Sermons

ንስሃ በፍሬ

Posted on
ሉቃ 13፡1-9 ንስሓ በፍሬ ECMYIS ,Evalgelical Church Mekane Yesus, Ethiopian Christian Church in Glasgow, Eritrean Christian Church in Scotland, Evangelical and Lutheran church,cross

በሕይወት ኖረን፣ ተጨማሪ የእግዚአብሄር ቃል፣ ተጨማሪ የእግዚአብሄር መልካምነት፣ የእግዚአብሄር ጥበቃ፣ መልካም ፍሬ ለማፍራት ይረዱን ዘንድ የተቀበልናቸው የጸጋ ሥጦታዎችና ተጨማሪ አገልግሎቶች ሁሉ በአሁንና በሚመጣው ዓመት መካከል ፍሬ አፍርተን እንድንገኝ ነው፡፡ እርሱ (ሠራተኛው) ግን መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት። ወደ ፊትም ብታፈራ፥ ደኅና ነው፤ ያለዚያ ግን ትቈርጣታለህ አለው።” (ቁ 6-9)፡፡

ለእኛ “የሚቀጥለው ዓመት” የተባለው መቼ ይሆን? ከተሠጠን የጸጋና የእንክብካቤ ዘመን ምን ያክሉን እንዲሁ አሳልፈን ይሆን? ፍሬስ ይታይብን ይሆንን? በክርስቶስ በኩል ጽድቅን ከተቀበሉት አማኞችም ያንን የጽድቅ ፍሬ እያፈሩ እንድኖሩ ይፈልግባቸዋል፡፡ጌታ “እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።” ይላልና (ራዕ 3፡19)፡፡

Sermons

ኢየሱስ ሥራውን ቀጠለ

Posted on
I must work the works of him that sent me, while it is day: the night cometh, when no man can work. “ ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች ”Evangelical Church Mekane Yesus in Scotland, ECMYIS, Glasgow, Uk. Amharic service

ጌታ እየሱስ ብዙ የሚሠራቸው ሥራዎች ነበሩት፡፡ በተለይ ደግሞ አጋንንትን ማውጣት እና በሽተኞችን መፈወስ (ቁ.32)፡፡ ይህ ማለት የታሰሩንና ጤናቸውን ያጡትን የሰዎችን ልጆች ነጻ ማውጣት በቀረችው ጊዜ መፈጸም የሚፈልጋቸው ሥራዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህንን ዓላማውን ትቶ እንዲሄድና ከሄሮድስ የመግደል ዕቅድ እንዲያመልጥ ስመክሩት እንመለከታለን፡፡“ከፈሪሳውያን አንዳንዱ ቀርበው፦ ሄሮድስ ሊገድልህ ይወዳልና ከዚህ ውጣና ሂድ አሉት።” (ቁ 31)
ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ የነበረውን ተልዕኮ (ሚሽን) ጨርሶ ከመሄዱ በፊት የተወሰነ ወይም ጥቂት ጊዜ እንደነበረው ያውቅ ነበረ፣ ይናገርም ነበረ፡፡ “ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች” (ዮሓ 9፡4) ብሎአልና። ኢየሱስ ሰው ሊሠራበት የማይችልበት “ሌሊት” ይመጣል ሲል ሰው ሌሊቱ ሳይመጣ የተሠጠውን የቤት ሥራ በርትቶ መጨረስ እንዳለበት ለማሳሰብም ነው፡፡ …..

Sermons

የእምነት ቃል

Posted on
ወንጌላችን እንግዲህ ይህ ነው፡፡ በኢየሱስ አምኖ ስለመዳን፣ በትንሳኤው ጉልበት አምኖም ስለመጽደቅ፡፡ ዛሬ እኛም “ የምንሰብከው የእምነት ቃል ” ይህ ነው፡፡

… ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው፡: እንደ ሓዋሪያው አገላለጽ፣ በዘመኑ የነበሩት እስራኤላዊያን “የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም” (ቁ.3) ። ያ ማለት ምን ማለት ነው? ሰዎች ይጸድቁበትና ይድኑበት ዘንድ የተላከላቸውን ኢየሱስን ማመን ትተው፣ በሙሴ ህግ ላይ ሙጭጭ ብለው በመቆም፣ እጅግ እየደከሙ ግን ደግሞ ሳይጸድቁ ይኖራሉ፡፡
በዘመናችም ይህ በግልጽ ይታያል፡፡ ብዙ ሰዎች ኢየሱስን አምኖ በእርሱ ከመጽደቅ ይልቅ፣ “እኔ ክፉ ነገር አላደረግሁ፣ ሰው አልበድልም፣ አልሰርቅም፣ አላመነዝርም፣ እጾማለሁ፣ ለደሃ እሰጣለሁ፣ ወዘተ. እያሉ የራሳቸውን ጽድቅ ይደረድራሉ፡፡ መጽሓፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ብሎ በግልጽ ያስቀምጣል

Sermons

እርሱን ስሙት

Posted on
እርሱን ስሙት::ኢየሱስን አለመስማት ለሰው ልጅ ሕይወት ትልቅ ጉዳት ነው፡፡ ስለዚህ ነው “እርሱን ስሙት፡፡” የሚል ድምጽ የመጣው፡ecmyis, Mekane Yesus in Scotland, Glasgow Mekane Yesus, Lutheran chuch in Glasgow, Evangelical Christian chuch in Scotland, Glasgow, Amharic Service, Afan Oromo, Tigrigna and Enlsih Bible daily verses. Sundy service

ኢየሱስን አለመስማት ለሰው ልጅ ሕይወት ትልቅ ጉዳት ነው፡፡ ስለዚህ ነው “እርሱን ስሙት፡፡” የሚል ድምጽ የመጣው፡፡
ከማናቸውም ጊዜ የበለጠ፣ በጸጋ ጊዜ ውስጥ አለን፡፡ በብዙ የእግዚአብሄር ምህረትና መልካምነት፣ በጸጋው በሚሠጡ የተለያዩ ለቤተክርስቲያን የተሰጡ ስጦታዎች ተከበን አለን፡፡ ጌታን ከፈለግነው ለማግኘት በካህናት ወይም በመላዕክት በኩል መቅረብ ወይም የበግ ጠቦት፣ ኮርማ ወዘተ.ማቅረብ አያስፈልገንም፡፡ ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተከፈተ በር ሠጥቶናል፣ “ለምኑ ይሠጣችሁሃል፣ ፈልጉ ታገኛላችሁ፣ መዝጊያውን አንኳኩ ይከፈትላችሁሃል” ብሎ፡፡ “በስሜ የምትለምኑትን አብ ይሠጣችሃል” ብሎም መክሮአል፡፡ ግን ደግሞ በዚህ ሁሉ በረከትና ሥጦታ፣ በዚህ ትልቅ ዕድልና ጊዜ በአግባቡ እየተጠቀምን ይሆን?
ስንቶቻችን በዚህን ጊዜ እንኳ ኃጢአት ከብዶን እንኖራለን፣ ስንቶቻችን በዚህን ጊዜ ስንፍናና “እንቅልፍ” ከብዶን የምንናገረውንና የምናደርገውን እስከማናውቅ ድረስ እንቅልፍ ተጫጭኖናል?
እያዬን የማናይ፣ እየሰማን የማንሰማ፣ ጌታ ከእኛ ጋር እያለ የማናስተውል፣ ግን በእንቅልፍ ልብ የምንቀባጥር ጌታም የምታዝበን ስንቶች ነን?
ሕይወታችንና ዘላለማችን በኢየሱስ ውስጥ አለ፡፡ ኢየሱስን መስማት እግዚአብሄር አብ ከእኛ የሚፈለገው ትልቅ ነገር ነው፡፡ “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።” ተብሎ ተጽፎአልና (ዮሃ 3፡26)፡፡ “እርሱን ስሙት፡፡”