Sermons

Kalu Yadinal

Posted on

ማሪያም ሊትወልድ ያለውን ልጅ በሌላ ዮሴፍ በፈለገው ስም መጥራት አይችልም ማለት ነው፡፡ ምናልባት እግዚአብሄር ጣልቃ ገብቶ ለዮሴፍ ይህንን ሃላፊነት ባይሰጠው፣ ኢየሱስ ምን ተብሎ ይጠራ ኖሮአል? በሀገራችን በስም አሠጣጥ ባህል ምናልባት “የሴት ልጅ፣ አፍራሽ፣ ድንጋታ፣ አሳምኖት፣ አስጨናቂ፣ ወይም ሌሎችም በዚህ ላይ ከመናገር የተቆጠብኳቸው ሥሞች ሊሰጡት ይችሉ ነበረ፡፡ እነዚህ ስሞች ደግሞ ከዓላማው ጋር የማይሄዱ ናቸው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሄር፣ “ለጻድቁ” ዮሴፍ የራዕይ አግባብነት ያለውን ስም ለልጁ እንዲያወጣለት ተናገረው፡፡ “ኢየሱስ” ወይም “አዳኝ” “ፈይሳ” ተብሎ እንዲጠራ፡፡ በመገለጡ መሠረት፣ ይህ ስም “ሥጋ ለሆነው ቃል” የተሰጠው፣ እርሱ “ሕዝቡን ሁሉ ከኃጢአታቸው ስለሚያድናቸው” ነው፡፡

Sermons

On the Cross

Posted on

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ፣ ስለሰቃዮቹ ይጨነቅ ነበረ፡፡ እግዚአብሄር ይቅር ካላላቸው፣ እያደረጉት ያሉ ነገር ወደ ዘላለም ቅጣት ይወስዳቸዋል፡፡ “ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ ለሚሉ፥ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፥ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!” ይላልና እግዚአብሄር (ኢሳ 5፡20-24)፡፡ ወገኖቼ፣ በበሽታ፣ በችግር፣ በረሃብ፣ በጦሪነት፣ በእርጅና፣ በተለያዩ አደጋዎች ይህችን ዓለም ከመልቀቃችን በፊት ምን ያክል ጊዜ እንደቀረን አናውቅም፡፡ ግን ይህችን የቀረችንን እድሜ እንዴት እናሳልፍ? እግዚአብሄርን በመሳደብ ወይስ ለምህረት ወደ ተዘረጋችው የእግዚአብሄር እጅ በመሸሽ?

Uncategorized

መልካም ግንኙነት

Posted on
መልካም ግንኙነት ,wilesofthedevil, Mekane Yesus in Scotland, salvation, prayer, resist,

“እግዚአብሄር አምላኬ ሆይ፣ ስለምትወደኝ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ፡፡ ክቡር በሆነውን መልከህና ምሳሌህ ስለፈጠርከኝ ተመስገን፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተመላልሰህ በጠበቅህኝ ቦታ ስላላገኘህኝ ዕቅርታ እጠይቅሃለሁ፡፡ ከውድቀተ አንስቶኝ፣ ከጥፋቴም መልሶኝ ሕይወትን ይሰጠኝ ዘንድ ስለእኔ ስለሞቴውና ከሞትም ስለተነሳው ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ አከብርሃለሁ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከወደደኝና ስለእኔ ነፍሱን ከሰጠው ከልጅህ ከኢየሱስ ጋር መኖርን እፈልጋለሁ፡፡ በምህረትህ ተቀበለኝ፡፡ ያወቅሁ እየመሰለኝ ተታልዬ ከገባሁበት ማንኛውም ሁኔታ አንቴ አውጣኝ፡፡ ስሜን በሕይወት መዝገብ ጻፍልኝ፡፡ አንቴ የምትወደው ዓይነት ሰውም ሆኜ ከአንቴ ጋር በመልካም ግንኙነት መኖር እንዲችል በጸጋህ እርዳኝ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፡፡ አሜን፡፡”

Sermons

እግዚአብሄርን ማስገረም

Posted on
እግዚአብሄርን ማስገረም አይቻልም፡፡ መካነ ኢየሱስ, መካነ የሱስ በስኮትላንድ, እጅህ ንጹህ አይደለም, No surprise!, ስብከት በተክሉ , የግላስጎ አመኞች, የእግዚአብሄርን ጸጋ አልጥልም, እሬ እኔ ማን ነኝ, ያንስብሃል ምስጋናዬ ያንስብሃል ጌታ, ምህረት የበዛለት , Amazing grace, saved by grace, Mekane Yesus, ECMYIS, Mekana Yasus in Scotland, Glasgow christians, Evangelical chuch in glasgow, wash your hand, hand washing

ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት (በመገኘቱ ውስጥ) ተቀመጠ። በዚያም ሆኖ ትክክለኛ ማንነቱን እና የእግዚአብሔርን ቸርነት ማሰብ ጀመሬ። እግዚአብሔር ልብን እንደሚያውቅም ተረዳ።

ሞት ተፈርዶበት እያሌ ከዚያ አስመልጦት በህይወት ያኖረውን ጌታ ንጉሥ ሆኖ ማገልገል ላይ የሚገኘው ዳዊት እግዚአብሄርን ባለእዳ ማድረግ ይችላል ወይ? እኛስ ብንሆን፣ እግዚአብሄር ሳያደርግልን፣ ለእግዚአብሄር የምናቀርበው ነገር ምን ይኖረናል?

Sermons

ኢየሱስ ሥራውን ቀጠለ

Posted on
I must work the works of him that sent me, while it is day: the night cometh, when no man can work. “ ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች ”Evangelical Church Mekane Yesus in Scotland, ECMYIS, Glasgow, Uk. Amharic service

ጌታ እየሱስ ብዙ የሚሠራቸው ሥራዎች ነበሩት፡፡ በተለይ ደግሞ አጋንንትን ማውጣት እና በሽተኞችን መፈወስ (ቁ.32)፡፡ ይህ ማለት የታሰሩንና ጤናቸውን ያጡትን የሰዎችን ልጆች ነጻ ማውጣት በቀረችው ጊዜ መፈጸም የሚፈልጋቸው ሥራዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህንን ዓላማውን ትቶ እንዲሄድና ከሄሮድስ የመግደል ዕቅድ እንዲያመልጥ ስመክሩት እንመለከታለን፡፡“ከፈሪሳውያን አንዳንዱ ቀርበው፦ ሄሮድስ ሊገድልህ ይወዳልና ከዚህ ውጣና ሂድ አሉት።” (ቁ 31)
ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ የነበረውን ተልዕኮ (ሚሽን) ጨርሶ ከመሄዱ በፊት የተወሰነ ወይም ጥቂት ጊዜ እንደነበረው ያውቅ ነበረ፣ ይናገርም ነበረ፡፡ “ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች” (ዮሓ 9፡4) ብሎአልና። ኢየሱስ ሰው ሊሠራበት የማይችልበት “ሌሊት” ይመጣል ሲል ሰው ሌሊቱ ሳይመጣ የተሠጠውን የቤት ሥራ በርትቶ መጨረስ እንዳለበት ለማሳሰብም ነው፡፡ …..

Sermons

ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው

Posted on
ecmyis sunday service, Mekane Yesus in Scotland, Christianity, Glasgow church,

ዓለማዊ ዜጎችን በወንጌሉ ቃል የሰማያዊ ዜጎች የማድረግ ሥራ ውስጥ የመንፈሳዊው ድንበር ጥሰት መዘዞች አሉበት፡፡ ይህ ደግሞ መገለጫው በቤተሰዎች መካከል፣ በዘመዶች መካከል፣ በወዳጆች መካከል፣ በህብረተሰብ መካከል የሚመጡ አለመግባባቶች፣ አለመስማማቶችና በተለይም ስለቃሉ በሚነሱት ስዴቶች ናቸው፡፡ ክርስቲና ለሕወትና ለጥሪ የሚንኖርበት ሕይወት እንጂ የምቾት ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡ ያ ማለት ደግሞ ክርስቲያኖች ፈጽሞ የምቾት ሕይወት አያስፈልጋቸውም፣ ወይም በምቾት መኖር አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ደስታ፣ ሠላም፣ በረከት፣ አብሮነትና መንፈስ የደስታቸውና የምቾታቸው መሠረት ነውና፡፡… የሚላኩ ሰዎች ወይም ደቀ መዛሙርት በተለያዬ መንገድ የሚደግፉአቸውን ከእነርሱ በታች አድርገው መቁጠር አይገባቸውም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ሁለቱም እኩል ዋጋ አላቸውና፡፡