እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ፡፡ ህንን ቀን ስናስታውስና ስናከብር ትልቁ ቁምነገር እግዚአብሄር ለእኛ በግል ስላደረገልን ነገር ማወቅና ማመስገን ስንችል ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ ጎልጎታ በሚባል ኮረብታ ላይ በመስቀል ላይ የሞተው እኛን ፍለጋ መጥቶ ነው፡፡ ለመሞትም የፈቀደው እኔና እናንተ እንዳንሞት ስለፈለገ ነው፡፡ ይህንን በዓል ሲናከብር የበዓሉን ዋና የሆነውን ኢየሱስንና ዋጋው የተከፈለላትን ነፍሳችንን ረስተን በተለያዩ ነገሮች መባከን የለብንም፡፡
ኢየሱስ ዛሬ ሙት አይደለም፡፡ ኢየሱስ ተነስቶአል፡፡ ኢየሱስ ሁለተኛም ሊሞት አይችልም፡፡ ኢየሱስ “… አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ” ብሎአል፡፡(ራእ 1፡17-18)፡፡
ጌታ ኢየሱስ ከትንሳኤው ቦኃላ ከተከታዮቹ ከጠየቃቸው ነገሮች የተወሰኑትን ማየት የራሳችንን የትንሳኤው አከባበር ሥርዓታችንን ለመፈተሸ ይረዳናል ብዬ አምናለሁ፡፡ (ቀጥሎ ለማንበብ ከላይ ያለውን ምስል ወይም ሪዕሱን ይጫኑ)
መልካም የትንሳኤ በዓል፡፡