ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው
Posted onዓለማዊ ዜጎችን በወንጌሉ ቃል የሰማያዊ ዜጎች የማድረግ ሥራ ውስጥ የመንፈሳዊው ድንበር ጥሰት መዘዞች አሉበት፡፡ ይህ ደግሞ መገለጫው በቤተሰዎች መካከል፣ በዘመዶች መካከል፣ በወዳጆች መካከል፣ በህብረተሰብ መካከል የሚመጡ አለመግባባቶች፣ አለመስማማቶችና በተለይም ስለቃሉ በሚነሱት ስዴቶች ናቸው፡፡ ክርስቲና ለሕወትና ለጥሪ የሚንኖርበት ሕይወት እንጂ የምቾት ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡ ያ ማለት ደግሞ ክርስቲያኖች ፈጽሞ የምቾት ሕይወት አያስፈልጋቸውም፣ ወይም በምቾት መኖር አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ደስታ፣ ሠላም፣ በረከት፣ አብሮነትና መንፈስ የደስታቸውና የምቾታቸው መሠረት ነውና፡፡… የሚላኩ ሰዎች ወይም ደቀ መዛሙርት በተለያዬ መንገድ የሚደግፉአቸውን ከእነርሱ በታች አድርገው መቁጠር አይገባቸውም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ሁለቱም እኩል ዋጋ አላቸውና፡፡