Sermons

Go home justified

Posted on

እግዚአብሄር ያልሰጠንን ጽድቅ ለራሳችን ብንቆጥር ራስን መሸንገል እንጂ ድነት አናገኝበትም፡፡ በሕይወት የሚያኖረው እግዚአብሄር ራሱ በዕቅር ባይነቱ የሚሠጠው ጽድቅ ነው፡፡
ይህንን ምሳሌ ኢየሱስ ሲናገር አድማጮች ሰምተው የእግዚአብሄርን ጽድቅ እንዲቀበሉ ነው፡፡ ሰሚዎቹ ኢየሱስ ከጎናቸው ሆኖ እየለመናቸው ያለጽድቅና ምህረት እንዳይመለሱ ነው፡፡ ሰሚዎቹ የራሳቸውን ጽድቅ ትተው የእግዚአብሄርን ጽድቅ እንዲቀበሉ ነው፡፡ የምህረትንና የጉብኝታቸውንም ጊዜ እንዳይንቁ ነው፡፡ ኢየሱስን ለማየትና ለመስማት መምጣታቸው ካልቀረ፣ ለምንድር ነው ከነ ኃጢአት መኖር? ኢየሱስ በእግዚአብሄር ፊት ራሱን ስላዋረደው ሰውዬ ሲናገር “ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ” አለ፡፡

Sermons

Tell Your Story

Posted on

ሰውዬው እየዞረ አሥርቱን ከተማ በጌታ ምህረትና ድርግት ሞላው፡፡ እርሱ ስለስነ-መለኮት መናገር አይችልም፡፡ ስለኢየሱስ ማንነትም በዘመኑ ሰዎች ዘንድ ያለውን ኮንትሮቬርሲ መመለስ አይችልም፡፡ ግን ያየውንና የተደረገለትን መሰከረ፡፡ በእግዚአብሄር ጣት የተሠራውም ሥራ ሕያው ስለነበረ፣ ሰዎች ይሰሙት ጀመር፡፡

Sermons

ሊያከብሩ የተመለሱ

Posted on

ለተደረገልን ማንኛውም ነገር እግዚአብሄርን ማመስገን ስንለማመድ፣ ብዙ ተጨማሪ በረከቶችን ከእግዚአብሄር እንቀበላለን፡፡ ስለመቀበሉ ብቻም አይደለም፡፡ እስቲ አስቡ፣ ሕዶ በጌታ ፊት ተገኝቶ ከእርሱ ጋር መነጋገርስ ምነኛ ትልቅ በረከት ነው፡፡ ወደ እርሱ ቀርቦ ከሥጋ ፈውሱ የሚበልጠው ምህረቱና ደንነቱ በሕይወታችን መኖሩን ከአፉ ስንሰማ አያስደስትምን?