ምሕረትን አግኝታችኋል
Posted on“እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።” (1 Pet 2:10)
ሰዎቹ አማኞች ናቸው( ቁ7)፡፡ ከዚህ ሞኝነት ከሚመስል እምነት ጋር ተያይዘው በሕይወታቸው ላይ የተከሰተ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ፈጽሞ ማንነታቸውን የሚለውጥ ቅዱስ ስራ ተሠርቶባቸዋል፡፡
እነርሱ ለመዳንና ሰማያዊ ርስት ለውረስ የተጠበቁ ናቸው፡፡ “በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ” (1 ጴጥ 1፡3-5) ይላቸዋልና፡፡
እምነታቸውን ግን ጊዜያዊ ፈታና እያጋጠው ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡(1 ጴጥ 1፡6-7) ይህ ፈታና ምንም ያህል ጊዜያዊ ቢሆንም ልባቸውን ግን ያሳዘናቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህ ጊዜያዊ ሀዘን፣ ከእምነታቸውን ፍጻሜ ስመለከቱ የሚኖራቸውን ስሜት ፈጽሞ ሊለውጠው አልቻለም፡፡ “የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።” (1 ጴጥ 1፡ 9)