችም፣ ለልጆችም ለአዋቂም መቀረብ የሚችል አይነት ሁኔታ ላይ ነው ያለው፡፡ ፕረዘንተብል፡፡ ሰውዬው በራቁትነቱ ይታወቅ ነበረ፡፡ ድሮ ሰዎችን ያስፈራራና ያሳፊራቸው ነበረ፡፡ አሁን ግን ልብስ ለብሶ ተገኜ፡፡

ለ. አጋንን የወጡለት ሰው ልቡም ተመልሶ አገኙት፡፡ ያ ማለት አሁን እንደሰው ያስባል፣ አሁን መሆን እንዳለበት ሆኖአል፡፡ ራሱን እየቧጨረ፣ ሌሎችን እየተተናኮለ፣ በጬሄት እየረበሸ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ከኢየሱስ ጋር ሌሎችም ሰዎች ባሉበት በሠላም ተቀምጦአል፡፡ ሊያዩት የመጡት ሕዝብ ይህንንም ታዝበዋል፡፡

ሐ. አጋንን የወጡለት ሰው በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙት፡፡ ይህም ታምር ነው፡፡ በቤት እንዲቀመጥ፣ ከወገኖቹ ጋር እንዲኖር ሰንሰለትና የእግር ብረት ሊይዘው ያልቻለው ሰው በፍቅርና ነጻ በሚያወጣው የኢየሱስ ቃል ተደርሶለት አሁን በራሱ ጊዜ ወደ ኢየሱስ እግር ተጠግቶ ተቀምጦአል፡፡ በዚያ ሰላም አለ፡፡ በዚያ ነጻነት አለ፡፡ በዚያ ክፉ ሊያገነው አይችልም፡፡ ጌታ ይባረክ፡፡

ብዙ ጊዜ በመንፈሳዊው አለም ልምምድ ያላቸው ሰዎች ልዩነቱን ያውቁታል፡፡ ወደ ኢየሱስና ወደ ስሙ ሲጠጉም በዚያ የሚጎዳቸው ነገር እንደሌለ ይመሰክራሉ፡፡

እንግዲህ፣ በመናፍስት ዓለም ልምምዱ ያላቸው ሰዎች የኢየሱስን ክብርና በእግሩ ሲር መሆን ያለውን ልዩነት ያውቁታል፡፡

ሰዎቹ ያዩት ትይንቱን ብቻ ሳይሆን ስለሆነው ነገር በደንብ አድርገው የሚያብራሩ ሰዎችም በአከባቢው ነበሩ፡፡ ብዙ እረኞች ስለነበሩ ያዩትን ነገር ለሕዝቡ አስረዱት፡፡ ሕዝቡም ካዩና ከሰሙ በኋላ የራሳቸውን ምርጫ ማድረግ ይችሉ ነበረ፡፡

ቁ37 “በዙሪያውም በጌርጌሴኖን አገር ያሉት ሕዝብ ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ይዞአቸዋልና ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት በታንኳም ገብቶ ተመለሰ።”
ኢየሱስን ወደ ከተማቸው እንዲገባ መጠየቅ ሳይሆን ፍቀድ ምርጫቸው ኢየሱስን መከልከል ነበረ፡፡ ከከተማቸው አንዲሄድላቸው ለመኑት፡፡

ዛሬም ቢሆን ስለኢየሱስ እና ስለቤተ ክርሰቲያን ሚዘናዊ ያልሆነ ወሬ ስለደረሳቸው፣ ኢየሱስ እያደረገ ያለውን ነገር እያዩና እየሰሙም ቢሆን ልባቸውን አደንድነው ከቤታቸው፣ ከአከባቢያቸው ወይም ከሀገራቸው እንዲወጣላቸው ለማድረግ የሚሩ ሰዎች አሉ፡፡
በድሮው ዘመን፣ አንዳንዶቹ በስድብ፣ ሌሎች ለመውገር ድንጋይ በማንሳት፣ ሌሎችም ደግሞ ከፋፋ ላይ ለመወርወር በመግፋት ሲያሳድዱት አንዳንዶች ደግሞ ትህትና በሚመስል መልኩ ሂድልን ብለው ይለምኑት ነበር፡፡

ኢየሱስ ግን ትሁት ስለሆነ፣ ማንንም ስለማያስገድድ ያለ ክርክርና ያለ ጭቅጭቅ ሄዴላቸው፡፡ ስለእነርሱም ሲያጉረመርም ወይም ሲቆጣ አናየውም፡፡ ሆኖም ግን ምስክር የሚሆን ነገርን በመካከላቸው ተወላቸው፡፡ እስኪገባቸውም ጊዜ ሰጣቸው፡፡ ጌታ የሚያደርገውን ያውቃልና፡፡

ቁ38 -39 “አጋንንት የወጡለት ሰውም ከእርሱ ጋር ይኖር ዘንድ ለመነው። ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ ተመለስ፥ እግዚአብሔር እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረግልህ ንገር ብሎ አሰናበተው። ኢየሱስም እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት በከተማው ሁሉ እየሰበከ ሄደ።”

ከላይ እንዳየነው፣ ኢየሱስ የአጋንትን ጸሎት ሰምቶ ወደ አሳማዎቹ እንዲገቡ ፈቀደላቸው፡፡ የህዝቡን የህድልን ልመናም ተቀበለላቸው። እግር እግሩን ተከትሎ ለመሄድ የለመነውን የሰውዬውን ልመና ግን እምቢ አለ፡፡ ጌታ ፀሎትን እንደፈቃዱ ይመልሳል፡፡

ኢየሱስ ተከታዮቹ እግር እግሩን እየተከተሉ በተዓምር አጀብ እንዲሉ ብቻ ሳይሆን ያገኙትን ሕይወት ለሌሎች እንዲያካፊሉ ይፈልጋል፡፡ የተረገለት ካልመሰከረ፣ ሌሎች ለማመን ይቸገራሉ፡፡ ውሌታው ያለበት ደግሞ ከመመስከር አይቆጠብም፡፡

እውነተኛና ታማኝ ምስክር እንኳን ለቤተ ሰዎቹ ለምድርቱም ይጠቅማል፡፡

ሰውዬው እየዞረ አሥርቱን ከተማ በጌታ ምህረትና ድርግት ሞላው፡፡ እርሱ ስለስነ-መለኮት መናገር አይችልም፡፡ ስለኢየሱስ ማንነትም በዘመኑ ሰዎች ዘንድ ያለውን ኮንትሮቬርሲ መመለስ አይችልም፡፡ ግን ያየውንና የተደረገለትን መሰከረ፡፡ በእግዚአብሄር ጣት የተሠራውም ሥራ ሕያው ስለነበረ፣ ሰዎች ይሰሙት ጀመር፡፡

በሌላ ጊዜ ኢየሱስ ወደ አስርት ከተማ ሲመለስ ብዙ ሰዎች በደስታ ኢየሱስን ተቀበሉት (ማር7:31-32)፡፡

አሁን ባለንበት ዘመን፣ ስለብዙ ነገር ካምፔይን የሚያደርግ አለ፡፡ ስለነፍስ ግን ግድ የሚለው ጥቅት ነው፡፡ በአንዳንድ ቦታ ባክርስቲናችን ለመመስከር ቀርቶ ለመታዬትም አልቻለም፡፡ ሌላው ቀርቶ ሰዎች ክርስቲያኖች መሆናችንን ለማወቅ ይቸገራሉ፡፡

ብዙ ስለሀገሮቻቸን፣ ስለባህሎቻችን፣ ስለአለባበሳችን፣ ስለአመጋገባችን፣ ስለስፖርት፣ ስለፖለትካዎቻችን ለመናገር ይቀለናል፡፡ ስለኢየሱስ እና እርሱን በማመን ስለሚገኘው ሕይወት ግን ለማውራት ብዙዎቻችን አፋችን ተለጉሞአል፡፡ ግን ለምን?

ምናልባት ውለታው ቀልሎብን ይሆን ወይም ትርፋችን/ጥቅማችን/ክብራችን በልጦብን ይሆን ?

ሰውየው ኢየሱስን ወደደው፡፡ ወደ አእምሮው እንዲመለስ ስላደረገው (ከጥላቻ፣ ከመግደል፣ ራስን ከመጉዳት፣ እርቃኑን ሆኖ ከመሯሯጥ፣ ለሊትና ቀን ከመጮህ፣ ያለዘመድ ያለበተሰብ ለሞት ተጋልጦ በነበረበት ቦታ ላይ ኢየሱስ ስለደረሰለት፤ ኢየሱስን መከተል ፈለገ፡፡ ወደደው፡፡

ኢየሱስም ሰውዬው በዚህ የፊቅር ጉልበት ይህችን በአሳማ ሀብት የታወረች ከተማ ማሸፍ እንደሚችል አወቀ፡፡

አስቀድሞ ቤተሰብ መጽናናት ነበረበት፡፡ ቤተሰብ መጽናናቱ ብቻ ሳይሆን ይህ ሰውዬ ለሚሠጠው ምስክርነት ማረጋገጫ ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ከቤተሰዎቹ እንዲጀምር ኢየሱስ ተናገረው፡፡

እኛም በያለንበት ቤት፣ አካባቢና ከተማ የእግዚአብሄር ምህረት መስካሪዎች መሆን ይገባናል፡፡

ጌታ በጸጋው ይርዳን፡፡ አሜን፡፡

በተክሉ

(በወንጌል ሰላም ቤተ ክርስቲያን የቀረበ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *