Events

Merry Christmas

Posted on

But one thing is assured, God is looking after the one He has sent. Heaven is ready to guide and provide.Don’t be afraid of the disturbed evil forces, Heaven is with you and for you! Just remember God with us, Emmanuel!

Sermons

Kalu Yadinal

Posted on

ማሪያም ሊትወልድ ያለውን ልጅ በሌላ ዮሴፍ በፈለገው ስም መጥራት አይችልም ማለት ነው፡፡ ምናልባት እግዚአብሄር ጣልቃ ገብቶ ለዮሴፍ ይህንን ሃላፊነት ባይሰጠው፣ ኢየሱስ ምን ተብሎ ይጠራ ኖሮአል? በሀገራችን በስም አሠጣጥ ባህል ምናልባት “የሴት ልጅ፣ አፍራሽ፣ ድንጋታ፣ አሳምኖት፣ አስጨናቂ፣ ወይም ሌሎችም በዚህ ላይ ከመናገር የተቆጠብኳቸው ሥሞች ሊሰጡት ይችሉ ነበረ፡፡ እነዚህ ስሞች ደግሞ ከዓላማው ጋር የማይሄዱ ናቸው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሄር፣ “ለጻድቁ” ዮሴፍ የራዕይ አግባብነት ያለውን ስም ለልጁ እንዲያወጣለት ተናገረው፡፡ “ኢየሱስ” ወይም “አዳኝ” “ፈይሳ” ተብሎ እንዲጠራ፡፡ በመገለጡ መሠረት፣ ይህ ስም “ሥጋ ለሆነው ቃል” የተሰጠው፣ እርሱ “ሕዝቡን ሁሉ ከኃጢአታቸው ስለሚያድናቸው” ነው፡፡

Sermons

min litayu

Posted on

የዮሃንስ አገልግሎት የእግዚአብሄርን መንግሥት መቅረቧን ሃጢአተኞች ለሆኑት ለሰዎች ልጆች በሙሉ መናገር ነበረ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ለሰዎች ሁሉ መናገር ዋጋ ያስከፍላል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ለእውነተኛ አገልጋይ (ቢሮው ምንም ይሁን ምን) መሠረቱ፣ መለኪያውና መመዘኛው እንዲሁም መመሪያው ነው፡፡

Sermons

prepare the way

Posted on

እጅግ አስደናቂ የሆነ የምህረት እጅ ዛሬ ለሚመለሱ ሁሉ ተዘርግቶ አለ፡፡ “ኑ!” እያሌ ይጣራል፡፡ “ኑ!”
ቀጣዩ ዘመን እንደዛሬው ሁሉም ተቀላቅሎ የሚኖርበት፣ ስንዴና ገለባ ተሰባጥሮ የሚቀመጥበት ጊዜ አይደለም፡፡ የሚወሰደው እርምጃም እንደዛሬው የማባበልና የርህራዬ አይደለም፡፡ ጎተራውም እሳቱም ሁለተኛ ስንዴውና ገለባው ላይቀላቀሉ ለመለዬት የተዘጋጁ ቦታዎች ናቸው፡፡