አይዳ ብርሃኔ

እኛ፣ የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በስኮትላንድ ምዕመናን፣ በተወደደችው እህታችን አይዳ ብርሃኔ (ሊሊ) በድንገታዊ ሞት ከእኛ መለየት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን፡፡

አይዳ ብርሃኔ ግላስጎ ባለችሁ ማህበረ ምዕመናችን ውስጥ በትጋት፣ በመሰጠት እና በፍቅር ሲትገለገልና ሲታገለግል የነበረች እህት ነበረች፡፡ ሊሊ በሁሉም ዘንድ የተወደደችና የተከበረች እህት ነበረች፡፡ ሊሊ የአንድት ልጅ እናት እናት፣ መልካም ጓደኛ፣ የቃሉ ሰባኪ፣ እና በጣም ትልቅ ነገርን የሚታልም ሴት ነበረች፡፡ አይዳ(ሊሊ) ብርሃኔ እግዚአብሄርንና ሰዎችን የሚትወድ ወጣት ሴት ነበረች፡፡ የሊሊ በሞት ከእኛ መለየትም እጅግ አሳዝኖናል፡፡

ሊሊ ከዚህ ዓለም በሞት ሲትለይ፣ የሦስት ወር ነፍሴ ጡር የነበረች እና ሁለተኛ ልጇን ወልዳ ለመሳም በጉጉት ሲትጠብቅ የነበረች እናት ናት፡፡

የአይዳ ብርሃኔ ከእኛ መለየት ትልቅ ድንጋጤና እና ሃዘንን አምጥቶብናል፡፡ ሆኖም ግን፣ እንደ አንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምና እንደሚትከተል ሰው፣ ከጌታ ጋር ለመኖር ወደ ተሸሌ ሕይወት እንደተሸጋገረች እናምናለን፡፡

በጸሎታችንን በሓሳብ እና ባለን አቅም ከሊሊ ባለቤትና ከሁለት ዓመት ልጇ ጋር እንቆማለን፡፡ እንዲሁም ለሊሊ ቤተሰቦችና እና በኃዘኑ ለተጎዱ ጓደኞቿ በሙሉ የእግዚአብሄርን ማፅናናጽ እንለምናለን፡፡

በተጨማሪም፣ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ወስጥ በጸሎት፣ በሓሳብ፣ በተለያዪ መንገዶች ከሊሊ ቤተሰቦች እና ከእኛ ጋር ለቆማችሁ የግላስጎ ከተማና ከስኮላነድ ውጪ ላላችሁ ወገኞች ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ እግዚአብሄር ይባርካችሁ፡፡

በቀጣይም የሊሊን ቤተሰቦችና ጓደኞች በጸሎታችሁና በሃሳብ እንድትደግፉ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን፡፡

ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በስኮትላንድ

ግላስጎ፣ ብሪታኒያ