Sermons

ሕይወት በገንዘብ

Posted on
የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ

የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለም፡፡ ኢየሱስ በምሳሌው ውስጥ ስለእርሱ የተናገረው ሰውዬ ለብዙ ዘመን የሚበቃው መብል አግኝቶአል ለራሱ ግን ብዙ ዘመን አልነበረውም፡፡ ብዙ ዘመን የሚለበስ ልብስ መግዛት ይችላል፣ ግን ብዙ ዘመን የሚኖር ሰውነት የለውም፡፡ ብዙ ዘመንንም ባገኘው ንብረት መግዛት አልቻለም፡፡ እርሱ የብዙ ዘመን ህልም እያለመና ነፍሱን እያባበለ ነበረ፣ ለካ አንድ ሙሉ ሌሊትም አልነበረውም፡፡ ስለዚህ ዘመንን የሚሠጥ እግዚአብሄር ነውና ለነፍሳችን እና ለዘመናችን ባለቤት ራሳችንን አሳልፈን እንስጥ፡፡

Sermons

ኢየሱስ ሥራውን ቀጠለ

Posted on
I must work the works of him that sent me, while it is day: the night cometh, when no man can work. “ ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች ”Evangelical Church Mekane Yesus in Scotland, ECMYIS, Glasgow, Uk. Amharic service

ጌታ እየሱስ ብዙ የሚሠራቸው ሥራዎች ነበሩት፡፡ በተለይ ደግሞ አጋንንትን ማውጣት እና በሽተኞችን መፈወስ (ቁ.32)፡፡ ይህ ማለት የታሰሩንና ጤናቸውን ያጡትን የሰዎችን ልጆች ነጻ ማውጣት በቀረችው ጊዜ መፈጸም የሚፈልጋቸው ሥራዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህንን ዓላማውን ትቶ እንዲሄድና ከሄሮድስ የመግደል ዕቅድ እንዲያመልጥ ስመክሩት እንመለከታለን፡፡“ከፈሪሳውያን አንዳንዱ ቀርበው፦ ሄሮድስ ሊገድልህ ይወዳልና ከዚህ ውጣና ሂድ አሉት።” (ቁ 31)
ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ የነበረውን ተልዕኮ (ሚሽን) ጨርሶ ከመሄዱ በፊት የተወሰነ ወይም ጥቂት ጊዜ እንደነበረው ያውቅ ነበረ፣ ይናገርም ነበረ፡፡ “ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች” (ዮሓ 9፡4) ብሎአልና። ኢየሱስ ሰው ሊሠራበት የማይችልበት “ሌሊት” ይመጣል ሲል ሰው ሌሊቱ ሳይመጣ የተሠጠውን የቤት ሥራ በርትቶ መጨረስ እንዳለበት ለማሳሰብም ነው፡፡ …..