Sermons

መሸከም አትችሉም

Posted on
ቢነገራቸው መሸከም እንደማይችሉ ኢየሱስ ያውቅ ነበረ፡፡ye cannot bear them now. “12 የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። 13 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። 14 እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። 15 ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።”ዮሓ 16፡12-15

ደቄ መዛሙርቱ ሊመጣ ስላለው ነገር ቢነገራቸው መሸከም እንደማይችሉ ኢየሱስ ያውቅ ነበረ፡፡ ስለዚህ “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም” አላቸው፡፡ መንፈስ ቅዱ ሲመጣ የሚናገር ብዙ አለና፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት መቀበልና እርሱን መስማት የኢየሱስን ፈቃድ ማድረግ ነው፡፡ አንዳንዶቹን የሕይወትና የአገልግሎታችንን ሁኔታዎች፣ ጉዞውን ከመጀመራችን በፊት አውቀናቸው ቢሆን በራሳችን እንደማናልፋቸው ስለምናውቅ ጉዞውን ሁሉ የምንጀመር አይመስለኝ፡፡ የመሸከም አቅማችንን የሚያውቅ ጌታ ዛሬም ከአቅማችን በላይ አይሠጠንም፡፡ ስለዚህ ለዛሬና ለሚመጣው ማንኛውም ሁኔታ፣ መንፈስ ቅዱስን መጠበቅ፣ እርሱን መታመንና ቃሉን መስማት እጅግ የበጀናል፡፡

Sermons

መዳን በኢየሱስ

Posted on
መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው፡፡

በምዋርተኝነት መንፈስ የተያዘችና በጥንቆላዋ (በምዋርቷ) ለጌቶቿ ብዙ ትርፍ ታስገኝ የነበረች ሴት ናት፡፡ እርሷ ከሚትናገረው ትንቢት (ምዋርት) ይልቅ እነጳውሎስ የሚሰብኩት ስብከት ለመዳን ጠቃሚ እንደሆነ ትናገራለች፡፡ እነርሱም የሚላኩለት ጌታ እርሷ ከሚታገለግላቸው ጌቶችና ከምዋሪት መንፈስ የሚሻል እንደሆነም ጠቁማለች፡፡ “የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው” እያለች፡፡