Sermons

ዓላማህን ተጠንቀቀው

ዓላማህን ተጠንቀቀው Evalgelical Church Mekane Yesus, Ethiopian Christian Church in Glasgow, Eritrean Christian Church in Scotland, Evangelical and Lutheran church,raodmap,road,karaa, menged,meged,ecis,

ዓላማህን ተጠንቀቀው ፡፡

ዛሬ በምናየው የኢየሱስ ትምህርት ውስጥ እንደ ክርስቲያን የምንኖርበትን ዓላማ ከተውንና ካልተጠነቀቅንለት ጠቃሚነታችንን እንደተውን እንረዳለን፡፡

ጠቃሚነቱን የተወ ነገር ደግሞ ክብር አይጠብቀውም፡፡

ካነበብነው ክፍል (ቁ 14) ከፍ ብሎ ባለው ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ጨው ጨውነቱን ከተወ ወጥቶ እንደሚጣል አስተማረ፡፡

በዚህ ክፍል ደግሞ መብራታችሁ በሰው ፊት እንዲበራ አድርጉ ካልሆነ እና ብርሃናችሁን ከደበቃችሁት ጠቃሚነታችሁ ይቀራል አለ፡፡

ማቴ 5፡14-16
14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
15 መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።

16 መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።

ይህን ንግግር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከት ላይ ለተከታዮቹ ከተናገራቸው ነገሮች መካከል ነው፡፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ የተጠቀማቸውን ቃላትና አገላለጾች በመፈተሽ ከእነርሱ ለመማር እንሞክራለን፡፡
– ክፍሉ ከማንነትን ጋር ተያያዥነት ያለውን ነገር በማምጣት ይጀምርል፡፡

‹‹እኔ ማን ነኝ?›› የሚለውን ጥያቄ ራሳችንን ብንጠይቅ የምናገኛቸው ትክክለኛ መልሶች ማንነታችን ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው፡፡

ያ ማለት ግን ሁሌ “እኔ እንዲህ ነኝ።” የምንለው ነገር ትክክለኛ ማንነታችንን ይገልጻል ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ብዙ ሰው በጥንትም ሆነ ባለንበት ዘመን በብዙ የማንንት ቀውስ ውስጥ (አይደንቲት ክራይስስ) ውስጥ ይኖራሉና፡፡ ስለዚህ ስለራሳቸውም ሆነ ስለ ሌላው ማንነት የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፡፡

ጌታ ግን ግልጽ አድርጎ በእርሱ ያገኘነውን ማንነት እንዲናውቅ ዛሬ ይፈልጋል፡፡ ከማንነትህ ጋር ግንኙነት አለውና ዓላማህን ተጠንቀቀው ፡፡

ጌታ ለተከተሉት ሰዎች እንዲህ ነበር ያላቸው “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡፡”

እናንተ
-እንዲህ እየተባሉ ያሉት ሰዎች ከማንኛችንም የሚለዩበት ሌላ ነገር የላቸውም፡፡ የተለያዬ አይነት ባህሪይ፣ አመለካከት፣ አደራረግ ነበራቸው፡፡ ነገር ግን በጋራ ያላቸው ኢየሱስን ለመከተል መወሰናቸው ነበር፡፡
ያንን ሲያደርጉ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ አድስ ማንነት በውስጣቸው እንደተከሰተና ይህ ማንነት ደግሞ በተቀረው ዘመናቸው መገለጥ እንዳለበት ያስተምራችው ጀመረ፡፡

“ብርሃን”
-“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡፡” ብርሃን የጨለማ ተቃራኒ ነው፡፡ ብርሃን ብወደድም ብጠላም ከወጣ ይታያል፣ ያሳያልም፡፡

ብርሃን ተጽኖ ከሚያመጣበት መንገድ አንዱ በፍጥነት በመሄድ ግልጽነትን/ አለመጨለምንና ሙቀትን በደረሰበት በማስገኘት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከጸሓይ ብርሃን የምናገኘው አገልግሎት ምስክር ነው።

“ብርሃን ናቸሁ”፡፡

እንዲታበራ ተጠርተሃልና ዓላማህን ተጠንቀቀው፡፡

– ያውም “የዓለም ብርሃን”–ለዓለም ሁሉ የሚሆን፣ ዓለም ሁሉ የሚጠብቃችሁ፣ ለዓለም ሁሉ የተሠጣችሁ ብርሃን ናችሁ፡፡ ያ ማለት የእናንተ አገልግሎት ተጽዕኖ ለዓለም ሁሉ የሚሆን ነው ማለቱ ነው፡፡

ይህ ኢየሱስ በተከታዮቹ ላይ የተናገረው የእውነትና የትምቢት ቃል እውነት እንደነበረና እንደሆነ ደግሞ እዚህ የተቀመጥን እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፡፡

ምክንያቱም ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት እነዚያ ሰዎች (ዴቀ መዛሙርቱ) ከኢየሱስ ሰምተው በመሰከሩት ምስክርነት ብዙ ትውልዶች ተደርሶል፣ እኛም ዛሬ እድሉ ደረሰን፡፡ እንዲሁ ደግሞ ዛሬ ቃሉን ሰምተን ለምናምን ሰዎች ይህ እውነተኛና ትንቢታዊ ቃል ይሰራል፡፡ የዓለም ብርሃን ናችሁ!

ብርሃን ስለሆናችሁ፣ በጨለማ (በኋጢአት) በተሞላች ዓለም ለማብራት (የጽድቅን ሥራ ለመግለጽ) ስለተጠራችሁ፣ መሰወር አይቻላችሁም፡፡

ይህ መሰወር ያለመቻል ምስጥር የመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ከሚገኘው አድስ ማንነት የተነሳ ነው፡፡
ያ ማለት ደግሞ ከእኛ ከእረሳችን የሚሆን ነገር ሳይሆን እርሱ በጸጋው በእኛ ላይ ካደረገውና ከተናገረው ነገር የተነሳ ነው፡፡ ልክ ሰማይና ምድርን በቃሉ እንደፈጠረ ሁሉ ማለት ነው፡፡ በተራራ ላይ ያለች ከተማ መሰወር እንደማይቻላት ሁሉ እናንተም እንዲሁ ትሆናላችሁ አለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ዓላማህን ተጠንቀቀው ፡፡

ለምን ብርሃን ተደረግን

-እንድናበራ፡፡ እግዚአብሄር ራሱ የብርሃን ማንነትን በሰዎች ውስጥ ሲያደርግ አለመሰወርን ደግሞ ጨምሮበት ነው፡፡ ብርሃኑ እንድታይ መብራቱ መታዬት ወደሚችልበት ከፍታ መውጣት አለበት፡፡

-እግዚአብሄር እንዲከብር፡፡ “መልካሙን ስራችሁን አይተው የሰማዩን አባታችሁን እንዲያከብሩ”፡፡

እኛ ራሳችንን እንድናሳይበትና የራሳችንን ክብር እንድንገነባበት አይደለም፡፡ ግን ለሌሎች መንገድ ለማሳየትና ድነው እግዚአብሄርን እንዲያከብሩት ነው፡፡ ይህ ፈጽሞ መሳት የማይገባን ዓላማችን ነው፡፡ ጌታ ይርዳን።

– የብርሃን ትልቁና ዋነኛው ሥራ ጨለማን መግፈፍ ነው፡፡ ጨለማ ሲገፈፍ መንገድ የሆውና ያልሆነው ይገለጣል፡፡ የሚጎዳውና የሚጠቅመው ይታያል፡፡

ይህ መልካሙ ሥራችሁ ነው፡፡ እናንተም እንዲሁ ለሌሎች መታዬት የሚችል፣ እነርሱም አይተው የሰማዩን አባታችሁን እንዲያከብሩ፣ “ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ”፡፡ መልካሙ ሥራችሁ ለሁሉም ይገለጥ።

– ተጨማሪ ማሳሰቢያ ደግሞ አለ፡፡
እግዚአብሄር አባቻችሁ ነው፡፡

ሰው ምን ሲያገኝ እግዚአብሄርን ያለማቀቋረጥ ሊያመሰግን ይችላል? ከስዖል ስድን።
ያ ደግሞ ሊሆን የሚችለው በተለያየ መንገድ የእውነት ቃል ይዘን ስንደርስለት ነው፡፡ ዓላማህን ተጠንቀቀው ፡፡

ጌታ ይርዳን።

በተክሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *