Sermons

ጋሻህ ነኝ

ጦሪነትና ተያይዞ ያለው ፍለጻ ወይም ጦር ባይኖር ጋሻ ባላስፈለገ ነበር፡፡ ጋሻ የሚጠቅመው የሚወረወርብን ነገር ሲኖር ከእርሱ እንዲሸፍነንና እንዲያድነን ነው፡፡ እግዚአብሄርም ለአብርሃም “እኔ ጋሻህ ነኝ” ሲለው፣ በአብርሃም ቀሪው ዘመን የሚቀጥል ጦሪነትና ሰልፍ ሊኖር እንደሚችል አመልካች ነው፡፡

“አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ” (ዘፍ 15፡1)

ከእለታት አንድ ቀን ሎጥ በሰዶም እያለ፣ ሲዲም በሚትባል ሸለቆ ውስጥ ዘጠኝ ነገስታትን ያሳተፈ ጦሪነት ተደረገ፡፡ በዚህ ጦሪነት ውስጥ የሰዶምና የጎሞራ ነገስታትም ነበሩበት ግን ደግሞ ድል ተነስተው ሸሹ፡፡ ነገስታቱ በጦርነቱ በመሸነፋቸው፣ ያሸነፉአቸው ነገስታት “የሰዶምንና የገሞራን ከብት ሁሉ መብላቸውንም ሁሉ ወስደው ሄዱ። በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ። ”(ዘፍ 14፡11-12)

አብርሃም ይህንን በሰማ ጊዜ 318 “ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።” አብርሃምም በሌሊት ወረደባቸው፣ መታቸውም ከዚያም አሳደዳቸው፡፡ በጦርነቱ ተማርከው የነበሩትንም ከብቶችና ሰዎች ሁሉ አስመለሰ፡፡ እግዚብሄር ድልን ስለሠጠው በድል ተመለሰ፡፡

ሆኖም ግን በአብርሀም ልብ ውስጥ ያልተለመደ ፍርሃት መታየት የጀመረ ይመስላል፡፡ ምናልባት የፍርሃቱ ምንጭ እነዚያ የተሸነፉት ነገስታት ሃይላቸውን አድሰው ቢመጡብኝስ የሚል ሃሳብ ይሆን ወይም በዙሪያው ያሉ ሌሎች ነገስታት በፍርሃት ቢነሱብኝስ የሚል ይሆን?

አብሪሃም ዛሬ በጦሪነቱ ቢያሸንፍም ነገ የራሱ ልጅ ስለሌለው እርሱ ሲደክም ሲያረጅ፣ ማን ይዋጋልኛል፣ ማን ጋሻ ይሆንልኛል፣ ማለቱ አልቀረም፡፡ በተጨማሪም ደግሞ አብርሃም፡- በጦሪነቱ ውስጥ ሞቼ ቢሆን ወይም ደግሞ ሊገጥሙኝ በሚችሉ ጦርነቶች ውስጥ ብሞት የእኔ ወራሽ የቤቴ መጋቢ የሆነው ኤልዔዘር ነው፤ ብሎ ማሰብ እጅግ ያስፈራው ይመስላል፡፡

እግዚአብሄር ይህንን የአብርሃምን ልብ የወረረውን ፍርሃትና ጭንቀት ተመለከተ፡፡ እንዲህም አለው “አብራም ሆይ፥ አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።” (ዘፍ 15፡1) ደግሞም እግዚአብሄር እንዲህ ብሎ ለአብርሃም ተናገረው “ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።” እግዚአብሄር ይመስገን፡፡

“አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ” ብሎአል እግዚአብሄር፡፡

ጦሪነትና ተያይዞ ያለው ፍለጻ ወይም ጦር ባይኖር ጋሻ ባላስፈለገ ነበር፡፡ ጋሻ የሚጠቅመው የሚወረወርብን ነገር ሲኖር ከእርሱ እንዲሸፍነንና እንዲያድነን ነው፡፡

እግዚአብሄርም ለአብርሃም “እኔ ጋሻህ ነኝ” ሲለው፣ በአብርሃም ቀሪው ዘመን የሚቀጥል ጦሪነትና ሰልፍ ሊኖር እንደሚችል አመልካች ነው፡፡

እግዚአብሄር ለአብርሃምም ሆነ ከእርሱ በሃላ ለነበሩት የእምነት አባቶች፣ በአንድም ቦታ ተግዳሮቶች እንደማይገጥሙአቸው ለማድረግ ቃል አልገባላቸውም፡፡ ነገር ግን እንደሚጠብቃቸው፣ ድልን እንደሚሰጣቸው፣ እንደሚያድናቸው፣ እንደሚከልላቸው፣ የሚነሳባቸው እሳት እንደማያቃጥላቸው፣ ውሃም ይዞአቸው እንደማይሄድ፣ ወዘተ. ነው፡፡ “አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ” ብሎአል እግዚአብሄር፡፡

እኛ በሕይወታችን ለሚያጋጥሙን አብዛኞች ነገሮች መፍራት፣ ማጨነቅ፣ አንዳንድ ግዜ ደግሞ በእግዚአብሄር ላይ ማጉረምረም የተለመደ ነው፡፡ በብዛት ከእኛም ሆነ ከሌሎች የሚነሱ ጥያቄዎች “እግዚአብሄርን እያመለክሁ ለምን ይህ ይደርስብኛል?” የሚል ነው፡፡ ሌሎቹም “ታዲያ የት አለ እርሱ የሚያመልከው አምላክ/እርሷ የሚታመልከው አምላክ?” ይላሉ፡፡

እግዚአብሄር ግን አልተወንም፡፡ በመከራም ውስጥ ቢሆን፣ ብቸኝነት በሚመስለው፣ ግራ መጋባት በሚመስለው፣ ስደት በሚመስለውና አንዳንደም ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሄር ከእኛ አልራቀም፡፡ “አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ” ብሎአል እግዚአብሄር፡፡

ገድኦን ፈርቶ ተደብቆ ስንዴ በሚወቃበት ጊዜ እግዚአብሄር ያየው ነበረ፡፡ ዳቂት በምድረ በዳ በሚንከራተትበት ጊዜ እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ነበረ፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እግዚብሄር ያይ ነበረ፣ ከእነርሱም ጋር ነበረ፡፡ ዮሓንስ በፍጥሞ ደሴት ላይ ታስሮ በሚጠበቅበት ጊዜ እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ነበረ፣ እንዲያም ለብዙ ትውልድ የሚሆን መልእክት እየሰጠው ነበረ፡፡ “አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ” ብሎአል እግዚአብሄር፡፡

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሄርን እያመለክንና እያገለገልን ስለምናልፍባቸው ማናቸውም ሁኔታዎች ቀጥለን በእግዚአብሄር ከመታመን ውጪ ወደ ማጉረምረም መግባት የለብንም፡፡ “አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ” ብሎአል እግዚአብሄር፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *