Sermons

ከድካምሽ ተፈትተሻል

Posted on
ከድካምሽ ተፈትተሻል

ችግሮችና ተግዳሮቶች ዘመናትን ቢያስቆጥሩም አንድ ቀን እግዚአብሄር መፍትሄ ማምጣቱ አይቀርም፡፡ ሴትዮ፣ ለ18 ዓመት ብርታቷ ተወስዶባታል፡፡ ይህ ደግሞ ቀና ብላ እንዳትሄድ አድርጓታል፡፡ ሠይጣን ከባድ ሸክም ጭኖባታል፡፡ ሆኖም ግን ከነ ድካሟ በአምልኮ ቦታ የሚትገኝ፣ ነበረች፡፡

ኢየሱስ የመፈታትን ቃል ተናገረባት፡፡ “ ከድካምሽ ተፈትተሻል ” አላት፡፡

ከእንግዲህ ችግርሽ ጊዘው አልፎበታል፣ ከእንገዲህ ጉብጥናሽ ታሪክ ብቻ ነው፡፡ ከድካምሽ ነጻ ወጥተሸል፡፡ ኢየሱስ ዛሬም ነጻ ያወጣል፡፡ ኢየሱስ ዛሬም ከድካም መንፈስ ይፈታል፡፡

Sermons

ሕይወት በገንዘብ

Posted on
የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ

የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለም፡፡ ኢየሱስ በምሳሌው ውስጥ ስለእርሱ የተናገረው ሰውዬ ለብዙ ዘመን የሚበቃው መብል አግኝቶአል ለራሱ ግን ብዙ ዘመን አልነበረውም፡፡ ብዙ ዘመን የሚለበስ ልብስ መግዛት ይችላል፣ ግን ብዙ ዘመን የሚኖር ሰውነት የለውም፡፡ ብዙ ዘመንንም ባገኘው ንብረት መግዛት አልቻለም፡፡ እርሱ የብዙ ዘመን ህልም እያለመና ነፍሱን እያባበለ ነበረ፣ ለካ አንድ ሙሉ ሌሊትም አልነበረውም፡፡ ስለዚህ ዘመንን የሚሠጥ እግዚአብሄር ነውና ለነፍሳችን እና ለዘመናችን ባለቤት ራሳችንን አሳልፈን እንስጥ፡፡

Sermons

የሚያስፈልገው ግን

Posted on
የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነውMary hath chosen that good part, which shall not be taken away from her

ማርታ ኢየሱስን ወደ ቤቷ ጋብዛለች፣ ይህ መቀበል ለማሪያምና ለሌሎች ሰዎች ከኢየሱስ ጋር ቁጭ ብለው ከእርሱ ለመስማት ልዩ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ ማርታ ራሷ ግን ከአገልግሎት ብዛት የተነሳ ከኢየሱስ የመስማት ዕድል እያገኘች አይደለም፡፡ በተጨማሪም፣ ማርታ የአገልግሎቷን ቀልጣፋነት ለማሻሻል ማሪያም ከተቀመጠችበት የኢየሱስ እግር ተነስታ ወደ እርሷ እንትመጣ ፈልጋለች፣ ጠይቃለችም፡፡ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፡፡

Sermons

እልካችኋለሁ

Posted on
እልካችኋለሁ ፡፡

“ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፡፡” በተኵላ መካከል ማርኮ ለመመለስ ተልእኮ ወስዶ የምንቀሳቀስ በግ ተመልከቱ፡፡ ለራሱም ተስፋ የሌለው ይመስላል፡፡ የወንጌልን ሰባኪነት ተልዕኮ ይዞ የምንቀሳቀስ ሰው እንዲሁ ነው፡፡ ተግዳሮቱ ብዙና ከባድ ነው፡፡ግን የተልዕኮው ባለበት እግዚአብሄር ደግሞ የበለጠ ብርቱና ታማኝ ነው፡፡ ስለዚህ ስመችም ሳይመችም መልእክቱ መተላለፍ አለበት፡፡ “የእግዚአብሔር መንግሥት ግን ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን እወቁ”

Sermons

ኢየሩሳሌም እና ኢየሱስ

Posted on
የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም አለ። ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።” (ሉቃ 9፡ 56)

ጥላቻና አለመቀባበል ስር እየሰደደ ሲሄድ ሰዎች ከጌታ ዘንድ የመጣላቸውን ታላቅ እድል እንኳ የሰውና ከሰው ስለሚመስላቸው በቀላሉ ያናንቁታል፡፡ ክርስቶስና ቃሉን፣ በረከቱንም ከድርጅት፣ ከቡድን፣ ከጎሳ፣ ከቋንቋ ጋር አያይዘው ስለሚመለከቱ የመልእክቱ ተጠቃሚዎች መሆን ያቅታቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ከዚህ አይነቱ መታወር ይጠብቀን፡፡

ኢየሩሳሌም:: በብሉህ ክዳን ታሪኳን የምናነብ የሳባ ንግሥት ረጅም መንገድ ተጉዛ የሰማችውን የሰለሞንን ዝና ለማየት ሲትሄድ፣ በሰማሪያ የነበሩ ሰዎች ደግሞ የነገስታት ንጉስ የሆነው ኢየሱስ በመካከላቸው ለማለፍና ለማረፍ ሲፈቅድ እምቢ ብለው አሳደዱት፡፡ የኢየሩሳሌም ሰዎች ደግሞ ከከተማቸው አውጥተው ሰቀሉት፡፡

Sermons

መሸከም አትችሉም

Posted on
ቢነገራቸው መሸከም እንደማይችሉ ኢየሱስ ያውቅ ነበረ፡፡ye cannot bear them now. “12 የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። 13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። 14 እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። 15 ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።”ዮሓ 16፡12-15

ደቄ መዛሙርቱ ሊመጣ ስላለው ነገር ቢነገራቸው መሸከም እንደማይችሉ ኢየሱስ ያውቅ ነበረ፡፡ ስለዚህ “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም” አላቸው፡፡ መንፈስ ቅዱ ሲመጣ የሚናገር ብዙ አለና፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት መቀበልና እርሱን መስማት የኢየሱስን ፈቃድ ማድረግ ነው፡፡ አንዳንዶቹን የሕይወትና የአገልግሎታችንን ሁኔታዎች፣ ጉዞውን ከመጀመራችን በፊት አውቀናቸው ቢሆን በራሳችን እንደማናልፋቸው ስለምናውቅ ጉዞውን ሁሉ የምንጀመር አይመስለኝ፡፡ የመሸከም አቅማችንን የሚያውቅ ጌታ ዛሬም ከአቅማችን በላይ አይሠጠንም፡፡ ስለዚህ ለዛሬና ለሚመጣው ማንኛውም ሁኔታ፣ መንፈስ ቅዱስን መጠበቅ፣ እርሱን መታመንና ቃሉን መስማት እጅግ የበጀናል፡፡

Sermons

መዳን በኢየሱስ

Posted on
መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው፡፡

በምዋርተኝነት መንፈስ የተያዘችና በጥንቆላዋ (በምዋርቷ) ለጌቶቿ ብዙ ትርፍ ታስገኝ የነበረች ሴት ናት፡፡ እርሷ ከሚትናገረው ትንቢት (ምዋርት) ይልቅ እነጳውሎስ የሚሰብኩት ስብከት ለመዳን ጠቃሚ እንደሆነ ትናገራለች፡፡ እነርሱም የሚላኩለት ጌታ እርሷ ከሚታገለግላቸው ጌቶችና ከምዋሪት መንፈስ የሚሻል እንደሆነም ጠቁማለች፡፡ “የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው” እያለች፡፡

Uncategorized

መልካም ግንኙነት

Posted on
መልካም ግንኙነት ,wilesofthedevil, Mekane Yesus in Scotland, salvation, prayer, resist,

“እግዚአብሄር አምላኬ ሆይ፣ ስለምትወደኝ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ፡፡ ክቡር በሆነውን መልከህና ምሳሌህ ስለፈጠርከኝ ተመስገን፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተመላልሰህ በጠበቅህኝ ቦታ ስላላገኘህኝ ዕቅርታ እጠይቅሃለሁ፡፡ ከውድቀተ አንስቶኝ፣ ከጥፋቴም መልሶኝ ሕይወትን ይሰጠኝ ዘንድ ስለእኔ ስለሞቴውና ከሞትም ስለተነሳው ልጅህ ኢየሱስ ክርስቶስ አከብርሃለሁ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከወደደኝና ስለእኔ ነፍሱን ከሰጠው ከልጅህ ከኢየሱስ ጋር መኖርን እፈልጋለሁ፡፡ በምህረትህ ተቀበለኝ፡፡ ያወቅሁ እየመሰለኝ ተታልዬ ከገባሁበት ማንኛውም ሁኔታ አንቴ አውጣኝ፡፡ ስሜን በሕይወት መዝገብ ጻፍልኝ፡፡ አንቴ የምትወደው ዓይነት ሰውም ሆኜ ከአንቴ ጋር በመልካም ግንኙነት መኖር እንዲችል በጸጋህ እርዳኝ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፡፡ አሜን፡፡”

Sermons

እግዚአብሄርን ማስገረም

Posted on
እግዚአብሄርን ማስገረም አይቻልም፡፡ መካነ ኢየሱስ, መካነ የሱስ በስኮትላንድ, እጅህ ንጹህ አይደለም, No surprise!, ስብከት በተክሉ , የግላስጎ አመኞች, የእግዚአብሄርን ጸጋ አልጥልም, እሬ እኔ ማን ነኝ, ያንስብሃል ምስጋናዬ ያንስብሃል ጌታ, ምህረት የበዛለት , Amazing grace, saved by grace, Mekane Yesus, ECMYIS, Mekana Yasus in Scotland, Glasgow christians, Evangelical chuch in glasgow, wash your hand, hand washing

ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት (በመገኘቱ ውስጥ) ተቀመጠ። በዚያም ሆኖ ትክክለኛ ማንነቱን እና የእግዚአብሔርን ቸርነት ማሰብ ጀመሬ። እግዚአብሔር ልብን እንደሚያውቅም ተረዳ።

ሞት ተፈርዶበት እያሌ ከዚያ አስመልጦት በህይወት ያኖረውን ጌታ ንጉሥ ሆኖ ማገልገል ላይ የሚገኘው ዳዊት እግዚአብሄርን ባለእዳ ማድረግ ይችላል ወይ? እኛስ ብንሆን፣ እግዚአብሄር ሳያደርግልን፣ ለእግዚአብሄር የምናቀርበው ነገር ምን ይኖረናል?

Sermons

Easter about Future

Posted on

ከኢየሱስ ከሞት ከመነሳት እውነት (ሃቅ) በተስተጀርባ በተለይ ዛሬ ላይ ያለን ትውልድ በትክክል ማሰብና መገንዘብ ያለብን እውነት እንዳለ አምናለሁ፡፡ እርሱም ትንሳኤው ኢየሱስ ተመልሶ እንደሚመጣ እርግጠኞች ያደርገናል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ገና ከመገደሉ በፊት ለተከታዮቹ ደጋግሞ ኣሳልፎ ሊሠጥና መከራ ሊቀበል እንዳለ፣ ሊሰቀልና በሶስተኛው ቀን ከሞት ስለመነሳቱ እና ወደ አባቱ እንደሚሄድ ተናግሮ ነበረ፡፡ እያንዳንዱም ነገር ከሦስት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተፈጸመ፡፡ ኢየሱስ እንደ ተናገረ ሆኖአል፡፡
(Sermon By Teklu, ECMYIS, Scotland, UK)