Sermons

ኢየሱስ ማን ነው?

Jesus the son of the Living God

የዕለቱ ክፍል

ማቴ 16፡13-20

“ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።

እርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።

እርሱም ፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።

የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።”

የኢየሱስ ጥያቄና ዓላማው

ኢየሱስ ከደቄ መዛሙርቱ ጋር ወደ ፍልጶስ ቂሣሪያ ሀገር ሄዴ፡፡ በዚያ ብዙ የጣዖታትና የቄሳር አምልኮ በስቶበት አለ፡፡

ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።” ለምን? በዚህ ቦታ ኢየሱስ የመረጃ ጥማት አልነበረውም (የማያውቀው ነገር ስላልነበረ ማለት ነው)፡፡ ግን ደግሞ በየሄዱበት ቦታ ሰዎች ከእርሱ የበለጠ ደቀመዛሙርቱን እንደሚያናግሯቸው ያውቃል፡፡ እነርሱ ብዙ ስለነበሩም፣ በቀላሉ ለሰዎች ስለሚገኙም ማለት ነው፡፡ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ ኢየሱስ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ስጠይቅ ነበረ፡፡ “ምን ትፈልጋላችሁ?”፣ “የሚበላ አላችሁ ወይ?”፣ ሰዎች ምን ይላሉ?”፣ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?”

ደቀ መዛሙርቱም፡-” አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።” በዚህ ቦታ የተጠቀሱት ሰዎች ሁሉ እግዚአብሄር በዘመናቸው በተሠጣቸው መንገድ ያገለገሉ ሰዎች ብቻ የሆኑ (መለኮትነት የሌላቸው) ነበሩ፡፡

እየሱስ ግን “እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” አላቸው፡፡

ጥያቄው ስለሌሎች ሰዎች የመጣ ሳይሆን ደቄመዛሙርቱ እየሰሙና እያሰላሰሉት፣ እያመኑት፣ እያወቁት ስላላቸው ነገር ነው፡፡ በየቀኑ በአካባቢያችን የምንሰማቸው ነገሮች በአስተሳሰባችንና በእምነታችን ላይ በተለያየ መልኩ ተጽኖ ያመጣሉ፡፡ ስለዚህ እነርሱ ምንን እያመኑ እንደሆነ ለማስገንዘብና ለማረጋገጥ ኢየሱስ ያንን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡  አንዳንድ ጊዜ ጌታ የሚጠይቀን ጥያቄዎች በበለጠ እርሱን እንዲናውቅ፣ ጉዞዎቻችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉን እንጂ ትክክለኛውን መልስ ከእኛ ፈልጎ አይደለም፡፡ በዚህም ክፍል ኢየሱስ ለምን ሰማችሁ ለማለት ፈልጎ ወይ ደግሞ ሰዎች ለምን እንዲህ አሉኝ ለማለት ፈልጎ አይደለም፡፡ ነገር ግን የሰማችሁት ነገር ወዴት እያሳደጋችሁ ነው? እምነታችሁ በምን ላይ የተመሰረተ ነው? ለማለት ነው እንጂ፡፡

ስለ ኢየሱስ ምን ሰሙ?

እምነት ከመስመት ይመጣል፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ጊዜ ሲኖረውና እርሱን ሲሰማ፣ በህይወቱ ውስጥ የእግዚአብሄር የሆነ ነገር እየበዛ፣ እያደገ፣ መመዘኛው እየሆነ ይሄዳል፡፡ የሚሰማው ሰዎችን አከባቢን ሲሆን ደግሞ የሰዎችና አካባቢው የሚናገረው ነገር ሁሉ በሕይወቱ ላይ ተጽዕኖ ከማምጣቱ የተነሳ፣ በፍርሃት፣ በስጋት፣ በሓጢአት፣ በክፋት፣ በጥላቻ፣ በስግብግበነት፣ ወዘተ. እየበዛ ይሄዳል፡፡ እንዴ የትውልድ መሪ፣ ደቀመዛሙርት ይህንን ነገር አጥርቶ ማወቅ አለባቸው፡፡ እግዚአብሄር ምን ተናገረህ? (ኤሊ-ለሳሙኤል፣ እግዚአብሄር ለእያሱ)

ዛሬም ቢሆን ተመሳሳይ ጥያቄ ልንጠየቅ እንችላለን? የምንኖርበት ትውልድ ስለኢየሱስ ምን ይላል? የተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶችና ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና ሕግ አውጪዎች፣ አስተማሪዎችና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ስለ ኢየሱስ ምን ይላል? እኛስ በእነርሱ ፊት ቆመን፣ በእነርሱ መካከል ኖረን፣ እየሱስን እንዴት እናውቀዋለን? ምናልባት ትውልዱ ስለኢሱስ የሚናገረው ፈጽሞ መጥፎ ላይሆን ይችላል፡፡ መልካም የሆነ ነገር ሁሉ ግን እውነት አይደለም፡፡ ስለኢሱስ ብዙ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን (ነብይነቱን፣ አስተማሪነቱን፣ የሃይማኖት መሪነቱን፣ ተዓምር አድራግነቱን…) እየተናገሩ ግን አምላክነቱን፣ ጌትነቱን፣ የመዳን ብቸኛ መንገድ መሆንን ከካዱት እንደማለት ነው፡፡  

“ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።” ፈጣን የሆ መልስ ሰጠ፡፡ ከላይ ሲመጣ በምርምርና በጥናት ስላለሆነ፣ ቅጽበታዊ ነው፡፡ ይህ ደግሞ

ECMYIS, Mekane Yeesus be Scotland, Jesus is the Son of God

ለመናገር የመፍጠኑ ብቻ ሳይሆን እውነትና ከእግዚአብሄር ሃሳብ ጋር መስማማቱ ነው፡፡ በተለይ ጌታ ጠይቆን በጌታ ፊት በቀላሉ የመሰለንን ነገር መናገር አይቻልም፡፡ እርሱ ሁሉንም ያውቃልና፡፡ መሸወድም አይቻልም፡፡  ካላይ ሲገለጥልን ግን በመንፈስ ቅዱሰ አማካይነት፣  ሁሉም ይቀላል፡፡

“ምን እንደምጸልይ አናውቅም መንፍስ ግን ድካማችንን ያግዘናል”፡፡ “ምን እንድት መልሱ አትጨነቁ፣ መንፈስ ቅዱሰ ምን መመለስ እንዳለባችሁ ይሰጣችሃልና”

ኢየሱስ ምን ያስደስተዋል?

 ልክ ጴጥሮስ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ ሲናገር፣ ኢየሱስ “ይህ መረዳት ከሰዎች በተገኘ መረጃ የመጣ እንዳልሆነ፣ ጴጥሮስ እስከዛሬ ባገኘው ልምምድ ላይ ተመስርቶ ያገኘው ግኝት (የምርምሩ ውጤት) እንዳልሆነ ግን “በሰማያት ያለው አባቱ እንደገለጠለት” ነገረው፡፡ ዛሬም የሰዎች የየቀን ምርምርና ልምምድ እግዚእብሄርን እንዲያውቁት እያረገ እንዳልሆን መገንዘብ እንችላለን፣ እንዲህማ ቢሆን ሳይንትስቶች የተባሉ ሁሉ፣ የህዋ ተመራማሪዎች በሙሉ፣ በብዙ በዓለማችን ላይ ለሚገኙ የምርምርና ግኝት ውጤታቸው የሚታወቁ ሁሉ ክርስቲያኖች በሆኑ ነበረ፡፡ በርግጥ ክርስቲና ለብዙ ምርምሮችና ግኝቶች መሠረት እንደሆነ መካድ አይቻልም፡፡  ሆኖም ግን ሰው እግዚአብሄርን እንዲያውቅ የሚያደርገው እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡ እርሱ ካልገለጠለት ሰማያዊ ምስጥርን ሰው የሚያውቅበት አቅም የለውም፡፡

ጌታ ኢየሱስ “ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” ዮሓ.14፡21፡፡

በሌላ ቦታ ደግሞ “ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” ማቴ 11፡27

በዮሃን1፡18  ደግሞ “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።” ይላል፡፡

ለጴጥሮስም እንዲሁ ተገለጠለት፡፡ ጴጥሮስ ይህንን መገለጥ ሲነገር ኢየሱስም ደስ አለው፡፡ “ለእኔ የሚመሰክር አለ” ብሎ የነበረው አባቱ እግዚአብሄር ኢየሱስን ገለጠው፡፡

በመጽሓፍ ቅዱስ ላይ ኢየሱስ ከተደሰተባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ይህ መለጥ በመካከለላቸው ሲገለጥ ነው፡፡ ሌሎች ኢየሱስ የተደሰተባቸውና ያደነቃቸው ነገሮች፣ “ትልቅ እምነት”ና የፍቅር ተግባር ነው (ሳሚራዊው ሰው)፡፡ እነዚህ ሁሉ የእግዝአብሄርን ሓሳብ ከማግኘት ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ “እግዚአብሄርን ማወቅ በላከውም ማመን ይህቺ የዘላለም ሕይወት ናት” ብሎአልና፡፡

በልብህ ብታምን ትጸድቃለህ በአፍህም በመመስከር ትድናለህ፡፡

ብፁዕ ነህ።

የተባረከ ሰው የእግዚአብሄር እውነት የገባውና ያንን ደግሞ የሚናዘዝ/የሚመሰክር ነው፡፡ ለማንኛውም ውጤታማ የሆነ ረጅም ጉዞ፣ የጉዞውን ትክክለኛ መንገድ ማግኘት ትልቁ ነው፡፡

ጴጥሮስን ብፁዕ ነህ ያሰኘው ብቃቱ፣ ከሰው የተለዬ መረዳት ስላለው፣ ወይም ሓይማኖተኝነቱ አልነበረም፡፡ ግን እግዚአብሄር እውነቱን ለሰው ልጅ መግለጥ ሲፈልግ፣ መገለጡን ለመቀበል መዘጋጀቱና መቀበሉ ነው፡፡

ሰማያዊውን ድምጽ የሚሰሙ ሰዎች ሁሌም ብጹዓን ናቸው፡፡

የእግዚአብሄር ግንባታ ሁሌም የሚገነባው ከእግዚአብሄር ዘንድ በመጣው እውነት ላይ እንጂ በሌላ በምንም አይደለም፡፡ ኢየሱስም በዚህ እውነት ላይ (እንደ አለት በሆነው ላይ) ቤተክርስቲያኔን እገነባለሁ አለ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚትገነባው በጠጠሩ ላይ ሳይሆን በአለቱ ላይ ነው፡፡ በጴጥሮስ (ትንሸ ድንጋይ) ላይ ሳይሆን በአለቱ (ፔትራ) ላይ ነው፡፡ ይህንን ቤተክርስቲያን የገሃነም ደጆች አይችሉአትም፡፡ ክፋት ሁሉ ብተባበር፣ በተለያየ ጊዜ የሚወጣው የክፋት ምክር ሁሉ አያጠፋትም፡፡

(By Teklu)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *