Sermons

የእግዚአብሄርን ክብር ማየት

Mekane Yesus in Scotland,evangelical church Mekane Yesus in Scotland,evangelical church Scotland,evangelical churches glasgow scotland, evangelical lutheran church in scotland,baptist church glasgow scotland,evangelical union church scotland, evangelical church scotland,evangelical church glasgow,evangelical churches glasgow scotland,evangelical lutheran church in scotland, mekane Yesus

ማር8፡38- 9፡1 (የእግዚአብሄርን ክብር ማየት መታደል ነው፡፡)

በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።

እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ አላቸው።”

በቁጥር 38 ላይ ኢየሱስ

– ሰዎችን ከሞት ሊያድን የሚችለው ቃሉ እንዲነገር እንደሚፈልግ ተናግሮአል፡፡

– ትውልዱ ከጽድቅ የወደቀ ወይም ሓጢአተኛ መሆኑን አሳይቶአል፡፡

– ዛሬ ሰዎች በዚህ ዓለምና በዚህ ሕይወት የሚመርጡት ምርጫ በኋላ ኢየሱስ ለመውሰድ የሚመርጠውንም እርምጃ ያሳያል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን

– ኢየሱስ በእግዚአብሄር አብ ዘንድ ክብር እንዳለሁና በዚያ ክብርም ሊገለጥ እንዳለ ተናሮአል፡፡ ይህ ማለትም

–አባቱ በሠጠው/በሚሠጠው ክብር

–በዓይነቱ የአባቱ ብቻ /የእግዚአብሄር ብቻ በሆነው መለኮታዊ ክብር

–በማንነቱ/መለኮታዊ በሆነው ክብር ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ ክብር ሲገለጥ መላእክት ያጅቡታል፣ ይሰግዱለታል፣ ይገልጡታል፣ ይመሰክሩለታል፡፡

ይህ ክብር መኖሩ መታወቁ ብቻ ሳይሆን፣ ኢየሱስ በዚያ ክብር ሆኖ/ ተገልጦ የሚያከብራቸው፣ የሚባርካቸው፣ የሚያመሰግናቸው ሰዎች እንዳሉም ጭምር ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል ይናገራል፡፡

እነዚያ ሰዎች ያንን ክብር ሊያዩ የሚችሉት በዚህ ክፍል መሠረት፣ ራስን ዝቅ በማድግ መንገድ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት መታደል ነው፡፡

ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትም ደግሞ ኢየሱስን በመመስከር፣ እርሱ ለሓጢአተኞች እንዲታወቅ በማድግ፣ ያም ሊያመጣባቸው የሚችለውን መከራ በመቀበልም ጭምር ነው፡፡

እነርሱ ኢየሱስ ሓጢአተኞች ናቸው ባላቸው ፊት ከመመስከራቸው የተነሳ ሓጢአተኞቹ በንስሓ ወደ እግዚአብሄር ይመለሳሉ፡፡ የኢየሱስንም ጌትነት ያውቃሉ፡፡ ጌታን ለመታዘዝም/ለመቀበልም ሆነ ላለመታዘዝ/ላለመቀበል ውሳኔ ያደርጋሉ፡፡

 

ኢየሱስም በክብሩ ሲገለጥ እነዚያን መስካሪ የሆኑ ሰዎች በአባቱ ፊት ማመስገን፣ ማክበር፣ ለእነርሱም ለመመስከር እንደሚፈልግ ይናገራል፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት መታደል ነው፡፡

በሌላ አንጻር ደግሞ በዚያኑ ጊዜ በሌሎች ሰዎች ደግሞ እንደሚታፈርባቸው፣ እንደሚኮነኑ፣ እንደሚካዱም ኢየሱስ ጨምሮ ተናግሮአል፡፡

 

እንግዲህ በዛሬው ክፍል የምናየው የእግዚአብሄርን ክብር ማየት ለኋለኛው ቀን ብቻ የቀረ ሳይሆን በዚህች ዓለምም፣ ያውም በዚህች ትውልድ መካከል ራሱ የሚገለጥበት ሁኔታ እንዳለም ነው፡፡

 

ማር 9፡1 “እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ አላቸው።

ይህ ቃል እግዚአብሄር የነገ አምላክ ብቻ ሳይሆን የዛሬም አምላክ፣ የሰማያዊ ብቻ ሳይሆን የምድርም እንደሆነ፣ የማይታየው አለም ብቻ ሳይሆን የሚታየው ዓለምም አምላክ እንደሆነ ይናገራል፡፡

 

ኢየሱስ የእግዚአብሄርን መንግስትና ሥልጣን ሲያስተምር፣ ከመጨረሻው ቀን ቀጥሎ ስለሚቀጥለው ሕይወት ብቻ አላስተማረም፡፡ ነገር ግን

– ዛሬም የእግዚአብሄር ክንድ እንደሚሠራ፣ በሥራ ላይም እንዳለ

– በዚህ በምንኖርበት ዓለምና በትውልዳችንም የእግዚአብሄር ክብር መገለጥ እንደሚችል ጭምር አሳየ ማለት ነው፡፡

 

ይህ ማለት ደግሞ ዛሬ በግላችም፣ በሕብረትም የእግዚአብሄርን ክብር የማየት ዕድል አለልን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር የሁልጊዜ አምላክ ነው፡፡

 

መጽሓፍ ቅዱሳች

– እግዚአብሄር ፍጥረታትን ሁሉ በመፍጠር ክብሩን የገለጠ እንደሆነ ይናገራል፡፡

– ደግሞም ቃሉ ሲጻፍ ተአምራት አድራጊ አምላክ መሆኑን ይናገራል– ሕዝቡን ከግብጽ ነጻ ሲወጣ፣ ባህር ሲከፈል፣ ከሰማይ መና ሲያወርድ፣ በሽተኛ ሲያድን፣ አልአዛርን ከሞት ሲያስነሳ፣ ኢየሱስ በትንሳኤው ጉልበት ሲገለጥና ሲያርግ…ወዘተ

– ከዘመናት በኃላ ስለሚመጣውም ታላላቅና አስገራሚ ነገሮች ይናገራል፡፡

– ዛሬም ቃሉን በሚያነቡትና በሚያምኑት ሰዎች ሕይወት የእግዚአብሄር ክብር እና ክንድ ይገለጣል፡፡

ኢየሱስ እርሱን በመከተል ውስጥ መከራ እንዳለ፣ ከመከራው ቀጥሎ ደግሞ ዘላለማዊ ክብር እንዳለ አስተማረ፡፡ ትክክለኛ ክብር የሚመው ከመከራ በኃላ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እውነት እንደሆነና የሚመጣው ክብር ምን ሊሆን እንደሚችል ትንሽ ጨረፍታም ቢሆን ኢየሱስ ክብሩን ከ6 ቀን በሃላ ለደቀ መዛሙርቱ አሳየ፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት መታደል ነው፡፡

ታዲያ ኢየሱስ “…በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ” ሲል ምን ማለቱ ነበር?

– የመግደል ሙከራዎች አይደረጉባችሁም ማለቱ አልነበረም፡፡ ወይም ደግሞ ዓለም አጨብጭባ ትቀባላቸዋለች ማለቱም አይደለም፡፡

– በሌላ ጎኑ ደግሞ ሁሉም ሰው የእግዚአብሄርን ክብር ያያል ብሎም አልተናገረም፡፡ “አንዳንዶች አሉ” ብሎ ነው የተናገረው፡፡

– ወንጌል ከመሰበኩና ከተሰበከም በኋላ የሚገለጥ የእግዚአብሄር ክብር አለ፡፡

 

እግዚአብሄር ተስፋ ሰጭ ብቻ ሳይሆን የተስፋ ቃሉን አሳቢ አምላክም ነው፡፡ መጽሓፍ ቅዱስ ይህንን ግልጽ አድርጎ ይገልጣል፡፡

– እናንተ ከጌታ ምንን ሰምታችሃል? እርሱን ጠብቁት እርሱ ያደርገዋልና፡፡

— ስምዖን በእምነት ይጠባበቅ ነበረ–“ልጁንም አይቶ ሳመው”

–ሃና በእምነት ጥጠብቅ ነበር– ልጁን አይታ ተደሰተች

–ጳውሎስ “ያመንኩትን አውቃለሁ” አለ፡፡ በመርከቡ ላይ የደረሰውም አደጋ በሮማ መንግስት ፊት ከመቆም አላገደውም፡፡

— “የእግዘአብሄርን ክብር ታያላችሁ” እግዚአብሄር ብሎአችሁ ከሆነ፣ እናንተም አምናችሁ ተቀብላችሁ ከሆነ፣ በእርግጥ ይሆናል፡፡

— ከ6ቀን በሃላ ኢየሱስ ክብሩን ገለጠላቸው (ማር 9፡2)፡፡ 6 ቀን፡፡ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነው፡፡ ሰው የራሱን ሲጨርስ የእግዚአብሄር ክብር ይገለጣል፡፡ በሰው አስተሳሰብ፣ በሰው አገማመት፣ በሰው ስለት፣ በሰው ጊዜ ሳይሆን ጌታ በራሱ ጊዜና መንገድ ይመጣላችሁአል፡፡

—ሰው የእግዚአብሄርን ክብር ማየቱ ብቻ ደግሞ በቂ አይደለም፣ መጠንቀቅ መቻል አለበት፡፡ ካልሆነ መሳሳት፣ መጎዳት፣ መውደቅም ይችላል፡፡ ምሳሌ፡- ሙሴ፣ ጴጥሮስ፣…፡፡ ነገር ግን በጸጋው ከታመንን ጌታ አይጥልም፡፡

-ኢየሱስ ያለው ክብር የተለጠው በተራራ ላይ በሆነው ነገር ብቻ አላቆመም ነገር ግን ትልቁ በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ሲር ሆነው መንቀሳቀስ የሚጀምርበትን ሕይወትም አመጣላቸው እንጂ፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት መታደል ነው፡፡

 

እኛስ ዛሬ የእግዚአብሄርን ክብር እንፈልጋለን ወይ?

  • ጌታንና አደራረጉን እንደቃሉ ወስዶ በእምነት መጠበቅ
  • የጌታ ጊዜን በመጠበቅ

የጌታን ፈቃድ በማድረግ (ለሌሎች መመስከርም ጨምሮ) የእግዚአብሄርን ክብር በራሳችንም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ እንዲናይ ያደርገናል፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት መታደል ነው፡፡

 

እግዚአብሄር በጸጋው ይርዳን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *