Sermons

ጎዳናህን ያቀናልሃል

ወደ እግዚብሄርና ወደ ቃሉ ስንመለስ፣ ስንጠጋና በእርሱ መስተዋት ውስጥ ራሳችንን ስንመለከት ግን በትክክል የሆነውንና ምን እንደምንመስል፤ ነገሮችን ለምንና እንዴት እንደምናደርግም ጭምር በግልጥ እናየዋለን፡፡ ጎዳናህን ያቀናልሃል It doesn't matter if we are from Orthodox, catholic, protestant or Lutheran, Muslim or other religions background. What matters is we are all human beings. We are not perfect. All we need is God's forgiveness and mercy to be saved. Jesus Christ died for our sins. If we believe and accept what God has done for us, we will have eternal security የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ የሱስ በስኮትላንድ

ምሳ 3፡5-6 (እግዚአብሔር ጎዳናህን ያቀናልሃል)

“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”

ይህን ክፍል ስናነብ ግልጽ መገንዘብ የምንችላቸው ነገሮች ፡-

  • አሁን ጎዳናህ የቀና አይደለም የሚል ሃሳብ በውስጡ አዝሎአል፡፡ ያልቀና ጎዳና በሌላም አገላለጽ የጠመመ መንገድ በባህሪው ብዙ አዙሪቶች ሊኖሩበት ይችላሉ፤ አድካሚ መንገድ ነው፤ ለተለያዩ አደጋዎች የማጋለጥ ባህሪይ አለው፡፡ ምክንያቱም አርቆ ለማየትና ሊመጣ ያለውን ነገር በቀላሉ ለማወቅም ሆነ ለመዘጋጀት ያስቸግራልና፡፡ ስለዚህ በጠመመ ጎዳና ላይ ብዙ ችግሮች በድንገት ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ በጣም በስጋት የሚሄዱበት መንገድ ነው፡፡ በዚያም ላይ ያ የጠመመ መንገድ የሰውን ጊዜና ጉልበት የሚጨርስ ሊሆን ይችላል፡፡
  • ይህ አይነቱ የጠመመ መንገድ የኃጢአት ሕይወት ምሳሌ ነው፡፡ ቅንነት፣ እግዚአብሄርን መፍራር፣ ታማኝነት፣ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ ጽድቅ የሌለበት ሕይወት ነው፡፡ የሓጢአት ሕይወት የሰውን ሁለንተናዊ ማንነት ተጋላጭ የሚያደርግና ደስታ፣ ሠላም፣ እረፍት፣ ተስፋ የማይታይበት ሕይወት ነው፡፡ በኃጢአት ሕይወት ውስጥ ብዙ የሚያስፈሩ፣ የሚያስደነግጡ፣ የሚያስጨንቁ ና ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች በሰው ሕይወት ይፈራረቃሉ፡፡
  • በዚህ በአነበብነው ክፍል ግን “እግዚአብሄር መንገድህን ያቀናልሃል” ይላል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እግዚአብሄር ራሱ በጽድቅ፣ በቅንነት፣ እርሱን በመፍራት፣ ተስፋና ሠላም በሞላበት ሕይወት እንድትኖር ሊያድርግህ ይችላል ማለት ነው፡፡ ይህ የተስፋ ቃልህ ነው፡፡
  • እግዚአብሄር መንገድህን እንዲያቀናል ከፈለግህ ለእርሱ መፍቀድ አስፈላጊ እንደሆነ ያሳየናል፡፡

እንዴት አድርገን እግዚአብሄር ጎዳናችንን እንዲያቀናልን እንፍቀድለት?

“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን”  ጎዳናህን ያቀናልሃል

በእግዚአብሄር “መታመን” – እርሱ ያለውን እንደሚያደርግ፣ እርሱንና መንገዱን ተከትለን እንደማያሳፍረንና እንደማይጥለን ማወቅ፡፡

ነገሮች እኛ እንደፈለግነው ባይሆኑልንም እንኳ፣ እርሱ ብቻ መሰማት፣ መታመን እና እውነተኛ ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት ማወቅ ነው፡፡ ምክንያቱም እርሱ ለመድረስ ወደምናስበበት ቦታ የሚያደርሰንን ትክክለኛ መንገድ ያውቃል፡፡

ይህ ማለት ደግሞ ሁልጊዜ በሐሳብ ደረጃ ብቻ ከእርሱ ጋር መስማማት ሳይሆን በሕይወትና በሞትም በእርሱ ላይ ማረፍን ይጠይቃል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል ውስጥ የሚናነበው የ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታርክ መታመን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ ያስረዳናል፡፡

“ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡንም፦ ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም። የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።” (ዳን.3፡16-18)ስለዚህ በፍጹም ልብ በእግዚአብሄር የሚታመን ሰው እግዚብሄር እንደተናገረው እንደሚያደርግ ያምናል፣ እግዚአብሄርን በመከተሉ እከስራለሁ ብሎ አያስብም፡፡ የእነሲድራቅን ፍርሃትና ስጋት ያስወገደላቸውና እስከ መጨረሻ እንዲጸኑ ያደረጋቸው፣ የቅጣቱ ቅለት ወይም ከሌሎች ሰዎች የተለየ እሳት የማያቃጥለው ሰውነት ስላላቸው ሳይሆን እግዚአብሄርን በፍጹም ልባቸው መታመናቸው ብቻ ነው፡፡

ይህ ማለት ደግሞ ሁልጊዜ በሐሳብ ደረጃ ብቻ ከእርሱ ጋር መስማማት ሳይሆን በሕይወትና በሞትም በእርሱ ላይ ማረፍን ይጠይቃል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል ውስጥ የሚናነበው የ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታርክ መታመን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ ያስረዳናል፡፡

ነገሮች እኛ እንደፈለግነው ባይሆኑልንም እንኳ፣ እርሱ ብቻ መሰማት፣ መታመን እና እውነተኛ ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት ማወቅ ነው፡፡ ምክንያቱም እርሱ ለመድረስ ወደምናስበበት ቦታ የሚያደርሰንን ትክክለኛ መንገድ ያውቃል፡፡

በእግዚአብሄር “መታመን” – እርሱ ያለውን እንደሚያደርግ፣ እርሱንና መንገዱን ተከትለን እንደማያሳፍረንና እንደማይጥለን ማወቅ፡፡

“በራስህም ማስተዋል አትደገፍ” ጎዳናህን ያቀናልሃል

  • በራስ ማስተዋል መደገፍ ማለት ከእግዚአብሄር ቃልና ስርዓት የተሻሌ የሚመስል ሃሳብ ቢኖርህም እንኳ በእግዚአብሄር ሃሳብ ተቃራኒ አትህድ ማለት ነው፡፡ በሰው ህሳቤ የማይመስል የሚመስል ነገር ሲፈጠር ጨከን አድርጎ እግዚአብሄር በተናገረው ነገር ላይ እምነትን በመጣል መራመድ ነው፡፡ በራሱ ማስተዋል የሚታመን ሰው ቀይ ባህርን በእግሩ ለመሻገር አይራመድበትም፣ ከዓለትም ውሃ ይፈልቅልኛል ብሎ አይጠብቅም፣ ወይም ደግሞ ውሃ ብቻ በጋን ተሞልቶ መልክና ጣዕም ያለው የወይን ጠጅ ይሆናል ብሎ አይጠብቅም፡፡ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፡፡

“በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ” ጎዳናህን ያቀናልሃል

እግዚአብሄር በሕይወታችንና በምናደርጋቸው ውሳነዎች ሁሉ ለእርሱ እውቅና እንድንሰጥ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በዚህ ቦታ አይፈለግምና ይህንን እኔው ብቻ ላድርግ አትበል፡፡ እግዚአብሄር አያየኝም፣ አይሰማኝም፣ አያውቀኝም ወይም ደግሞ እግዚአብሄር የለም ብለህ ምንም ነገር አታድርግ፡፡ ይልቁንስ በሁሉም ቦታና እና ጊዜ ውስጥ እግዚአብሄር እንዳለ፣ እንደሚኖር፣ እንሚያይ፣ እንደሚሰማ፣ እንደሚፈርድም አትርሳ፡፡

እንግድህ አንተ (አንቺም እንድህው) በእግዚአብሄር ስትታመን፣ በራስህ ማስተዋል መደገፍ ስታቆሞና በደረስክበት ሁሉ እግዚብሄርን ስታውቅ፣ እርሱ ራሱ ደግሞ መንገድህን ያቀናልሃል፡፡ እንቅፋትንም ሁሉ ከመንገድህ ላይ ያነሳልሃል፡፡

በእግዚብሄር መንገድና እርሱ ባወጣልህ ጎዳና ስትሄድ በመንገድህ መደናቀፊያ ነገር አይኖርበትም፡፡ የጠመመ ነገር ሁሉ ይቀናል፣ የጎበጠ ይስተካከላል፡፡ እርሱ ያልተስተካለውን ነገርህን በራሱ ቸርነትና በጎነት ያስተካክልልሃል፡፡ “ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም ጠገን” (ምሳ 3፡8)፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *