Sermons

የእግዚአብሔር ታማኝነት

በብሉህ ኪዳንም ሆነ በአድስ ክዳን ዛሬንም ጨምሮ፣ እግዚአብሄር ሰዎችን የሚጠራውና የሚያናግረው ስለሰውየው /ስለሴትዮዋ ብቻ ሳይሆን ለሚወዳቸውና ስለሚራራላቸው ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ጭምር ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ሲሆን፣ ሲሠራ በኮምንከሽኖቻችን መካከል የሚያነሳቸው ሰዎች የሉምን? ለኢያሱ ሲናገር “ለአባቶቻቸወን የማልኩላቸውን ታወርሳቸው ዘንድ….” ለደቄ መዘሙርቱ ሲናገር “ሁልጊዜ እስከ አለም ፍጻም ድረስ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ…” ምን እንድሆን? ወንጌልን ላልደረሳቸው እንድያደርሱ…

የዕለቱ የመልእክት ክፍል
ትንቢተ ኢሳይያስ 45 1- 7
1 እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል።
2 በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ
3 በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
4 ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም።
5-6 እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም ከእኔም በቀር አምላክ የለም በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።
7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።

የዕለቱ የወንጌል ክፍል

ማቴ 22፡ 15-22
22 ስለዚህ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በነገር እንዲያጠምዱት ተማከሩ።
16 ደቀ መዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን  ጋር ላኩበት፥ እርሱም፦ መምህር ሆይ፥ እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፥ ለማንምም አታደላም፥ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤
17 እንግዲህ ምን ይመስልሃል? ንገረን ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? አሉት።
18 ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ። እናንተ ግብዞች፥ ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ?
19 የግብሩን ብር አሳዩኝ አለ። እነርሱም ዲናር አመጡለት።
20 እርሱም፦ ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው።
21 የቄሣር ነው አሉት። በዚያን ጊዜ። እንኪያስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው።
22 ይህንም ሰምተው ተደነቁ፥ ትተውትም ሄዱ።

ለምን እግዚአብሄር በቃል ክዳንም ከእኛ ጋር ራሱን አሰረ?

ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሄር ከግለሰቦች ጋር ይነጋገር፣ ቃል ክዳን ይገባ፣ ያፅናናቸው፣ ይቅር ይላቸው፣ ይጠነቀቅላቸውም ነበር፡፡ ዛሬም እኔንና እናንቴን ጨምሮ ማለት ነው፣ እግዚአብሄር በብዙ ረድቶናል፣ መርቶናል፣ ይቅር ብሎናል፣ በቃል ክዳንም ከእኛ ጋር ራሱን አስሮአል፡፡ ግን ለምን ብላችሁ ታውቃላችሁ?
ለሁላችንም ቶሎ ሊመጣልን የሚችለው እውነት “እግዚአብሄር ይወደኛል” የሚል ይመስለኛል፡፡ በእርግጥም እግዚአብሄር እያንዳንዳችንን ይወደናል፡፡ ዛሬ የምናነበው የእግዚአብሄር ቃል ክፍል ይህንን አስገራሚ ፍቅር እንድንጠራጠር የሚያደርገን ሳይሆን በፍቅሩ ጥልቀትና ከፍታ ላይ ደርዝን የሚጨምር ይሆናል፡፡ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ስለእኛ መልካም የሚያደርገው በታማኝነቱ የጸና፣ ቃሉን የሚያከብር፣ መልካምና መሃሪም በመሆኑ ነው፡፡

እግዚአብሄር በማንነቱ፣ በክብሩ፣ በእውቀቱ በእይታውም ከፍ ያለ ስለሆነ፣ እኛንና ነገሮቻችንን እኛ እንደምንመለከተው ብቻ አይመለከተውም፡፡ አስፍቶና አቅርቦ (ከእነ ድተይልስ) ይመለከተዋል፡፡
ኢሳ 45፡ 1 ላይ ስለ ቂሮስ ሲናገር፡-
– እንደቀባው
– ቀኝ እጁንም እንደያዘው ይናገራል፡፡ ለምን?
-አሕዛብ እንድገዙለት
-ነገስታት እንድፈሩት
– በሮች እንዳይዘጉበት
– ተዘግተው ያሉትም ደጆች እንድከፈቱለት (ምንም ከልካይ በፊቱ እንዳይኖር ማለት ነው)
ቁ.3 ‹‹በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።››
ቁ.4 ‹‹ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም።››
5-6 ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም ሌላ ማንም የለም ከእኔም በቀር አምላክ የለም በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።››
7 ‹‹ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።››

– በፊቱ እንደሚሄድ፣ ለምን?
– ተራሮችን ለማስተካከል
– በጥንካሬ የሚታወቁ የተዘጉ በሮችን ለመስበር
– ሁሉም በርቀት አይቶ የሚፈራውን የብረት መወርወሪያዎች ለመቁረጥ በፊቱ እንደሚሄድ ይናገራል፡፡
– በተጫማሪም ‹‹በጨለማ የነበረችውን መዝገብ፣ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት›› እንደሚሠጠው ይናገራል፡፡ ለምን እግዚአብሄር ይህንን ማድረግ ፈለገ ብለን ብንጠይቅ?
– ታውቀኝ ዘንድ (የእግዚአብሄር አቅርቦት እርሱን እንዲናውቀውና እንዲንታመነው እንጂ እንዲንኩራራበት ወይም ራሳችንን እንድንጎዳበት አይደለም)
– አንተን እንደማውቅህም (ነገሮችህ ስምህ ሳይቀር) በእኔ ዘንድ የታወቁ እንደሆነም ታውቅ ዘንድ
– በእኔ ዘንድ ተወደድደሀል (በቁልምጫ ስም ጠርቸሃለሁ)፡፡ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ስለተለመደ ብቻ፣ ወይም ሌሎች የቁልምጫ ስማችንን ስጠቀሙ ስለሚሰሙ ወይም ደግሞ አፍቃሪ መስለውም ለመቅረብ በቁልምጫ ስም ልጠሩን ይችላሉ፡፡ በእግዘብሄር ዘንድ ግን ማስመሰልም ሆነ ማጭበርበር የሚበል ነገር ፈጽሞ የለም፡፡ እርሱ ማንንም አይፈራም፡፡ የማንንም ስድብ ወይም ጫና ፈርቶ የማይፈልገውን አይናገርም፣ አያደርግምም፡፡ ስለዚህ በቁልምጫ ስምህ ጠራሁህ ካለ ወደድሁህ ማለቱ ነው፡፡

– ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ እግዘብሄር ቂሮስን ‹‹አስታጠቅሁህ›› ሲለው እናነባለን፡፡

ግን ቀሮስ ምን ስለሆነ ይህንን ሁሉ ክብር (ፕሪቪለጅ) አገኜ?
– ቁ 4. ስለሌሎች ነው
– “ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ”
-“ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ”
-ቁ. 4 ስለራሱ ነው፡፡ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” እንተዋወቅ፡፡
– ከእኔም ሌላ ማንም የለም
– ከእኔም በቀር አምላክ የለም
– ሁሉ በእኔ ሆነ (“ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ”) ቁ 7

እንግድህ ቂሮስ ማወቅ ያለበት

1. እግዚአብሄር ራሱን ሊያስተዋውቀው እንደሚፈልግ
2.እግዚአብሄር እንደሚወደውና ምህረት እንዳደረገለት
3. እግዚአብሄር የሚራራላቸውና ሊረዳቸው የሚፈልግ ሕዝብም እንዳለሁ

በብሉህም ሆነ በአድስ (ክዳን ዛሬንም ጨምሮ) እግዚአብሄር ሰዎችን የሚጠራውና የሚያናግረው ስለሰውየው /ስለሴትዮዋ ብቻ ሳይሆን ለሚወዳቸውና ስለሚራራላቸው ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ጭምር ነው፡፡
ለኢያሱ ሲናገር “ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ታወርሳቸው ዘንድ….”
ጌታ ኢየሱስ ለደቄ መዛሙርቱ ሲናገር “ሁልጊዜ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ…” ብሎ ቃል ሲገባላቸው ወንጌልን ላልደረሳቸው እንድያደርሱ ነው፡፡
ዛሬ እግዚአብሄር ከእኛም ጋር ሲሆን፣ ሲሠራ በግንኙነቶቻችን (በኮምንከሽኖቻችን) መካከል የሚያነሳቸው ሰዎች የሉምን?

ጌታ ይርዳን

(By Teklu,  22 Oct 2017)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *