Sermons

ምሕረትን አግኝታችኋል

አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋልGod has the power to heal and save a person! By preaching the true word of God and trusting God for the fulfilment of his word, Mekane Yesus in Scotland, Glasgow city, United Kingdom, points out to Him who is the saviour, the creator and sustainer of the whole Universe, God and His Son Jesus Christ. ECMYIS is a church with Lutheran background. ECMYI church is set up by mainly members of the Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus,EECMY and Eritrean Lutheran church to reach humanity in Scotland. God saves! EECMY, ECMYIS, Mekane Yesus in Scotland, Mekane Yasus, Ethiopian Church in Glasgow, Scotland, Ethiopian Christina Community, Evangelical Church, Lutheran chuch in Glasgow, Scotland. we meet in St George's Tron Church, Church of Scotland, city center. Christian family, infant baptism is also practiced here. Eritrean Christian church from Lutheran chuch of Eritrea. Mark 10:23-31, Glasgow Mekane Yesus, Glasgow Ethiopian Christians, Glasgow Evangelical church, Mekane Yesus,

ምሕረትን አግኝታችኋል

“እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።” (1 ጴጥ. 2:10)

የመልእክቱ ተቀባዮች
ሓዋሪያው ጴጥሮስ ይህንን የሚጽፈው በተለያዩ ሃገራት ተበታትነው መጻተኞች ሆነው ይኖሩ ለነበሩ የክርስቶስ ተከታዮች ነበር (1 ጴጥ 1፡1-2)፡፡ ከመልእክቱ እንደምንረዳው፣ ሰዎቹ ዛሬ ላይ ሳይሆን ዛሬን በትናንትናው ማንነትና ሕይወት እየኖሩ ያሉ ይመስላሉ፡፡ ያም ማሌት አድስ ሆነው በተለወለዱበት ማንነት ሳይሆን፣ ቀድሞ ይኖሩ በነበሩት አሮገው ማንነት እጅጉን ይፈታተኑ እንደነበር እንገነዘባለን፡፡
ለምሳሌ፣ ርኩሰት (ቅድስና ማጣት)፣ ኃጢአት፣ ከንቱ ኑሮ፣ ግብዝነት፣ ጥላቻ ፣ ክፋት ፣ ተንኰል፣ እንዲሁም በቅንዓትና በሐሜት መመላለስ በመልእክቱ ውስጥ ከተጠቀሱት የአሮገው ማንነት ባሕሪያት ናቸው፡፡
እስቲ ሕይወታቻው ምን እንደነበረ እንቃኝ፡፡

መልእክቱን ስናጠና የምንረዳው አንድ በተደጋጋሚ የገለጸው ነገር፣ ሰዎቹ አማኞች መሆናቸው ነው( ቁ7)፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንገል ያምናሉ፡፡ ይህ እምነት በብዙዎች ዘንድ እንደሞኝነት የሚቆጠር ነበር፡፡  ቢሆንም ግን ከዚህ ሞኝነት ከሚመስል እምነት የተነሣ በሕይወታቸው ላይ የተከሰተ  ትልቅ ነገር እንዳለ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ይናገራል፡፡ ፈጽሞ ማንነታቸውን የሚለውጥ ቅዱስ ስራ ተሠርቶባቸዋል፡፡ ሊጠፋ ከማይችለው የእግዚአብሄር ቃል ዳግሞ ልዴት አግኝተዋል (1፡23)፡፡

ዳግም ውልዴት በሕይወታቸው ያመጣው ለውጥ

-እነርሱ ለመዳንና ሰማያዊ ርስት ለውረስ  የተጠበቁ ናቸው፡፡ በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል እየተጠበቁ አንደሆነ ሐዋሪያው ያስረዳቸዋል (1 ጴጥ 1፡3-5)፡፡
እምነታቸውን ግን ጊዜያዊ ፈታና እያጋጠው ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡(1 ጴጥ 1፡6-7) ይህ ፈታና ምንም ያህል ጊዜያዊ ቢሆንም ልባቸውን ግን ያሳዘናቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህ ጊዜያዊ ሀዘን፣ ከእምነታቸውን ፍጻሜ ስመለከቱ የሚኖራቸውን ስሜት ፈጽሞ ሊለውጠው አልቻለም፡፡ “የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።” (1 ጴጥ 1፡ 9)

ከዚህ እንደምንረዳው፣ ለጊዜው የሚታዩ ጊዜያዊ ሁኔታዎች ልብ ሰባሪና አሳዛኝ  ነው፡፡ የስደታቸውና ስለ እምነታቸው እየደረሰባቸው ያለው ነገር ፈታኝ ነበረ፡፡ ቢሆንም ግን በእምነታቸው እያገኙ ያሉትን ውስጣዊና ዘላለማዊ በረከት ሲያስቡ ደስታቸው በቃል ሊነገር የማይችል እና እጅግም ክብር የሞላበት ደስታ ነው፡፡

ሰዎቹ ጸጋ የተሠጣቸው ናቸው፡፡

ጸጋ ማለት በሥራ ያልተገኘ ግን ከሠጪው ከእግዚአብሄር በጎነትና መልካም ፈቃድ የሚገኝ ሥጦታ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጴጥሮስ  እየፃፈላቸው ያሉ ሰዎች (ይህ እኛንም ይመለተከናል)፣ የቀደሙት ታላላቅ ነቢያት ስለእርሱ ትንቢት እየተናገሩ ሊያገኙትም እየተመኙ ያላገኙትን መዳን ነው (1 ጴጥ 1፡ 10-12)፡፡ በአጠቃላይ የታደሉና የተባረኩ ሰዎች ናቸው፡፡ (ምንም እንኳ ለጊዜው በሚያሳዝን ስደት ውስጥ ቢያልፉም፡፡)

ከመልእክቱ እንደምንረዳው ጸጋው አንድ ጊዜ ብቻ ተሰጥቶ የሚነጥፍ ሳይሆን በዚህ ምድር ላይ እያለን ወደ እምነት የሚያመጣና ወደ ፊት የሚያስከድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ደግሞ በሙላት በፊቱ መቆም እንድንችል የሚረዳ ጸጋ አለላቸው፡፡ ይህንን የኢየሱስ ስገለጥ የሚያገኙትን ነጻ ስጦታ (ፀጋ) ደግሞ በተስፋ መጠባበቅ እንዳለባቸውም ይመክራቸዋል፡፡ “በኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ” እያለ፡፡ (1 ጴጥ 1፡13)
በ2፡ 9 ላይም “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤” ይላቸዋል፡፡ ይህም ማለት ልዩና የከበረ ተልዕኮ የተሰጥቶአችሁ ያንን መለማመድ የሚገባችሁ ሰዎች ናችሁ ይላቸዋል፡፡

ስለዚህ እናንተ እንዲህ የታደላችሁ ሰዎች ድሮ ትኖሩበት የነበረውን ርኩሰት፣ ኃጢአት፣ ከአባቶቻችሁ የወረሳችሁትን ከንቱ ኑሮ፣ ግብዝነት፣ ጥላቻ ፣ ክፋት ፣ ተንኰል፣ ቅንዓትና ሐሜት  ከሕይወታችሁ አስወግዱ ይላቸዋል፡፡
እናንተ የእግዚብሄር ምህረት የተንፀባረቀበትን ደግም ልዴት አግኝታችሁሃል፡፡ “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ” (1፡23)።

ስለዚህ አሮገው ልምምዳችሁ ከአድሱ ማንነታችሁ ጋር ስለማይሄድ ከእነርሱ ተለዩ ብሎ ሐዋሪያው ይመክራቸዋል፡፡  እንደ መልእክቱ ሀሳብ፣ እግዚአብሄር ከዚህን በፊት ለተመላለሳችሁባቸው የአመጽና የኃጢአት ሕይወት ምህረት ሰጥቶአችሁኃል፡፡ ስለዚህ ድሮ የቁጣ ልጆች በነበራችሁ ጊዜ የኖራችሁትን ኑሮ ሳይሆን ምህረት አግኝታችሁኃልና ምህረት እንደተደረገላቸው ሰዎች ተመላለሱ ይላቸዋል፡፡ ለእኛም ይህንን ነገር መገንዘብ ዛሬ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ከትናንትናው የቀጠለና በእርሱም ላይ የተገነባ ልምምድ ሳይሆን ከአድሱ ማንነት የሚመነጭ አድስ ልምምድ ልኖረን ያስፈልጋል፡፡ አሁን ምሕረትን አግኝታችኋል የምለውን ቁልፍ ቃል ማስታወስ ጠቃሚ ነው።

ስለዚአህ ጌታን ውደዱት፡፡ የእምነታችሁን እርሱም የነፍሳችሁን መዳን አስቡ፡፡ በጊዜያዊ ሃዘናችሁ ውስጥ ዘላለማዊ ደስታችሁን እያሰባችሁ ተጽናኑ ፡፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።”
የሚታዘዙ ልጆች ሁኑ እንጂ “ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ” (ቁ14)፡፡ ቅዱስ የሆነውን ሰማያዊ አባታችሁን ምሰሉ፤ “በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።” አሁን የምትኖሩት ሕይወት የእንግድነት ኑሮ መሆኑን አውቃችሁ፣ ዘወትር እግዚብሄርን በመፍራትና በጥንቃቄ ኑሩ (ቁ17)፡፡

የተዋጃችሁበትንና ክቡር የሆነውን “የክርስቶስ ደም” ሁልጊዜ አትርሱ። እናንተን የሚጠብቃችሁ ለጊዜው ብቻ ታይቶ የሚጠፋ ጊዜያዊ ሀብት (ብርና ወርቅ) ሳይሆን፣ ከክርስቶስ ደም የተነሳ ባገኛችሁት ምህረት አማካይነት የምትቀበሉት ዘላለማዊ ሪስት ነው፡፡ አሁን ምሕረትን አግኝታችኋልና።

ስለዚህ ለእውነት ታዘዙ፡፡ ያለ ምንም ግብዝነት እርስ በርሳችሁን ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፡፡ በወንጌል የተሰበከላችሁን ቃል ተለማመዱት፡፡ አሁን ምሕረትን አግኝታችኋልና።

ይህ ክፍል ለእኛም ዛሬ ይሠራል፡፡ ምክሩም ማስጠንቀቅያውም ለእኛም ጭምር ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምናገኘውን ጸጋ በተስፋ መጠባበቅ ይኖርብናል፡፡ ከእርሱ የሚሻል ምንም ነገር ለእኛ ልናገኝ አንችልምና፡፡ ያለጌታ በነበርንበት ጊዜ የኖርነውን ኑሮ ሕያው እንድሆን ማድረግ የለብንም፡፡ ይልቁንም በገኘነው ምህረት ልክ፣ በአድስ ህይወትና ማንነት መመላለስ ይኖርብናል፡፡

ጌታ ይባርካችሁ፡፡

 

 

በተክሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *