Sermons

ለራሳችሁ ተጠንቀቁ

Posted on
ለራሳችሁ ተጠንቀቁ

“ብዙዎች፦ እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። “ ይህ ማለት ሓሰተኛ ክርስቶሶች ይነሳሉ ማለት ነው፡፡ በእኔ ስም ብዙዎችን ያስታሉ፡፡ ብዙዎችንም ያስከትላሉ፡፡ ዛሬም ባለንበት ዓለም በብዙ ሀገራት ክርስቶስ ነኝ እያሉ የተነሱ ብዙዎች አሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ክርስቶስ ማለት የተቀባ ማለት ነው፡፡ ብዙዎች ደግሞ ቀጥታ የግርኩን ስያሜ ባይጠቃሙም፣ በየአከባቢው ባለው ቋንቋ እየተጠቀሙ “እኔ የተቀባው ነኝ” በምል ስም ሰዎችን ከእውነተኛው ክርስቶስና ከቃሉ የሚመልሱ አሉ፡፡ ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ አላቸው፡፡ ውሸተኛ መሆኑ የሚታወቅ ሰው መጥቶ አድስ ነገር ቢነግረን እንደማንሰማው እርግጠኛ ነኝ፡፡ ግን አሳች የሚባለው፣ ራሱን እየለወጠ፣ ንግግሩን፣ አድራሻውን፣ ጉርብትናውን፣ አጋርነቱንና ስሙን እየለዋወጠ እውነት በመምሰል የሚገለጠው ነው፡፡

Sermons

ምሕረትን አግኝታችኋል

Posted on
አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋልGod has the power to heal and save a person! By preaching the true word of God and trusting God for the fulfilment of his word, Mekane Yesus in Scotland, Glasgow city, United Kingdom, points out to Him who is the saviour, the creator and sustainer of the whole Universe, God and His Son Jesus Christ. ECMYIS is a church with Lutheran background. ECMYI church is set up by mainly members of the Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus,EECMY and Eritrean Lutheran church to reach humanity in Scotland. God saves! EECMY, ECMYIS, Mekane Yesus in Scotland, Mekane Yasus, Ethiopian Church in Glasgow, Scotland, Ethiopian Christina Community, Evangelical Church, Lutheran chuch in Glasgow, Scotland. we meet in St George's Tron Church, Church of Scotland, city center. Christian family, infant baptism is also practiced here. Eritrean Christian church from Lutheran chuch of Eritrea. Mark 10:23-31, Glasgow Mekane Yesus, Glasgow Ethiopian Christians, Glasgow Evangelical church, Mekane Yesus,

“እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።” (1 Pet 2:10)
ሰዎቹ አማኞች ናቸው( ቁ7)፡፡ ከዚህ ሞኝነት ከሚመስል እምነት ጋር ተያይዘው በሕይወታቸው ላይ የተከሰተ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ፈጽሞ ማንነታቸውን የሚለውጥ ቅዱስ ስራ ተሠርቶባቸዋል፡፡

እነርሱ ለመዳንና ሰማያዊ ርስት ለውረስ የተጠበቁ ናቸው፡፡ “በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ” (1 ጴጥ 1፡3-5) ይላቸዋልና፡፡

እምነታቸውን ግን ጊዜያዊ ፈታና እያጋጠው ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡(1 ጴጥ 1፡6-7) ይህ ፈታና ምንም ያህል ጊዜያዊ ቢሆንም ልባቸውን ግን ያሳዘናቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህ ጊዜያዊ ሀዘን፣ ከእምነታቸውን ፍጻሜ ስመለከቱ የሚኖራቸውን ስሜት ፈጽሞ ሊለውጠው አልቻለም፡፡ “የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።” (1 ጴጥ 1፡ 9)

Sermons

ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ

Posted on
I will make you to become fishers of men አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ ወደማንችለው አገልግሎት እንደመጣን ይሰማን ይሆን? መዛሙርቱ ሰዎችን አጥማጆች ለመሆን የሚበቁ አልነበሩም፡፡ ኢየሱስ ግን "እንዲትሆኑ አደርጋችሃለሁ" አላቸው፡፡ ይህ ኢየሱስ ያለው ቃል ደግሞ ከንቱ ቃል አንዳልነበረ የደቀ መዛሙርት ሕይወትና የእኛ ራሳችን ክርስቲያኖች መሆን ይመሰክራል፡፡

ወደማንችለው አገልግሎት እንደመጣን ይሰማን ይሆን? እንዴትስ ይከናወንልናል እንል ይሆን? ደቀ መዛሙርቱ ሰዎችን አጥማጆች ለመሆን የሚበቁ አልነበሩም፡፡ በራሳቸው ሊሆኑም አይችሉም፡፡ ኢየሱስ ግን “እንድትሆኑ አደርጋችሃለሁ” አላቸው፡፡ ኢየሱስ ራሱ “እንድትሆኑ አደርጋችሃለሁ ” ብሎኣል፡፡ ይህ ኢየሱስ “እንድትሆኑ አደርጋችሃለሁ” ያለው ቃል ደግሞ ከንቱ ቃል አንዳልነበረ የደቀ መዛሙርት ሕይወትና የእኛ ራሳችን ክርስቲያኖች መሆን ይመሰክራል፡፡ ያ የኢየሱስ ቃል እውነትና ሕያው ሲለሆነ ነው እነስምዖን ጴጥሮስ በሺዎች ለሚቆጠሩት መመስከር የቻሉት፡፡