Sermons

የሚያስፈልገው ግን

Posted on
የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነውMary hath chosen that good part, which shall not be taken away from her

ማርታ ኢየሱስን ወደ ቤቷ ጋብዛለች፣ ይህ መቀበል ለማሪያምና ለሌሎች ሰዎች ከኢየሱስ ጋር ቁጭ ብለው ከእርሱ ለመስማት ልዩ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ ማርታ ራሷ ግን ከአገልግሎት ብዛት የተነሳ ከኢየሱስ የመስማት ዕድል እያገኘች አይደለም፡፡ በተጨማሪም፣ ማርታ የአገልግሎቷን ቀልጣፋነት ለማሻሻል ማሪያም ከተቀመጠችበት የኢየሱስ እግር ተነስታ ወደ እርሷ እንትመጣ ፈልጋለች፣ ጠይቃለችም፡፡ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፡፡

Sermons

ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው

Posted on
ecmyis sunday service, Mekane Yesus in Scotland, Christianity, Glasgow church,

ዓለማዊ ዜጎችን በወንጌሉ ቃል የሰማያዊ ዜጎች የማድረግ ሥራ ውስጥ የመንፈሳዊው ድንበር ጥሰት መዘዞች አሉበት፡፡ ይህ ደግሞ መገለጫው በቤተሰዎች መካከል፣ በዘመዶች መካከል፣ በወዳጆች መካከል፣ በህብረተሰብ መካከል የሚመጡ አለመግባባቶች፣ አለመስማማቶችና በተለይም ስለቃሉ በሚነሱት ስዴቶች ናቸው፡፡ ክርስቲና ለሕወትና ለጥሪ የሚንኖርበት ሕይወት እንጂ የምቾት ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡ ያ ማለት ደግሞ ክርስቲያኖች ፈጽሞ የምቾት ሕይወት አያስፈልጋቸውም፣ ወይም በምቾት መኖር አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ደስታ፣ ሠላም፣ በረከት፣ አብሮነትና መንፈስ የደስታቸውና የምቾታቸው መሠረት ነውና፡፡… የሚላኩ ሰዎች ወይም ደቀ መዛሙርት በተለያዬ መንገድ የሚደግፉአቸውን ከእነርሱ በታች አድርገው መቁጠር አይገባቸውም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ሁለቱም እኩል ዋጋ አላቸውና፡፡