EventsqophiAddaaqophiiWelcome

መጪ ዝግጅቶች

እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ፡፡
በግላስጎ ያለችው የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ከሜይ 4-5 2019 (እኤአ) ልዩ የአገልግሎት ጊዜ እያዘጋጀች ትገኛለች፡፡ በመሆኑም ስፕርንግበርን በሚትገኘው አሴምቢል ኦፍ ጎድ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት የአገልግሎቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል፡፡ ቄስ ባርናባስ ዳንኤል (ሌንደን ካለችው መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን) መጥተው የእግዚአብሄርን ቃል ያቀርቡልናል፡፡ የጌታ እራትና የቅዱስ ጥምቀት ስነ-ሥርዓት ቅዳሜ በሚኖረው አገልግሎት ላይ ይፈጸማል፡፡ በጸሎትና በዝማሬ እግዚአብሄርን አብረን የምናመልከበት ጊዜም ይኖረናል፡፡

ECMYIS, Mekane Yesus in Scotland, Rev Barnabs Daniel

የዝግጅቱ ቀን፡ ሜይ 4-5 2019

የዝግጅቱ ቦታ ፡ ፔለርሞ መንገድ፣ ግላስጎ፣ G21 4SX

ሠዓት፡ ከሠዓት በሃላ ከ 2፡00 እስከ 5 ሰዓት

በተጨማሪም ቄስ ባርናባስ እሁድ ጧት ከ11፡00- 12፡00 ሠዓት በሚኖረው የእንግሊዘኛ ፕሮግራም ላይ የእግዚብሄርን ቃል ያቀርባሉ፡፡

ስለዚህ በግላስጎና አከባቢዋ ያሉ ወገኖች ሁሉ በሚኖሩን የአገልግሎት ጊዜያት ላይ ተገኝተው የበረከት ተካፋዮች እንዲሆኑ ይህንን መልእክት በማድረስ እንድታገለግሉአቸው በጌታ ፍቅር እንጠይለን፡፡

የእግዚአብሄር ቃል የሰውን ሕይወት የመለወጥና ኃጢአተኞችን የማዳን አቅም እንዳለሁ፣ የሚሰሙትንም ወደ እግዚአብሄር ልብ እንደሚያቀርብ እናምናለን፡፡

እግዚአብሄር ይባርካችሁ፡፡