Sermons

የዘላለም ሕይወት ቃል

leaving bread, Jesus

ጌታ ኢየሱስ “ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ”  ሲል ትምህርቱን ሰምተው ስላልወደዱት ብዙ ሰዎች ትተውት ስሄዱ፣ ‹ለምን ትሄዱብኛላቸሁ? ኑ ትምህርቴን አስተካክላለው› አላላቸውም፡፡ ይልቁንም ከእርሱ ጋር ቀርተው ለነበሩት ጥያቄ አቀረበላቸው ፤ ‹‹እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? ›› በማለት፡፡ ይህንን በማለቱ ኢየሱስ ሰዎቹ ወደ ፈለጉት የመሄድን አማራጭ ሰጣቸው፡፡ ይህንን ያደረገው ግን የሰዎችን ጥፋት (ከእግዚብሄር መንግሥት መኮብለል) ፈልጎ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሕይወትን ያልመረጡ ካሉ በአካል በዚያ ቢኖሩም አስቀድሞውኑ ከእርሱ ጋር ስለሌሉ ነው እንጂ፡፡ ፍላጎታችንን በእግዚአብሄር ቃል መመርመር እንጂ የጌታን ቃል በፍላጎታችን መመርመር ስህተት ነው፡፡ ስላልተመቸኝ የእግዚብሄር ቃል ስህተት ሊሆን አይችልም

[read more=”በሙሉ ላንብብ…” Less=”አሳጥርልኝ…”]

የእለቱ የወንጌል ክፍል ዮሓንስ 6:51-69

51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው። 52 እንግዲህ አይሁድ፦ ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል? ብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ። 53 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። 54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። 55 ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። 56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። 57 ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል። 58 ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡ 59 በቅፍርናሆም ሲያስተምር ይህን በምኵራብ አለ። 60 ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ፦ ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ። 61 ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያሰናክላችኋልን? 62 እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል? 63 ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። 64 ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ። ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ከመጀመሪያ ያውቅ ነበርና። 65 ደግሞ፦ ስለዚህ አልኋችሁ፥ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ። 66 ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም። 67 ኢየሱስም ለአሥራ ሁለቱ፦ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ። 68 ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ 69 እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።”

ኢየሱስ ለሰዎች የማይገባ፣ ሰዎችም ቢሰሙት በቀላሉ ጥለውት እንዲሄዱ የሚያደርጋቸውን ነገር በመቅደስ ውስጥ በይፋ አስተማረ፡፡ በቃሉ መሰናከላቸውን ወይም አለመቀበላቸውንም እያወቀ እንኳ ቀጥሎ ማብራራቱን ቀጠለ፡፡ በእግዚአብርሄር መንግስት አሠራር ውስጥ አቀራረብና አደራረግ እንደየአውዱ መስተካከል ቢቻልም እውነት ግን ተቀባይነት ቢኖረውም ባይኖረውም ሳይሸራረፍ መነገር አለበት፡፡ ለዚህ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ራሱን በመስዋዕትነት ለማቅረብ የመጣው፡፡ እግዚአብሄር ሊዋሽ ስለማይችልና ሃጢአተኛውን ዋሽቶ ስለማያጸድቀው ኢየሱስ የእኛን የኃጢአተኞችን ዕዳ መክፈል ነበረበት፡፡

ሌላው በዛሬው ክፍል ውስጥ የምናየው ነገር፣ ኢየሱስ ሰዎችን ያውቃል (ቁ.64)፡፡ ማወቁ ግን እንዲያገላቸው አላደረገውም፡፡ ማን በእርሱ እንደማያምን እያወቀ፣ ማን ደግሞ እንደሚክደውም እያወቀ፣ እስከ መጨረሻው ድረስ አብሮአቸው ቀጠለ፡፡

ለቶማስ እምነቱን የሚያጸናበት ጊዜ (ሁለተኛ አድል) እንዳለው ያውቅ ነበረ፡፡ ይሁዳም በመንገዱ ስለሚቀጥል/ንስሓ ስለማይገባ ሕይወቱ በአደጋ ላይ እንዳሌ ያውቅ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ኢየሱስ እየተከተሉትም ስለማያምኑበትና አሳልፎ ሊሠጠው ስላለው ሰው ከመጨነቅ ይልቅ በምድር ላይ በነበረው ጊዜ ሰዎች ሁሉ ማወቅ ያለባቸውን በማሳወቅና መደረግ የሚገባውን በማድረግ ላይ ትኩት ሰጥቶ ነበረ፡፡

ሳምንትም እህታችን ሊሊ እንዳስተማረችን፣ ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ሆኖ እንደመጣ ደጋግሞ ሲናገር ነበር፡፡ በዛሬውም ክፍል ውስጥ ኢየሱስ ራሱን (ሥጋውንና ደሙን) የዘላለም ሕይወት እናገኝበት ዘንድ እንደሰጠ ይናገራል፡፡ ሰዎች ግን ይህንን ሕይወት የራሳችው ለማድረግ ሥጦታውን መቀበል አለባቸው፡፡

Jesus living bread . ECMYISኢየሱስ በቅፍርናሆም ሆኖ ይህንን ትምህርት ከማስተማሩ በፊት፣ ኢየሱስ የዚያን አከባቢ ሰዎች እንጄራ አብልቶአቸው ነበር፡፡ ስለዚህም በብዙ ሰዎች ውስጥ የነበረው ሓሳብ ‹ይህንን ምግብ የሚያበለውን ሰው ወይም አዲሱን አስተማሪ/ነቢይ ልንከተለው ይገባናል› የሚል ሳይሆን አልቀረም፡፡ እንዲያውም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከታዮቹ ብዛት ጨምሮአል፡፡ ይህ ሁኔታ እያለ ነው ኢየሱስ በሰሚዎች አገላለጥ ‹‹የማይቻል›› ወይም ‹‹ አስጨናቂ›› የተባለውን ትምህርቱን ያስተማረው (ቁ.52 እና ቁ.60 ተመልከቱ)፡፡ ለምን?

ጌታ ኢየሱስ ተንጋግተው በመከተል ቦታ የሚያጣብቡትን ሰዎች ሳይሆን ወደ የዘላለም ህይወት የሚሄዱትን ሰዎች ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ነው እያጉረመረሙበትም ቢሆን ጌታ ኢየሱስ ይህንን የዘላለም ሕይወት የሚኝበትን ትምርህት ያስተማረው፡፡ ሰዎች በስብከቱ ተደስተው ወይም ከስብከቱ ጋር ተስማምተው ግን ደግሞ የስኦል ልጆች ሆነው እንዲኖሩ አልፈለገም፡፡ የመከተል ዓላማቸውን ከጊዜያዊ እንጀራ ወደ የዘላለም ሕይወትን የሚያስገኝ እንጀራ መፈለግ መመለስ ነበረባቸው፡፡

ዛሬም ብዙ ሰዎች ክርስቲያን ናቸው፤ ጌታ ኢየሱስንም እንደሚከተሉት ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ክርስቲያን የሆኑት ጊዜአያዊ ጥቅም ለማግኘት ወይ ደግሞ ጥሩ ማህበራዊ ሕይወት እንዲኖራቸው ፈልገው ይመስላል፡፡ ክርስቲና ግን ሙሉ የሆነ ሕይወት አለበት፡፡ በዚህ ብቻ የተወሰነ ክርስቲና ለራሳቸውም ስለማይጠቅም፣ ‹‹ መንፈስና ሕይወት›› የሆነውን የኢየሱስን ቃል (ቁ.63) ዛሬ መስማ አለባቸው፡፡ ቤተክርስቲያን መናገር ያለባት ይህንን ነው፡፡ ሰዎች በስብሰባዋ ብቻ በዝተው ከህይወት ግን ጎድለው ከተገኙ ትልቅ ክሳራ ስለሚሆን እውነተኛውን የእግዚብሄርን ቃል ያለ ማመቻመችና ያለመሸቃቀጥ መናገር ይኖርባታል፡፡

ባለንበት ዘመን በብዛት የሚደመጡት ‹‹አብዛኞች ሰዎች እውነተኛው የእግዚአብሄር ቃል ከተነገረ ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው አይመጡም ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ግን መጽሓፍ ቅዱስ አስቀድሞውኑ መልስ ሰጥቶበታል፡፡ በቁ. 65-67 ተመልከከቱ፡፡ ተከታዮች ሁሉ ወደ ኋላቸው መመለስ ከፈለጉ የሚከለክል የለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት የፍቅር መንግስት ነው፡፡ የወደደው የጌታን ድምጽ ሰምቶ ይከተላል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ትምህርቱን ሰምተው ስላልወደዱት ብዙ ሰዎች ትተውት ስሄዱ፣ ‹ለምን ትሄዱብኛላቸሁ? ኑ ትምህርቴን አስተካክላለው› አላላቸውም፡፡ ይልቁንም ከእርሱ ጋር ቀርተው ለነበሩት ጥያቄ አቀረበላቸው ፤ ‹‹እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? ›› በማለት፡፡ ይህንን በማለቱ ኢየሱስ ሰዎቹ ወደ ፈለጉት የመሄድን አማራጭ ሰጣቸው፡፡ ይህንን ያደረገው ግን የሰዎችን ጥፋት (ከእግዚብሄር መንግሥት መኮብለል) ፈልጎ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሕይወትን ያልመረጡ ካሉ በአካል በዚያ ቢኖሩም አስቀድሞውኑ ከእርሱ ጋር ስለሌሉ ነው እንጂ፡፡ ደግሞም ‹‹ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም›› የሚለውን አስቡ፡፡ ፍላጎታችንን በእግዚአብሄር ቃል መመርመር እንጂ የጌታን ቃል በፍላጎታችን መመርመር ስህተት ነው፡፡ ስላልተመቸኝ የእግዚብሄር ቃል ስህተት ሊሆን አይችልም፡፡

እውነተኛው የእግዚአብሄር ቃል ሲነገረን ጆሮዎቻችንን የሚያሳክኩን ከሆነ፣ በሕይወታችን ላለመቀበልና ላለመለማመድ የምንወስን ከሆነ፣ ትንሽ ቆም ብለን ዓላማችንን መመርመር አለብን፡፡ ከእግዚአብሄር ቤትና መንግስት ምን እንፈልጋለን? ሕይወት ወይስ ፍላጎቶቻችንን ማርካት፡፡

ኢየሱስ ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እንደሆነ ለማረጋገጫነት የሰጣቸው ነገር ቢኖር የትንሳኤውንና የእርገቱን ምልክት ነው፡፡ ለሰሚዎቹም አሁን የሚነግራችሁን የሕየወት ቃል መቀበል ካቃታችሁ፣ ወደ አብ እንደሚሄድ ብነግራችሁ እንዴት ታምኑታላችሁ ? ይላቸዋል (ቁ፣62) ፡፡

ጴጥሮስና አብረውት የቀሩት ዴቀ መዛሙርት የውሳኔአቸውን መሠረት በሚፈልጉት የዘላለም ሕይወት ላይ አደረጉት፡፡ ማለትም ከጴጥርስ ንግግር እንደምናየው፣ ‹‹አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ›› ይህንን ደግሞ ከሌላ ሰው ወይም ቦታ ማግኘት አንችልምና ሌላ መሄጃ የለንም ማለቱ ነው፡፡

ውድ ወገኖቼ፣ ፍለጋችን የዘላለም ሕይወት ከሆነ፣ ወደ ኢየሱስ በመምጣታችን ትክክለኛ ውሳኔ አደረግን፡፡ ካልሆነ፣ ብዙም ሳንርቅና ሳንከስር ዓላማችንን እንመርምር፡፡ የዘላለም ሕይወትን ቅድሚያ በማድረጋችን ሌሎች ነገሮችም አይጎድሉብም፡፡ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።›› ተብሎ ተጽፎኣልና ፡፡

እግዚአብሄር በጸጋው ይርዳን፡፡

ጌታ ይባርካችሁ፡፡

19 August 2018 የዕለቱ ሰባኪ፡ ወንድም ተክሉ

[/read]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *