Sermons

እልካችኋለሁ

Posted on
እልካችኋለሁ ፡፡

“ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፡፡” በተኵላ መካከል ማርኮ ለመመለስ ተልእኮ ወስዶ የምንቀሳቀስ በግ ተመልከቱ፡፡ ለራሱም ተስፋ የሌለው ይመስላል፡፡ የወንጌልን ሰባኪነት ተልዕኮ ይዞ የምንቀሳቀስ ሰው እንዲሁ ነው፡፡ ተግዳሮቱ ብዙና ከባድ ነው፡፡ግን የተልዕኮው ባለበት እግዚአብሄር ደግሞ የበለጠ ብርቱና ታማኝ ነው፡፡ ስለዚህ ስመችም ሳይመችም መልእክቱ መተላለፍ አለበት፡፡ “የእግዚአብሔር መንግሥት ግን ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን እወቁ”

Uncategorized

መልካም ግንኙነት

Posted on
መልካም ግንኙነት ,wilesofthedevil, Mekane Yesus in Scotland, salvation, prayer, resist,

“እግዚአብሄር አምላኬ ሆይ፣ ስለምትወደኝ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ፡፡ ክቡር በሆነውን መልከህና ምሳሌህ ስለፈጠርከኝ ተመስገን፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተመላልሰህ በጠበቅህኝ ቦታ ስላላገኘህኝ ዕቅርታ እጠይቅሃለሁ፡፡ ከውድቀተ አንስቶኝ፣ ከጥፋቴም መልሶኝ ሕይወትን ይሰጠኝ ዘንድ ስለእኔ ስለሞቴውና ከሞትም ስለተነሳው ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ አከብርሃለሁ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከወደደኝና ስለእኔ ነፍሱን ከሰጠው ከልጅህ ከኢየሱስ ጋር መኖርን እፈልጋለሁ፡፡ በምህረትህ ተቀበለኝ፡፡ ያወቅሁ እየመሰለኝ ተታልዬ ከገባሁበት ማንኛውም ሁኔታ አንቴ አውጣኝ፡፡ ስሜን በሕይወት መዝገብ ጻፍልኝ፡፡ አንቴ የምትወደው ዓይነት ሰውም ሆኜ ከአንቴ ጋር በመልካም ግንኙነት መኖር እንዲችል በጸጋህ እርዳኝ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፡፡ አሜን፡፡”

Sermons

Easter about Future

Posted on

ከኢየሱስ ከሞት ከመነሳት እውነት (ሃቅ) በተስተጀርባ በተለይ ዛሬ ላይ ያለን ትውልድ በትክክል ማሰብና መገንዘብ ያለብን እውነት እንዳለ አምናለሁ፡፡ እርሱም ትንሳኤው ኢየሱስ ተመልሶ እንደሚመጣ እርግጠኞች ያደርገናል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ገና ከመገደሉ በፊት ለተከታዮቹ ደጋግሞ ኣሳልፎ ሊሠጥና መከራ ሊቀበል እንዳለ፣ ሊሰቀልና በሶስተኛው ቀን ከሞት ስለመነሳቱ እና ወደ አባቱ እንደሚሄድ ተናግሮ ነበረ፡፡ እያንዳንዱም ነገር ከሦስት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተፈጸመ፡፡ ኢየሱስ እንደ ተናገረ ሆኖአል፡፡
(Sermon By Teklu, ECMYIS, Scotland, UK)

Teachings

እምነታችን

Posted on

እንኳን ወደ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ በስኮትላንድ ድረ-ገጽ በደህና መጡ፡፡ የቤተክርስቲያናችን ስም ምንጫችን ከሆነችው እናት ቤተክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ በቀጥታ የመጣ ሆኖ በስኮትላንድ አውድና ኗሪዎችን ማዕከል ባደረገ መልኩ የተመሠረተች ቤተክርስቲያን ናት፡፡ የቤተክርስቲያንቱ ልዩ መታወቂያ የሆነው መካነ የሱስ ትርጉሙ የኢየሱስ መኖሪያ ሥፍራ ማለት ነው፡፡ በአጭሩ ለመጥራት እንዲመች “ መካነ የሱስ በስኮትላነድ ” የምለውን […]