Teachings

እምነታችን

እንኳን ወደ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ በስኮትላንድ ድረ-ገጽ በደህና መጡ፡፡

የቤተክርስቲያናችን ስም ምንጫችን ከሆነችው እናት ቤተክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ በቀጥታ የመጣ ሆኖ በስኮትላንድ አውድና ኗሪዎችን ማዕከል ባደረገ መልኩ የተመሠረተች ቤተክርስቲያን ናት፡፡
የቤተክርስቲያንቱ ልዩ መታወቂያ የሆነው መካነ የሱስ ትርጉሙ የኢየሱስ መኖሪያ ሥፍራ ማለት ነው፡፡ በአጭሩ ለመጥራት እንዲመች “ መካነ የሱስ በስኮትላነድ ” የምለውን ስም በተለዋዋጭነት በዚህ ድረ-ገጽ ላይ እንጠቀማለን፡፡

መካነ የሱስ በስኮትላነድ ወንጌላዊት የቤተክርስቲያን ናት ስንል ንጹሕ የሆነውን የወንጌል ትምህርት ለማስተማሪና ለመጠበቅ፣ በእግዚአብሄርም ቃል መሠረት የቅዱሳት ምስጥራትን ለመፈጸም የተቋቋመች መሆኑዋን ለመግለጽ ነው፡፡

መካነ የሱስ በስኮትላነድ የብሉይና የአድስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሄር ቅዱስ ቃል መሆናቸውን ታምናለች::

መካነ የሱስ በስኮትላንድ ECMYIS

ቤተክርስቲያንቱ በቀደሙት አባቶችና የጥንቷ ቤተክርስቲያን የተቀበላቻቸውን የሃዋሪያትን፣ የኒቅያን እና የአተናቶስን የሃይማኖት መግለጫዎች እንዲሁም ያልተለወጠውን የአውግስበርግ የሃይማኖት መግለጫና የሉተር ካተኪዝም የእግዚአብሄር ቃል በአግባቡ የተብራራባቸው መሆናቸውን ትቀበላለች፡፡

የወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ በስኮትላንድ በስኮትላንድ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ በምድርቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ለመድረስ፣ ለማስተማርና ለማገልገል የተቋቋመች ሲሆን የእናት ቤተክርስቲያን ከሆነችው የኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ ጋር የጸና አንድነትና ሕብረት ይኖረናል፡፡

ስለዚህም የኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስን እምነትና አስተምሮት ሙሉ በሙሉ እንቀበላለን፡፡ ሆኖም ግን የእለት ተዕለት ተግባራዊ እና አስተዳዳራዊ ሥራዎችንና ላይ ያለንበት ሀገርና ነበራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ እና ብሉይና አድስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ጋር በማይጻረር መልኩ ይሆናል፡፡

ቤተክርስቲያን ተልዕኮዋ የጌታ ኢየሱስ እንደራሴ ሆና ሰዎችን ወደ እግዚብሄርና ወደ መንግስቱ መምራት ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን መልዕክቷ የሰዉን ሁለንተና ማዳን የሚችል ወንጌል ነው፡፡

2 thoughts on “እምነታችን

  1. እግዚአብሔር: አብዝቶ: ይባርካችሁ። እኔም: በጌታ: ያደኩበት: ቤተክርስትያን: እንጦጦ: መካነ~እየሱስ: ነው። ስድስት: ኩሎ: አ.አ.ዮ.. ተማሪ: እያለሁ: የቄስ: በሊና: ትምህርት: አያመልጠኝም: ነበር። የጌታ: ያውቃልና: የብሩክታዊት: ዝማሬ: ስለሚባርከኝ: እሁድ: አልቀርም: ነበር። በቃል: እየመከሩ: ያሳደጉኝ: ቄስ: በሊና: ናቸው። ዩንቨርስቲ: ተማሪ: እያለሁ: እንጦጦ: መካነ~እየሱስ: ያሳዩኝ: ፍቅር: ትዝ: ይለኛል። ጄምስ: ሲቀበለን: እያንዳችንን: ትንፋሽ: እስከሚያጥረን: እቅፍ: አድርጎ: የጌታን: ፍቅር: ያሳየናል። ከአራት: ኪሎ: ስላሴ: ታሀድሶ: ተብለው: ከተባረሩት: ውስጥ: እኔ: ነበርኩ። ቄስ: በሊናና: በፍቅር: ሰበሰቡን። ስለዚህ: እግዚአብሔር: እናንተንም: እንደሚረዳችሁ: አምናለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *