Sermons

የእግዚአብሄርን ክብር ማየት

Posted on
Mekane Yesus in Scotland,evangelical church Mekane Yesus in Scotland,evangelical church Scotland,evangelical churches glasgow scotland, evangelical lutheran church in scotland,baptist church glasgow scotland,evangelical union church scotland, evangelical church scotland,evangelical church glasgow,evangelical churches glasgow scotland,evangelical lutheran church in scotland, mekane Yesus

ኢየሱስ በዚያ ክብር ሆኖ/ ተገልጦ የሚያከብራቸው፣ የሚባርካቸው፣ የሚያመሰግናቸው ሰዎች እንዳሉም ጭምር ይህ የመጽሓፍ ቅዱስ ክፍል ይናገራል፡፡ እነዚያ ሰዎች ያንን ክብር ሊያዩ የሚችሉት በዚህ ክፍል መሠረት፣ ራስን ዝቅ በማድግ መንገድ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ክብር ማየት መታደል ነው፡፡ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትም ደግሞ ኢየሱስን በመመስከር፣ እርሱ ለሓጢአተኞች እንዲታወቅ በማድግ፣ ያም ሊያመጣባቸው የሚችለውን መከራ በመቀበልም ጭምር ነው፡፡ እነርሱ ኢየሱስ ሓጢአተኞች ናቸው ባላቸው ፊት ከመመስከራቸው የተነሳ ሓጢአተኞቹ በንስሓ ወደ እግዚአብሄር ይመለሳሉ፡፡ የኢየሱስንም ጌትነት ያውቃሉ፡፡ ጌታን ለመታዘዝም/ለመቀበልም ሆነ ላለመታዘዝ/ላለመቀበል ውሳኔ ያደርጋሉ፡፡

Sermons

ጌታ ሁልጊዜ ትልቅ

Posted on
ጌታ ሁልጊዜ ትልቅ Ethipian and Eritrean Lutheran Christians in Scotland. Amharic Service,Evalgelical Church Mekane Yesus, Ethiopian Christian Church in Glasgow, Eritrean Christian Church in Scotland, Evangelical and Lutheran church,ECIS

ጌታ ሁልጊዜ ትልቅ ነው፡፡ ለደቀ መዛሙርት እንደ ትንቢት የተነጋራቸው እና እንዲጠባበቁት የተጠየቁት ኢየሱስ ተላልፎ እንደሚሠጥ፣ እንዲሞት፣ እንዲነሳና ወደ አባቱ እንዲሄድ ከዚያም ተመልሶ እንደሚወስዳቸው ነበረ (ዮሓ 14፡ 1-6)፡፡ ከእነዚህ አብዛኛው ተፈጽሞ ስላሌ ለእኛ የምንጠብቃቸው ነገሮች አይደሉም፡፡ ግን ለእኛ የቀረ አንድ ነገር ብኖር ኢየሱስ ዳግም እንደሚመጣና እንደሚወስደን ነው፡፡ ለዚህስ እኛ እየተዘጋጀንና ሌሎችን እያዘጋጀን ነው ወይ?

Sermons

ኃጢአተኛው ማቴዎስ ተጠራ

Posted on
I came not to call the righteous, but sinners to repentance.” ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።

ኃጢአተኛው-ማቴዎስ-ተጠራ፡፡ ወንድሞቹ እያሉ፣ ዳዊት ተጠራ፣ ሕዝብ እያሉ፣ ገድኦን ተጠራ፣ ሌሎች እያሉ ማቴዎስም ተጠራ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለእያንነዳዳችን ያለው የእግዚአብሄር ጥሪን መመርመር ጥሩ ነው፡፡ ሰው ስለጠፋ እግዚአብሄር አልጠራንም፡፡ እኛም ደግሞ ከሌሎች ተሸለን ስለተገኘን አይደለም፡፡

Sermons

ዓላማህን ተጠንቀቀው

Posted on
ዓላማህን ተጠንቀቀው Evalgelical Church Mekane Yesus, Ethiopian Christian Church in Glasgow, Eritrean Christian Church in Scotland, Evangelical and Lutheran church,raodmap,road,karaa, menged,meged,ecis,

ዓላማህን ተጠንቀቀው ፡፡ ዛሬ በምናየው የኢየሱስ ትምህርት ውስጥ እንደ ክርስቲያን የምንኖርበትን ዓላማ ከተውንና ካልተጠነቀቅነው ጠቃሚነታችንን ተውን ማለት ነው፡፡ ጠቃሚነቱን የተወ ነገር ደግሞ ክብር አይጠብቀውም፡፡

Sermons

እውነተኛ አምልኮ

Posted on
worshiping the Lord in truth and Spirit

ዛሬም ቢሆን ‹‹ኃጢአትን መንከባከብ›› ሳይሆን መናዘዝና ከርሷ መመለስ ለሰው ልጅ ነጻነትንና ሕይወትን ያስገኛል፡፡ ቃሉም ‹‹ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው› ይላልና፡፡ በአንድ ሰው ሕይወት፣ አገልግሎት ወይም የአምልኮ ቦታ ውስጥ የእግዚአብሄር ቃል አቅም ካጣ ወይም ከተሻረ እውነተኛ ፈውስና አርነት በዚያ ሰው አይኖርም ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስ በግልጽ ፍትለፍት ተናገራቸው፡፡ ‹‹ዕውሮችስ ብትሆኑ ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር፤ አሁን ግን። እናያለን ትላላችሁ፤ኃጢአታችሁ ይኖራል።›› ብሎ ነበር፡፡ ኃጢአታችሁ ይኖራል ማለት ምን ማለት ነው? አለመናዘዝና ንስሓ አለመግባት ለኃጢአት ሕያውነትን ይሰጣል ማለት ነው፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን እንዲህ አይነቱ ባሕሪይ የእግዚአብሄርም ፍርድ ይቀሰቅሳል፡፡ በኤርሚያስ 2፡35 እግዚአብሄር በነቢዩ ሲናገር ‹‹ አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ በእውነት ቍጣው ከእኔ ተመልሶአል አልሽ። እነሆ፦ ኃጢአት አልሠራሁም ብለሻልና በፍርድ እከስስሻለሁ።›› ብሎል፡፡