Sermons

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር

Posted on

በዓሉን ፈጽመው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ግን አንድ አስደንጋጭ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ “ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።” (ቁ 43) ኢየሱስ ”በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው:: የሚገርመው ይህንን ኢየሱስ የተናገረውን እውነት በዚያ የነበሩት ሰዎች አላስተዋሉትም፡፡ (ቁ 50) ኢየሱስ እግዚአብሄር አባቴ ነው ብሎ የተናገረውን ብዙዎች በተለምዶ የሚባል ሃይማኖታዊ ንግግር ወይም ደግሞ የሕፃን ንግግር አድርገውታል፡፡ ስለዚህም ምን ለማለት እንደፈለገ ያስተዋለና ተመጣጣኝ ምላሽ የሠጠ በዚያ አልነበረም፡፡

Events

ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል

Posted on
ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል Merry Chrismas, ECMYIS, mekane Yesus in Sctland

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህች ዓለም በመምጣቱ ብዙ ታሪኮች ተለውጦአል፣ ብዙ ጥያቄዎች መልስ አግኝተዋል፣ ብዙ እንቆቅልሾች ተፈተዋል፣ ብዙ በሽተኞችም ተፈውሰዋል፣ ብዙ ሙታኖችም ሕይወት አግኝተዋል፡፡ ይህ ብቻ ደግሞ አይደለም፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መምጣት ብዙ ጦሪነቶችን፣ ብዙ ሰልፎችን፣ ብዙ ስደቶችንም አስከትሎአል፡፡

ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው፣ ትልቅ የሕይወት ብርሃን በምድር ላይ በመብራቱ የብዙዎች ጨለማ ሲበራ፣ ብዙ የጨለማ ወዳጆችና በብርሃን ውስጥ መስራት የማይችሉቱ ደግሞ ላለመጋለጥ ብዙ ጦሪነቶችን በማወጃቸው ነው፡፡ አብዛኞቹ ጦሪነቶች የታወጁት በሰዎች አእምሮ ውስጥ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በገሃዱ አለም በግልጥ በታሪክ ተመዝግበው የሚገኙ ጦሪነቶች ናቸው፡፡

Sermons

ጋሻህ ነኝ

Posted on
ጦሪነትና ተያይዞ ያለው ፍለጻ ወይም ጦር ባይኖር ጋሻ ባላስፈለገ ነበር፡፡ ጋሻ የሚጠቅመው የሚወረወርብን ነገር ሲኖር ከእርሱ እንዲሸፍነንና እንዲያድነን ነው፡፡ እግዚአብሄርም ለአብርሃም “እኔ ጋሻህ ነኝ” ሲለው፣ በአብርሃም ቀሪው ዘመን የሚቀጥል ጦሪነትና ሰልፍ ሊኖር እንደሚችል አመልካች ነው፡፡

ጦሪነትና ተያይዞ ያለው ፍለጻ ወይም ጦር ባይኖር ጋሻ ባላስፈለገ ነበር፡፡ ጋሻ የሚጠቅመው የሚወረወርብን ነገር ሲኖር ከእርሱ እንዲሸፍነንና እንዲያድነን ነው፡፡ እግዚአብሄርም ለአብርሃም “እኔ ጋሻህ ነኝ” ሲለው፣ በአብርሃም ቀሪው ዘመን የሚቀጥል ጦሪነትና ሰልፍ ሊኖር እንደሚችል አመልካች ነው፡፡

Sermons

በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና

Posted on
Glasgow evangelical christians, Mekane Yesus in Scotland, UK, United Kingdom, Mekane Yesus, Erithrans and Ethiopians Christian church, Lutheran በማናቸውም ቦታና ሁኔታ ያለው ሰው የተለያዩ የሕይወት ውጣውረዶች ሊገጥሙት ይችላሉ፡፡ የዳዊት ሕይወት በማያቋርጥ ሰልፍና ለአደጋ አጋላጭ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም በየቀኑ በእግዚአብሄር መታመንን፣ መጸለይን፣ ጥንቃቄንና ትጋትን አስተምሮታል፡፡ እግዚአብሄር በመከራ ቀን ልጆቹን የሚሰውርበት “ድንኳን” አለው፣ በድንኳኑም ውስጥ ልዩ “መሸሸጊያ” ክፍል አለው፡፡ Church in Glasgow በድንኳኑ

በማናቸውም ቦታና ሁኔታ ያለው ሰው የተለያዩ የሕይወት ውጣውረዶች ሊገጥሙት ይችላሉ፡፡ የዳዊት ሕይወት በማያቋርጥ ሰልፍና ለአደጋ አጋላጭ ሁኔታ ውስጥ የነበረ ቢሆንም ሁኔታው በየቀኑ በእግዚአብሄር መታመንን፣ መጸለይን፣ ጥንቃቄንና ትጋትን አስተምሮታል፡፡ እግዚአብሄር በመከራ ቀን ልጆቹን የሚሰውርበት “ድንኳን” አለው፣ በድንኳኑም ውስጥ ልዩ “መሸሸጊያ” ሥፍራ አለው፡፡

qophii

ልባችሁ እንዳይከብድ ተጠንቀቁ

Posted on
ልባችሁ እንዳይከብድ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ መካነ የሱስ፣ ግላስጎ መካነ የሱስ፣ ስኮትላንድ፣ ዪናይትድ ኪንግደም፣ Lutheran Church in Glasgow, ECMYIS, evangelical Church mekane Yesus in Scotland, Luk 21 25-36 'And there shall be signs in the sun, and in the moon, and in the stars; and upon the earth distress of nations, with perplexity; the sea and the waves roaring; Men's hearts failing them for fear, and for looking after those things which are coming on the earth: for the powers of heaven shall be shaken.

ሰው በእግዚአብሄር መታመን ሲያቅተው ነገሮችን ሁሉ በራሱ መጀመሪና መጨረስ ስለሚሞክር፣ በራሱ ዓቅም ልሠሩ ወደማይችሉ ነገሮች ስደርስ በብዙ ጭንቀርትና አላስፈላጊ የሕይወት ጎዞዎች ወስጥ ይገባል፡፡
ይህ ደግሞ በኢየሱስ ትምህርት ውስጥ እንደተገለጠው፣ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳያፈራ በማድረግ ሰው ገለባ የሆነ ሕይወት ብቻ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በማቴ13፡22 “በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል።” ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ እያላችሁ “ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” ብሎ አስጠነቀቀ፡፡ ሐዋሪያውም ጳውሎስ፣ “ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።” (ፊልጵ 4፡6)