ኢየሱስ ሥራውን ቀጠለ
Posted onጌታ እየሱስ ብዙ የሚሠራቸው ሥራዎች ነበሩት፡፡ በተለይ ደግሞ አጋንንትን ማውጣት እና በሽተኞችን መፈወስ (ቁ.32)፡፡ ይህ ማለት የታሰሩንና ጤናቸውን ያጡትን የሰዎችን ልጆች ነጻ ማውጣት በቀረችው ጊዜ መፈጸም የሚፈልጋቸው ሥራዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህንን ዓላማውን ትቶ እንዲሄድና ከሄሮድስ የመግደል ዕቅድ እንዲያመልጥ ስመክሩት እንመለከታለን፡፡“ከፈሪሳውያን አንዳንዱ ቀርበው፦ ሄሮድስ ሊገድልህ ይወዳልና ከዚህ ውጣና ሂድ አሉት።” (ቁ 31)
ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ የነበረውን ተልዕኮ (ሚሽን) ጨርሶ ከመሄዱ በፊት የተወሰነ ወይም ጥቂት ጊዜ እንደነበረው ያውቅ ነበረ፣ ይናገርም ነበረ፡፡ “ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች” (ዮሓ 9፡4) ብሎአልና። ኢየሱስ ሰው ሊሠራበት የማይችልበት “ሌሊት” ይመጣል ሲል ሰው ሌሊቱ ሳይመጣ የተሠጠውን የቤት ሥራ በርትቶ መጨረስ እንዳለበት ለማሳሰብም ነው፡፡ …..