SermonsTeachings

ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ

I will make you to become fishers of men አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ወደማንችለው አገልግሎት እንደመጣን ይሰማን ይሆን? መዛሙርቱ ሰዎችን አጥማጆች ለመሆን የሚበቁ አልነበሩም፡፡ ኢየሱስ ግን "እንዲትሆኑ አደርጋችሃለሁ" አላቸው፡፡ ይህ ኢየሱስ ያለው ቃል ደግሞ ከንቱ ቃል አንዳልነበረ የደቀ መዛሙርት ሕይወትና የእኛ ራሳችን ክርስቲያኖች መሆን ይመሰክራል፡፡

Mark 1 14-20 (ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ /I will make you to become fishers of men)

14-15 “ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

16 በገሊላ ባሕርም አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።

17 ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

18 ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።

19 ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ።

20 ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።

የአገልግሎት መቀጠል

የዮሃንስ አሳልፎ መሠጠት፣ ከዚያም መገደል፣ የኢየሱስን አገልግሎት አላስቆመውም፡፡

ዮሓንስ የሰበከው የንስሓን ስበከት ነበረ፡፡ ወደ ወይኒ ያስጣለውም ቢሎም ያስገደለውም ይህው የንስሓ ስብከቱ ነበረ፡፡


የጊዜውን መልእክት መሥጠት

ይህ በዮሓንስ ላይ የደረሰ ነገር በኢየሱስም የሚታወቅ ቢሆነም፣ የስብከቱን ሪዕስ አላስቀረየውም፡፡

ኢየሱስ ለጊዜው ፖሊቲካ እንዲመች፣ የዘመኑም ትውልድ እንዲቀበለው አስቦ፣ ራሱንም ደግሞ ከአደጋ ለመከላከል፣ የስብከቱን ሪዕስና ዓላማ አልቀየረም፡፡

መሠበክ ያለበት የጊዜው መልእክት የሆነው የንስሓ ስብከት ስለነበረና፡፡

 

ንስሓ ምንድን ነው?

በራስ ክፉ መንገድ በመጸጸትና በመመለስ፣ ምህረት ለማግኘት የሚደረግ ጸሎት ነው፡፡ የራስን ሓጢአተኝነት ሳይቀበሉ ትክክለኛ ንስሓ መግባት አይቻልም፡፡

 

የእግዚአብሄር መንግሥትና የንስሓ ግንኙነት

– የእግዚአብሄር መንግሥት የእግዚብሄር ፍጹም አገዛዝና ፍትህ የሚንጸባረቅበት መንግሥት ናት፡፡ ስለዚህ ሓጢአትና ምህረት ያላገኘ ሓጢአተኛ ፈጽሞ ሊገቡባት የማይችሉ መንግሥት ናት፡፡

-ወደ እግዚብሄር መንግሥት ለመግባት ሓጢአተኞችን ወደሚያጸድቀው ጌታ በንስሓ መመለስ ግድ ነው፡፡ እግዚብሄርም ደግሞ ሐጢአተኞች ሊጸድቁበት የሚችሉትን የመዳን ወንጌል ሰጠን፡፡

– ሐጢአተኛው ለመዳን ግን በወንጌሉ ማመን አለበት፡፡

– ስለዚህ የእግዚብሄር መንግሥት ቀርባለች ማለት በሓጢአታቸው ለሚኖሩ ፍርድ፣ ምህረትን ለተቀበሉ ብጽዕና ቀርባለች ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ድግሞ የእግዚአብሄር የጽድቅና ፊትሃዊ አገዛዝ የሚሆንበት ጊዜ መጥቶአል ማለት ነው፡፡

– ይህ ጊዜያዊና አንገብጋቢ መልእክት በዮሓንስ ሲነገር ነበረ፡፡ ሆኖም ግን ይህንን እውነት መናገሩ ዮሓንስን አስያዘው ከዚያም አስገደለው፡፡ ይህ መልእክት ለሰዎች ጆሮ በደንብ ካልደረስ ደግሞ ሰዎች ሁሉ በቅርቡ በሚገለጠው የእግአብሄር ፍርድ ስር መውደቃቸው ነው፡፡

– ስለዚህ ኢየሱስ መልእክቱን በዮሓንስ ላይ በደረሰው ነገር ሳይበገር ቀጥሎ የሰበከው፡፡

 

ኢየሱስ ለምን አልፈራም?

– ሰው በሰው ላይ ስጋን ከመግደል የከፋ ነገር ሊያመጡበት እንደማይችሉ ያውቅ ነበረ፡፡ ሲያስተምርም “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። ” ብሎ ነበረ፡፡ ማቴ   6:28

– ይህም ማለት በሥጋው ላይ የሚደርሰውን መከራ በትዕግስተ በመቀበል ብዙዎችን ሊመጣ ካለው ኩኔኔ ማዳን አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ”

 

ለእኛ ትምህርት

-ሰዎች ከፍርድ እዲያመልጡ የሚቻልንን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ ያ ደግሞ ሊሆን የሚችለው እነርሱ በክርስቶስ ሲሆኑ ነው፡፡ “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፡፡” ሮሜ 8፡1

 

ለምን ወደ ገሊላ?

– ለዚህ አስቸኳይና ወሳኝ አገልሎት ሊጠራቸው ያሰባቸው ሰዎች በዚያ ስለነበሩ ነው፡፡

– ያንንም ያደረገው በዚህ አለም የተናቁትን በመጠቀም በከፍታ ያሉትን ለማውረድ ነው፡፡ 1 ቆሮ 1፡ 25-29 “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ”

 

25 “ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።

26 ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።

27 ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ

28 እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥

29 ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።”

 

ለምን ዓሳ አጥማጆች?

– ሙያው ትእግስትንና ጊዜ መስጠትን ይጠይቃል፡፡ ብዙ ንፋስን፣ብርድን፣ ችግርን መቻል ያስለምዳል፡፡ ደግሞ ውሳኔ ያደረጉ ሰዎች ብቻ ናቸው ሥራውን የሚሠሩት፡፡ ለማጥመድ ብለው ሌሊቱን እንኳ ሳይቀር እየሞከሩ የሚያድሩ፡፡  “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ”

– ኢየሱስ ይህንን ሙያቸውን፣ ልምዳቸውን ለሚሻለላ መጠቀም ፈለገ፡፡ እነርሱ “ማጥማድ” ምን ያህል አድካሚ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡

– “ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። ” ሲጡሩ ወዲው ያላቸውን ትተው ተከተሉት፡፡

– ምናልባት “የሚሻል ሥራ ” እናገኛለን ብለው ይሁን? ቀላል የሆነ ሲራ ለማግኘት?— “ሁሉን ትተን ተከትለንሃል፣ ምን ሊናገኝ አለን”

– ወይስ ምናልባት ደግሞ የኢየሱስ ጥር ከጆሮአቸው አልፎ ወደ ልባቸው ዘልቆ ገብቶ ይሆን?–እንደ ኤልሳይ

 

ለእኛ ትምህርት

-እግዚአብሄር ያለንን ጥቂት/የተናቀ የሚመስል ነገራችንን ለትልቅ ክብሩ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡

– የሰዎችና የሁኔታዎች መክፋት ጥሪያችንንም ሆን የስብከታችን/ መልእክታችንን ይዘት ሊያስቀይረን አይገባም፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን መልእክት ሰዎች ቢወዱትም ባይወዱትም መነገር ያለበት ብቸኛ መልእክታችን ይሁን፡፡

– አንዱ ዮሐንስ ሲያዝ ኢሱስ ራሱ መልእክቱን ሰበከው፣ ቀጥሎም ያንኑን ስብከት የሚሰብኩ ብዙዎችን ጠራ፡፡ የእግዚአብሄር ሐሳብ በክፋት ሊቆም አይችልም፡፡

– ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲጠራ በየተራ ነበረ፡፡ በአንድ ላይ ከአንድ ቦታ ሁሉንም በአንድ ጊዜ አልጠራም፡፡ ስምዖንና እንዲሪያስ እንዴት ሁለት ብቻ ሆነን እንከተለሃለን አላሉም፡፡ በግል የደረሳቸውን ጥሪ ሰምተው ብቻ ተከተሉት፡፡ ከዚያም አራት መሆናቸው ሲበግራቸው አናይም፡፡ በግላችን ለጠራን ጌታ በግል እየታመንንና እየሰማነው ብንከተለው እርሱ ብዙዎችን ወደ እኛ ይጨምራል፡፡ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ” “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ”

 

“በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ”

– እነዚህ ሰዎች ሰዎችን አጥማጆች ለመሆን የሚበቁ አልነበሩም፡፡ በራሳቸው ሊሆኑም አይችሉም፡፡ ኢየሱስ ግን “እንድትሆኑ አደርጋችሃለሁ” አላቸው፡፡

– ወደማንችለው አገልግሎት እንደመጣን ይሰማን ይሆን? እንዴትስ ይከናወንልናል እንል ይሆን?

ኢየሱስ ራሱ “እንድትሆኑ አደርጋችሃለሁ ” ብሎኣል፡፡

ይህ ኢየሱስ “እንድትሆኑ አደርጋችሃለሁ” ያለው ቃል ደግሞ ከንቱ ቃል አንዳልነበረ የደቀ መዛሙርት ሕይወትና የእኛ ራሳችን ክርስቲያኖች መሆን ይመሰክራል፡፡ ያ የኢየሱስ ቃል እውነትና ሕያው ሲለሆነ ነው እነስምዖን ጴጥሮስ በሺዎች ለሚቆጠሩት መመስከር የቻሉት፡፡ ያ ቃል እውነትና ሕያው ሲለሆነ ነው ለእነርሱ የተነገረው መልእክት አልፎ እኛ ጋ ደርሶ ሕይወታችን በወንጌሉ የተለወጠው፡፡ ዛሬም ደግሞ ወደ እኛ እየመጣ ላለው ጥሪ በጎ ምላሽ ብንሰጥ እና “ያለንን ትተን” ጌታን ብከተለው ምስክርነታችን ለብዙ ትውልድ ሊደርስ ይችላል፡፡ “በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ”  ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡

 

በተክሉ የቀረበ – 21 jan 2018

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *