Sermons

እውነተኛ አምልኮ

Posted on
worshiping the Lord in truth and Spirit

ዛሬም ቢሆን ‹‹ኃጢአትን መንከባከብ›› ሳይሆን መናዘዝና ከርሷ መመለስ ለሰው ልጅ ነጻነትንና ሕይወትን ያስገኛል፡፡ ቃሉም ‹‹ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው› ይላልና፡፡ በአንድ ሰው ሕይወት፣ አገልግሎት ወይም የአምልኮ ቦታ ውስጥ የእግዚአብሄር ቃል አቅም ካጣ ወይም ከተሻረ እውነተኛ ፈውስና አርነት በዚያ ሰው አይኖርም ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስ በግልጽ ፍትለፍት ተናገራቸው፡፡ ‹‹ዕውሮችስ ብትሆኑ ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን። እናያለን ትላላችሁ፤ኃጢአታችሁ ይኖራል።›› ብሎ ነበር፡፡ ኃጢአታችሁ ይኖራል ማለት ምን ማለት ነው? አለመናዘዝና ንስሓ አለመግባት ለኃጢአት ሕያውነትን ይሰጣል ማለት ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን እንዲህ አይነቱ ባሕሪይ የእግዚአብሄርም ፍርድ ይቀሰቅሳል፡፡ በኤርሚያስ 2፡35 እግዚአብሄር በነቢዩ ሲናገር ‹‹ አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ በእውነት ቍጣው ከእኔ ተመልሶአል አልሽ። እነሆ፦ ኃጢአት አልሠራሁም ብለሻልና በፍርድ እከስስሻለሁ።›› ብሎል፡፡

Sermons

ኢየሱስ ማን ነው?

Posted on
Jesus the son of the Living God

የዕለቱ ክፍል ማቴ 16፡13-20 “ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ። እርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት። እርሱም ፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። […]

Sermons

የዘላለም ሕይወት ቃል

Posted on
leaving bread, Jesus

ጌታ ኢየሱስ “ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ”  ሲል ትምህርቱን ሰምተው ስላልወደዱት ብዙ ሰዎች ትተውት ስሄዱ፣ ‹ለምን ትሄዱብኛላቸሁ? ኑ ትምህርቴን አስተካክላለው› አላላቸውም፡፡ ይልቁንም ከእርሱ ጋር ቀርተው ለነበሩት ጥያቄ አቀረበላቸው ፤ ‹‹እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? ›› በማለት፡፡ ይህንን በማለቱ ኢየሱስ ሰዎቹ ወደ ፈለጉት የመሄድን አማራጭ ሰጣቸው፡፡ ይህንን ያደረገው ግን የሰዎችን ጥፋት (ከእግዚብሄር መንግሥት መኮብለል) ፈልጎ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሕይወትን […]

Sermons

የእግዚአብሔር ታማኝነት

Posted on

በብሉህ ኪዳንም ሆነ በአድስ ክዳን ዛሬንም ጨምሮ፣ እግዚአብሄር ሰዎችን የሚጠራውና የሚያናግረው ስለሰውየው /ስለሴትዮዋ ብቻ ሳይሆን ለሚወዳቸውና ስለሚራራላቸው ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ጭምር ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ሲሆን፣ ሲሠራ በኮምንከሽኖቻችን መካከል የሚያነሳቸው ሰዎች የሉምን? ለኢያሱ ሲናገር “ለአባቶቻቸወን የማልኩላቸውን ታወርሳቸው ዘንድ….” ለደቄ መዘሙርቱ ሲናገር “ሁልጊዜ እስከ አለም ፍጻም ድረስ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ…” ምን እንድሆን? ወንጌልን ላልደረሳቸው እንድያደርሱ… […]

Teachings

እምነታችን

Posted on

እንኳን ወደ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ በስኮትላንድ ድረ-ገጽ በደህና መጡ፡፡ የቤተክርስቲያናችን ስም ምንጫችን ከሆነችው እናት ቤተክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ በቀጥታ የመጣ ሆኖ በስኮትላንድ አውድና ኗሪዎችን ማዕከል ባደረገ መልኩ የተመሠረተች ቤተክርስቲያን ናት፡፡ የቤተክርስቲያንቱ ልዩ መታወቂያ የሆነው መካነ የሱስ ትርጉሙ የኢየሱስ መኖሪያ ሥፍራ ማለት ነው፡፡ በአጭሩ ለመጥራት እንዲመች “ መካነ የሱስ በስኮትላነድ ” የምለውን […]

Welcome

የአምልኮ ሲፍራ

Posted on

   በቅርቡ ወደ ግላስጎ መጥተው የአምልኮ ሲፍራ እየፈለጉ ከሆነ ወይም በግላስጎም ቆይተው የአምልኮ ሲፍራ ያላገኙ ወይም ደግሞ ሕብረት ማድረግ የሚልጉ ከሆነ እንዲሁም ጸሎትንና የእግዚብሄርን ቃል የተጠሙ እንደሆን ወደ ትክክለኛ ድረ-ገጽ መጥተዋል፡፡ የእግዚብሄር ፈቃድ ከሆነ፣ በሚቀጥለው እሁድ መጥተው ከእኛ ጋር እንድያመልኩ ተጋብዘዋል፡፡ መጥተው ከእኛ ጋር እግዚብሄርን በማምለክዎ እንደሚባረኩና እንደሚፅናኑ እምነታችንና ፀሎታችን ነው፡፡ ስለጎበኙን በጣም እናመሰግናለን፡፡ […]