Uncategorized

መልካም ግንኙነት

Posted on
መልካም ግንኙነት ,wilesofthedevil, Mekane Yesus in Scotland, salvation, prayer, resist,

“እግዚአብሄር አምላኬ ሆይ፣ ስለምትወደኝ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ፡፡ ክቡር በሆነውን መልከህና ምሳሌህ ስለፈጠርከኝ ተመስገን፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተመላልሰህ በጠበቅህኝ ቦታ ስላላገኘህኝ ዕቅርታ እጠይቅሃለሁ፡፡ ከውድቀተ አንስቶኝ፣ ከጥፋቴም መልሶኝ ሕይወትን ይሰጠኝ ዘንድ ስለእኔ ስለሞቴውና ከሞትም ስለተነሳው ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ አከብርሃለሁ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከወደደኝና ስለእኔ ነፍሱን ከሰጠው ከልጅህ ከኢየሱስ ጋር መኖርን እፈልጋለሁ፡፡ በምህረትህ ተቀበለኝ፡፡ ያወቅሁ እየመሰለኝ ተታልዬ ከገባሁበት ማንኛውም ሁኔታ አንቴ አውጣኝ፡፡ ስሜን በሕይወት መዝገብ ጻፍልኝ፡፡ አንቴ የምትወደው ዓይነት ሰውም ሆኜ ከአንቴ ጋር በመልካም ግንኙነት መኖር እንዲችል በጸጋህ እርዳኝ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፡፡ አሜን፡፡”