Sermons

Kalu Yadinal

Posted on

ማሪያም ሊትወልድ ያለውን ልጅ በሌላ ዮሴፍ በፈለገው ስም መጥራት አይችልም ማለት ነው፡፡ ምናልባት እግዚአብሄር ጣልቃ ገብቶ ለዮሴፍ ይህንን ሃላፊነት ባይሰጠው፣ ኢየሱስ ምን ተብሎ ይጠራ ኖሮአል? በሀገራችን በስም አሠጣጥ ባህል ምናልባት “የሴት ልጅ፣ አፍራሽ፣ ድንጋታ፣ አሳምኖት፣ አስጨናቂ፣ ወይም ሌሎችም በዚህ ላይ ከመናገር የተቆጠብኳቸው ሥሞች ሊሰጡት ይችሉ ነበረ፡፡ እነዚህ ስሞች ደግሞ ከዓላማው ጋር የማይሄዱ ናቸው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሄር፣ “ለጻድቁ” ዮሴፍ የራዕይ አግባብነት ያለውን ስም ለልጁ እንዲያወጣለት ተናገረው፡፡ “ኢየሱስ” ወይም “አዳኝ” “ፈይሳ” ተብሎ እንዲጠራ፡፡ በመገለጡ መሠረት፣ ይህ ስም “ሥጋ ለሆነው ቃል” የተሰጠው፣ እርሱ “ሕዝቡን ሁሉ ከኃጢአታቸው ስለሚያድናቸው” ነው፡፡