Sermons

ሕይወት በገንዘብ

Posted on
የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ

የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለም፡፡ ኢየሱስ በምሳሌው ውስጥ ስለእርሱ የተናገረው ሰውዬ ለብዙ ዘመን የሚበቃው መብል አግኝቶአል ለራሱ ግን ብዙ ዘመን አልነበረውም፡፡ ብዙ ዘመን የሚለበስ ልብስ መግዛት ይችላል፣ ግን ብዙ ዘመን የሚኖር ሰውነት የለውም፡፡ ብዙ ዘመንንም ባገኘው ንብረት መግዛት አልቻለም፡፡ እርሱ የብዙ ዘመን ህልም እያለመና ነፍሱን እያባበለ ነበረ፣ ለካ አንድ ሙሉ ሌሊትም አልነበረውም፡፡ ስለዚህ ዘመንን የሚሠጥ እግዚአብሄር ነውና ለነፍሳችን እና ለዘመናችን ባለቤት ራሳችንን አሳልፈን እንስጥ፡፡