Sermons

ኃጢአተኛው ማቴዎስ ተጠራ

I came not to call the righteous, but sinners to repentance.” ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።

የወንጌል ክፍል (ማር.2፡13-17 ኃጢአተኛው ማቴዎስ ተጠራ ፡፡)

 

13 ደግሞም በባሕር አጠገብ ወጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡና አስተማራቸው።

14 ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።

15 በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙ ነበሩ ይከተሉትም ነበር።

16 ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ፦ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው? አሉ።

17 ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።

 

የታሪኩ ዳራን ስንመለከት

ቦታው፡ ክስተቱ የሆነው በቅፍርናሆም ከተማ አከባቢ ባለው የባህር ዳር አጠገብ ነበር፡፡ ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ ሲሄድ ብዙ ሰዎች እንደገና እርሱ ባለበት ተሰበሰቡ፡፡ እንደ ተለመደው ኢየሱስ ቃሉን ነገራቸው፡፡ ኢየሱስ ለሰዎች መስጠት የሚችለው ብዙ ነገር እያለው (ፈውሱ፣ ከአጋንንት ማውጣቱ፣ እንጀራ ማብላቱ፣ ወዘተ. እያለው) ብዙውን ጊዜ ሰዎች ወደ እርሱ ስመጡ አስቀድሞ የሚሰጣቸው ቃሉን ነበር፡፡ ከቃሉ ጋር የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንደሚመጣ ያውቅ ነበርና፡፡ ሲሰራም በቃሉ ነበር፤፤

በጉዞው ላይ ኢየሱስ ሌዊ የተባለውን ማቴዎስን በሥራ ቦታው (ቢሮው፣ የቀረጥ መሰብሰቢያ ቦታው) አገኘውና ጠራው፡፡ ኢየሱስ ሌዊን ለማግኘት ወደ በነበረበት ቦታ ሄደ፡፡ ዛሬም ኢየሱስ ባለህበት / ባለሽበት ቦታና ሁኔታ መጥቶ ያገኝሃል/ ያገኝሻል፡፡

ይህ ጥሪ ደግሞ (ከጥሪው ቀጥሎ ከሆነው ነገር እንደምንገነዘብ) በታወቁ የሃይማኖት መሪዎች እና በአንዳንዶች ዘንድ ትልቅ ጥያቄ ፈጥሮ ነበር፡፡ “እንዴት?”፤ “ለምን?” እንድሉ አድርጎአቸዋል፡፡

በኢየሱስና በአሠራሩ ላይ የተነሣው ጥያቄ የኢየሱስን ትክክለኛነት እና የትምህርቱን ከእግዚብሄር መሆን ላይ የጥርጣሬ ድባብ አጥልቶ ነበረ፡፡

ኢየሱስ ግን እነርሱ ልብ ባላሉትና ባልተገነዘቡት በእግዚአብሄር ቃልና መርሆ መልስ ሠጣቸው / ቻሌንጅ አደረጋቸው፡፡ እግዚአብሄር የሚወድደው ‹‹ምህረትን እንጂ መስዋእትን አይደለም›› በሚለው የነቢዩ ቃል ነበረ፡፡

–     ሌዊ ቀረጥ የሚሰበስበው ምናልት ባህር ተሸግራው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ከሚገቡ ነጋደዎች ሊሆን ይችላል፡፡

–     ሌዊ የሮማውያን ወኪል ነበረ፣ ጥሩ ስራ/ሁሌም ገቢ የሚያስገኝለት ቋሚ ስራ ነበረው— ግን ደግሞ በሕዝብ አይወደድም ነበር፡፡ የኢየሱስን ድምጽ ሲሰማ ግን የያዘውን ሥራ ትቶ ወዲያው ተከተለው፡፡ ወገኔ፣ ምናልባት ካለህበት ሁኔታ የተነሳ፣ ምናልባት የሚትሰማቸው ድምጾች ሁሉ ተስፋ አስቆርጦህ ይሆን? አይዞህ ለየት ያለና በፍቅር የተሞላው የኢየሱስ ድምጽ መጥቶልሃልና በርታ፡፡ እርሱ ለሕይወትህ አድስ ነገር አለው፡፡

–     ምናልባት ሌዊ በሕይወቱ ውስጥ ያለው ጦርነት ሰልችቶት ባለበት ጊዜ ኢየሱስ መውጫ መንገድ የሆነውን ጠሪውን አሰምቶት ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ደግሞ ሌዊ እየተጠላም ቢሆን በሚያገኘው ገቢ ተጽናንቶና ተመቻችቶም እያለ፣ የኢየሱስ የጥሪ ድምፅ ጠልቆ ወደ ልቡ ገብቶ ይሆናል፡፡

–     በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ነገር ሌዊ ወስኗል፡፡ ኤልሳይ ያደረገው አይነት ውሳኔን ያደረገም ይመስላል፡፡ ልዩነታቸው፣ ኤልሳይ ውሳኔውን ለማጽናት ማለትም ወደ ኃላው ላለመመለስ ቆርጦ ለመነሳቱ የሚሆን እርምጃ ሲወስድ፣ ሌዊ ደግሞ በመደሰት (ተቀባይነት ስላገኘ) የይታወቅልኝ እርምጃ ወስዶአል፡፡

–     በተጨማምር ደግሞ ኢየሱስን ወደ ቤቱ ሲጋብዝ፣ ሌዊ መሰሎቹንም በብዛት የጋበዛቸው ይመስላል፡፡ እርሱን የሚመሰሉና እንደእርሱ የተገለሉ ኃጢአተኞች በማዕዱ ዙሪያ ሞልተዋል፡፡

–     ሌላው ሌዊ በጌታ ፊትም ንስሃ ገባ፡፡

–     ኢየሱስ የሓጢአት ሳይሆን የሃጢአተኛ ወዳጅ ነው፡፡ ይህ ባህሪው ዛሬም አልተለወጠም፡፡

–     ሰዎችን ከሓጢአታቸው የተነሳ ፈሪጆ መሸሽ መጽሓፍ ቅዱሳዊ አይደለም ግን ከሃጢአተኝነት ሥራቸው ጋር አለመተባበርና ያንን አለማድረግ እንጂ፡፡

–     ከማያምኑት ጋር በማይሆን አካሄድ አትጠመድ ይላል እንጂ ያላመኑትን ሽሽ የሚል አልተጻፈም፡፡ ቢሆንማ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ” የሚለው ትእዛዝ ትርጉም አይኖረውም ነበር፡፡

ለምን?: ኢየሱስ ራሱ ሓጢአተኞችን ለመፈለግና ለማዳን መጣ

ማን?: ኢየሱስ፣ ደቄ መዛሙርቱ፣ ቀራጮች ና ሓጢአተኞች አብሮ ይበሉ ነበር፡፡ ይህ በዚያን ጊዜ በነበሩት የሃይማኖት ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ኢየሱስ ግን ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ እርሱና ደቄ መዛሙርቱ ከሃጢአተኞች ጋር በሉ፡፡ (በኃላ ይህ ችግር አምጥቶአል የሐ.ሥ.11፡3፣ ገላ.2፡12)፡፡ የጌታ ደቀ መዛሙርት ስንሆን ከእርሱ የምንማረው የምስማማንና ሕብረተሰቡ የሚቀበልልንን ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገውን ሁሉ ነው፡፡

ፈርሳዊያንና ሳዱቃውያን ደግሞ አይተው ደቀ መዛሙርትን ጠየቁአቸው፡፡

እንግዲህ በዛሬው ክፍል ኢየሱስን የሚከተሉት ብዙ ሕዝብ እያለ፣ ኢየሱስ ለዊን ‹‹ተከተለኝ›› አለው፡፡ ይህም ከእኔ ጋር ሂድ ማለቱ ነበር፡፡

እግዚአብሄር ብዙ ጊዜ ሰዎችን ሲጠራ፣ ከዓላማውና በሰውዬው ላይ መስራት በሚፈልገው መሠረት ነው፡፡

ወንድሞቹ እያሉ ዳዊት ተጠራ፣ ሕዝብ እያሉ ገድኦን ተጠራ፣ ብዙ ሰዎች ኢየሱስን ከብበውት እያሉ ሌዊ ተጠራ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለእያንነዳዳችን ያለው የእግዚአብሄር ጥሪን መመርመር ጥሩ ነው፡፡ ሰው ስለጠፋ እግዚአብሄር አልጠራንም፡፡ እኛም ደግሞ ከሌሎች ተሽለን ስለተገኘን አይደለም፡፡ ጌታ በጸጋው ለራሱ ዓላማም ሲጠራን፡፡

ሌላው ደግሞ ሌዊ የመጣለትን ጥሪ ችላ አላለውም፡፡ “በፊቱ ትቆሙና ታጠኑለት ዘንድ ጠርቶአችሃልና ችላ አትበሉ“ ተብሎ እንደ ተጻፈው፡፡

በተጠራም ግዜ ጓደኞቹ ላይ ግብዝ መሆንም አልፈለገም፣ ግን ወደ ቤቱ መጥተው እንድበሉና የተደረገለትን እንዲያዩ አደረጋቸው፡፡

ፈርሳዊያን ጭፍን የሆነ የማግለልን ሥራን ያካሕዱ ነበር፡፡ በህግ ቢመኩም እግዚአብሄር የሚወደውን ግን ፈጽመው አላወቁትም ነበር፡፡

አንዳንድ ጊዜ መልካም ያደረግን እየመሰለን እንገበዛለን፡፡ በእውቀታችን ወይም ልምምዳችን ላይ ብቻ ስለምንደገፍ፣ በጊዜው እግዚአብሄር ማድረግ የሚፈልገውን ለመስማትና ለመቀበል ልቡም ጆሮውም አይኖረንም፡፡

ኢየሱስ የሆነውን አልሆነም አላለም፤ ቀራጩን ማቴዎስ “ጻድቅ ነው” ብሎ አልተከራከረለትም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ሲል መጥቻለው አለ እንጂ፡፡ የተልኮዬ ዋና ተጠቃሚ ለመሆን መስፈርት ያሟላል አለ እንጂ፡፡

ኢየሱስ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ እንደ ዳኛ ሳይሆን ራሱን እንደ ባለመድሃኒት አድረጎ ነበር፡፡

አንድ የሰባኪ ሲናገር፣ ‹‹ለሓኪሞች መፍረድ ይቀላቸው ነበር፣ እኛ ጤናችንን መጠበቅ ስንችል ለበሽታ አጋልጠን ስንሰቃይ ስለሚአዩን፣ ግን እነርሱ ምክርንና መድሃንትን ሰጥተው ይለቁናል፡፡ ዓላማቸው ለማዳን መሞከር ስለሆነ›› ብሎአል፡፡

እንደ ባለመድሃንት ኢየሱስ ሊረዳቸው የሚችለው እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ለሚያውቁ እና በራሳቸው ጽድቅ የማይመኩትን ብቻ ነው፡፡

ፈርሳዊያን ጣት ጠቋሚዎች እንጂ ንስሃ መግባት እደሚያስፈልጋቸው የማያውቁ ሰዎች ነበሩ፡፡

ኢየሱስ ግን ኋጢአተኞችን እጅ ዘርግቶ ይጠራቸው ነበር፡፡ ፈርሳዊያኑም ቢሆን መጥተው ከእድሉ መጠቀም ስችሉ፣ ራሳቸውን ጻድቅ አድርጎ መቁጠርና ሌሎችን ማግለል መቼም አልተውም፡፡

ማቴዎስም ሆነ፣ ሌሎች ስለ ፈርሳዊያንና ጻፎች ጥያቄ መልስ ስሰጡ አትመለከቱም፣ እነርሱ አስቀድሞውኑ የእነርሱን አመለካከት ያውቁ ነበርና (ተቀብለውትማል)፡፡

ይህ ኢየሱስ እያደረገ ያለው ነገር ግን ለእነርሱ ራሱ እንግዳ ነው፡፡ ሃይማኖተኞች አስጠግቶአቸውና ከእነርሱ ጋር በማዕድ ተቀምጠው አያውቁምና፡፡ ማቴዎስ (ሌዊ) የደስታ ግብዣ አዘጋጅቶ ኢየሱስን ወደ ቤቱ ወሰደው፡፡ ይህ ደግሞ ሌሎች ኃጢአተኞችም ሳይቀሩ ከኢየሱስ ጋር ተቀምጠው ቃሉን የሚሰሙበት፣ በማዕድም ከእርሱ ጋር ተቀምጠው የሚበሉበትን አጋጣሚ ፈጠረላቸው፡፡

አንድ ጊዜ በዚህ ሀገር ከንጉስ በታች ሆኖ ሀገርን የሚያስተዳድር ሰው (ዱክ ኦፍ ከንት) ሊሞት ስቃረብ ሓክሙ ሊያበረታታው ፈልጎ፣ አንቴ እኮ ታዋቅና ዝነኛ ሰው ነህ ሲለው ሰውየው ግን፣ ‹‹አይደለም፤ ተወኝ፣ መዳን ካለብኝ እንደ ዋጋ ሳይሆን እንደ ኃጢአተኛ ነው›› አለው ይባላል፡፤

እንግዲህ ዛሬም ጌታ እንድንከተለው ይጠራናል፡፡ እንከተለው ወይስ እንመጻደቅ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *