Sermons

ለድሆች ወንጌል

Posted on
“ለድሆች ወንጌልን እሰብክ” ድህነት የገንዘብ እጦት ችግር ብቻ እንዳይደል ከዚህ እንገነዘባለን፡፡ ለደሃ ትልቁ የሚያስፈልገው ደግሞ ወንጌል ነው፡፡ ከወንጌል ሰው ሕይወትን ይጠግባል፣ ሠላምን ይጠግባል፣ እረፍትን፣ ደስታን፣ ፍቅርን፣ ተስፋን፣ ወዘተ. ይጠግባል፡፡ECMYIS, mekane Yesus Scotland, Mekane Yesus in SCotland, Glasgow Mekane Yesus, Makane yesus is Glasgow, Mekana Yasuus, Lutheran Church Glasgow, Amharic Service, Oromo, Tigrigna, Christian church in Glasgow, Evangelical Christian church, Salvation,Ethiopinan church glasgow, Erthrian and Ethiopian Christian Church, sermons, Sunday service, Jesus Christ saves. he came to Nazareth, where he had been brought up: and, as his custom was, he went into the synagogue on the sabbath day, and stood up for to read.18 The Spirit of the Lord is upon me, because he hath anointed me to preach the gospel to the poor; he hath sent me to heal the brokenhearted, to preach deliverance to the captives, and recovering of sight to the blind, to set at liberty them that are bruised,19 To preach the acceptable year of the Lord.

“ለድሆች ወንጌልን እሰብክ” ድህነት የገንዘብ እጦት ችግር ብቻ እንዳይደል ከዚህ እንገነዘባለን፡፡ ለደሃ ትልቁ የሚያስፈልገው ደግሞ ወንጌል ነው፡፡ ከወንጌል ሰው ሕይወትን ይጠግባል፣ ሠላምን ይጠግባል፣ እረፍትን፣ ደስታን፣ ፍቅርን፣ ተስፋን፣ ወዘተ. ይጠግባል፡፡ ሰላም ና መልካም እየመሰላቸው ወደ ሲሆል ከሚሄዱ ሰዎች የበለጠ ዕውር የለም፡፡ እግዚአብሄር የለም እያሉ ሰማይንና ምድርን የሞላውን እግዚብሄርን በመካድ ሕይወት ውስጥ ከሚኖሩ የበለጠ እውር ማን ነው? እግዚአብሄርን አገለግላለው፣ አመልካለሁ እያለ ግን በሠይጣን አገዛዝ ሥር ከሚኖር የበለጠ እውር ማን ነው? በአጠቃላይ የሕይወት መንገድ በአጠገቡ እያለ፣ በሞት ጎዳና ከሚራመድ ሰው የበለጠ እውር ማን ነው? ኢየሱስ የመጣው ለእነዚህ ሁሉ ነው፡፡

Sermons

መፍትሄ አለው

Posted on
It is important to listen to Jesus when it comes to godly life. Whatever comes on our way, Jesus has the answer. ECMYIS, EVANGELICAL CHUCH MEKANE Yesus in Scotland. An evangelical Christian church in Glasgow city, Scotland, United Kingdom. Ethiopian and Ertrian Christian church, Sunday service in Amharic. የዮሐንስ ወንጌል 2 1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ 2 ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። 3 የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። 4 ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። 5 እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። 6 አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። 7 ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። 8 አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። 9 አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦ 10 ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። 11 ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።

የአንዱን ቁሳዊ ባዶነት በመሙላት የሌላውን መንፈሳዊ ባዶነት ይቀይራል፡፡ ነገሩ በትክክል ቢመረመር መስካሪዎች አሉ፡፡ ለበረከታችን፣ እኛ ከሓፍረት የተረፍንበት፣ እኛ ከሞት የዳንበት ምክንያቱ ጌታ በልጆቹ ተለምኖ ደርሶልን እንደሆነ የሚመሰክሩ መስካሪዎች አሉ፡፡ እግዚብሄር በጸሎቶቻቸው ስለረዱን ሰዎች የተባረከ ይሁን፡፡ ፀጋው በዝቶልን ለሌሎች እንዲንጸልይ ስለረዳንም ስሙ ይባረክ፡፡ ቀውሶች ሲፈጠሩ፣ የሚበረግጉ ሳይሆን፣ በእምነት አስቀድመው ወደ ጌታ ከዚያም ወደ ሰዎችም የሚሄዱና ለጌታ መታዘዝን የሚያበረታቱ ሰዎች አምልጠው ያስመልጣሉ፡፡

Sermons

በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት

Posted on
Seek the Lord while he may be found; call on him while he is near. Let the wicked forsake his way and the evil man his thoughts. Let him turn to the Lord, and he will have mercy (Isa 55:6-7 NIV)

“እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤ ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።” (ኢሳ 55፡6-7)
ይህ መልእክት የሚመክረን፣ ትኩረታችሁን ወደ እግዚአብሄር እንድንመልስ ነው፡፡ ሰው እርስ በእርሱን እንደሚፈልግ፣ ገንዘብን፣ ሃብትን፣ ዝናን ክብርን፣ ወዘተ. እንደሚፈልግ እግዚአብሄርን “ወዴት አለህ” ብሎ መጠየቅ ቢችል በሕይወቱ ትልቅ ነገር አድርጎአል ማለት ነው፡፡ “እግዚአብሄርን መፈለግ” የራስን ደንነት፣ የራስን ደስታ፣ የራስን ዘላለም፣ የራስን ነጻነት መፈለግ ነው፡፡ ውድ አንባቢ ሆይ፣ አንተም/አንቺም አሁን ጊዜ አለህ/ሽ፡፡ አሁን፡፡ አሁን ማለት የሚትፈልገውን ለመጠየቅ፣ ለመጸለይ፣ ለማንበብ፣ ለመስማት፣ ለማሰብ፣ ለማስታወስ፣ ስትችል ማለት ነው፡፡ አሁን የሚባለው የጊዜ መቁጠሪያ በእጅህ እያለ፣ እግዚአብሄርን ፈልገው፡፡

Sermons

ልጆች ይጠይቃሉ

Posted on
ልጆች ከሚያዩት ነገር ተነስተው ይጠይቃሉ፣ ይፈጥራሉ፣ እይታቻውና በምናባቸው ስእሎችን ይስላሉ፡፡ እነዚህም ሁሉ ተያያዥነት አላቸው፡፡

ልጆች ከሚያዩት ነገር ተነስተው ይጠይቃሉ፣ ይፈጥራሉ፣ በምናባቸው ስእሎችን ይስላሉ፡፡ እነዚህም ሁሉ ተያያዥነት አላቸው፡፡
ልጆች ቃላትን መማር የሚጀምሩት በቤተሰቦቻቸው ዘንድ ተደጋግሞ በሚነገር፣ በቤታቸውም ሆነ በአከባቢአቸው ኖሮ ከሚሰሙትና ከሚመለከቱት ነገር ተነስተው ነው፡፡ ቃላትን ቢቻ ሳይሆን ጽንሴ-ሓሳቦችንም እንዲሁ፡፡ ስለዚህ አከባቢና በዓይን የሚታዩ ነገሮች በትውልድ ላይ የሚያመጣውን ነገር የተረዱ የተለያዩ አካላት በዘመናት ውስጥ ትውልዶችን የራሳቸው ለማድረግ በብዙ መልኩ እየሰሩ ነበሩ፤ ዛሬም እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በተለይ በዘመናችን በሚታዩ ተንቀሳቃሽም ሆነ ተንቀሳቃሽ ባልሆኑ ስእሎች በመጠቀም፣ በጌሞች፣ በአሻንጉልቶችና በሙዝቃዎች ትውልድ ገና ክፉና ደጉን ሳያውቅ እነርሱ የሚፈልጓቸውን ነገሮች (ሓሳቦችና ፍልስፍናዎች) ያስተምሩአቸዋል፡፡ ገና ከልጅነት መናገር፣ መዘመር፣ ማሰብ፣ መለማመድና ያንንም መሠረት አድርገው መጠበብ ይጀምራሉ፡፡ በኢያሱ መጽሓፍ ውስጥ ስናነብ እንዲህ ይላል፡- “ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው።” (4፡20) ቃሉ “ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። ቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።” ይላልና (ዘዳግም 6:7-9)