Sermons

ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው

ecmyis sunday service, Mekane Yesus in Scotland, Christianity, Glasgow church,

የማቴዎስ ወንጌል 10:34-42 ( ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው ፡፡)

34 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።

35 ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤

36 ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።

37 ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤

38 መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።

39 ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል።

40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።

 

በዚህ የወንጌል ክፍል ውስጥ የተናገረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

 

ለምን ይህንን ተናገረ?

ጌታችን ኢየሱስ ደቄ መዛርቱን ለወንጌል አገልግሎት ሲልካቸው ከተናገራቸው ብዙ ነገሮች መካከል ይህም ክፍል ይገኝበታል፡፡

ወንጌልን ለጠፉት ለእስራኤል ቤት ለማድረስ ሲሄዱ አንዳንድ ማወቅና መጠንቀቅ ያለባቸው ነገሮች (አለመስማማቶች፣ መገዳደሎች፣ መለያየቶች…) እንዳሉ ለማስገንዘብ ኢየሱስ ይህንን ተናገረ፡፡ ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው ፡፡

ይህ ደግሞ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአህዛብ አገልግሎት ውስጥም ጠቃሚ ማስጠንቀቂያና መመሪያ ነበር አሁንም ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው ፡፡

የማስጠንቀቅያው ዓላማ፡

  1. ችግሮቹ በሌሎች ላይ ሲከሰቱ ሲያዩ ግራ እንዳይገባቸውና ጥያቄ/ጥርጣሬ እንዳይፈጠረርባቸው ነው፡፡
  2. ችግሩቹ በእነርሱ ራሳቸውም ላይ ሲደርስባቸው እንዳይበረግጉና ወደ ሃላቸው እንዳይመለሱ ለማበረታታት፡፡
  3. በፊታቸው ላለው አገልግሎት/ተልዕኮ ሁለንተናዊ ዝግጅት (ማለትም የአእምሮና ስነልቦናዊ ዝግጅት፣ የመንፈስ ዝግጅት፣ በማህበረሰባዊ ግንኙነታቸው ላይ፣ በኢኮኖሚያቸው ላይ ሊመጣ ለሚችለውን ቀውስ ሁሉ ዝግጅት) አድርገው እንዲወጡ ለመርዳት ነው፡፡

ይህ ደግሞ በሌላ አገላለጽ፣ የተላኩበት ተልእኮ እነርሱንም ሆነ እነርሱን በሚቀበሉአቸው ወይም በማይቀበሉአቸው ዘንድ የሚያስከፍለውን ዋጋ አስቀድሞ አይተውና ዋጋቸውን ተምነው እንዲወጡ ለመርዳት ኢየሱስ ይህንን ተናገረ፡፡ ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው ፡፡

  1. የአገልግሎታቸው ውጤታማነት መለኪያ የሰዎች እነርሱን መቀበልና ማክበር ሳይሆን የወንጌል ተልእኮ ተጽዕኖ በምድር ላይ መገለጡና ሰዎች ላመኑበት እውነት ፈጽመው ራሳቸውን እስኪሰጡ ድረስ ዋጋ መክፈላቸው ነው፡፡

ይህም ወንጌሉን ከመቀበላቸውና ከማስተናገዳቸው የተነሳ፣ አማኞች ስለሆኑ ብቻ፣ ሰዎች፣ በተለይ ደግሞ ቤተሰዎቻቸው በእነርሱ ላይ በተቃውሞ ሊነሱ፣ ሊጠሉአቸው፣ ሊለዩአቸው፣ ሊጎዱአውና ሊገልድሉአቸው እንደሚችሉ ነው፡፡ ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው ፡፡

ለአገልግሎቱ ተሰጥቶአቸው ስለነበሩ ነገሮች

ከላይ ካነበብነው ክፍል ከፍ ብለን ስንመለከት፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሠጣቸው ነገሮች ነበሩ፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-

  1. መለኮታዊ ሥልጣን ና ሓይል (በመለኮት የሚሠጥ ስልጣን ማለቴ ነው)— በአጋንንትና በደዌ ሁሉ ላይ ስልጣን ተሰጣቸው፡፡
  2. የወንጌል መልእት–“ንስሓ ግቡ የእግዚአብሄር መንግስት ቀርባለችና” የሚል ሰማያዊ ጥሪ
  3. የአገልሎቱ አፈጻጸም መመሪያ–

– የጊዜያዊና የወደፊቱ የወንጌል አገልግሎት አከባቢ፣

– ስለ የወንጌል አገልግሎት የጉዞ አደራረግ፣ – የስብከት ሪዕስ፣ ሥልጣን፣ አገልግሎቻቸውን የሚሠጡበት ሁኔታ (“በነጻ ተቀበላችሁ በነጻ ሥጡ”)

– ገንዘብና ስንቅ ስለመያዝ፣ አገልያሎታቸው በገንዘብና በልብስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በእግዚአብሄር አቅርቦት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት፡፡ ያ ማለት ደግሞ እለት እለት በእግዚብሄር አቅርቦት በመታመን የሚኖር ኑሮና አገልግሎት መሆኑን

– ወደ ሰዎች ቤት ሲገቡ ማሳዬት ስላለባቸው ባህሪይ… የራሳቸውን ምቾት ለመጠበቅ ከአንድ ቤት ወደ ሌላ ቤት መዞር ሳይሆን በገቡበት ቤት ሆነው በወንጌል አገልግሎቱ/ተልዕኮው ላይ ትኩረት መሥጠት እንዳለባቸው፤

  1. ተስፋ ሰጣቸው–

– ያለ እግዚአብሄር ፈቃድ አንዳች ነገር እንደማይደርስባቸው፣ ፀጉራቸው እንኳ የተቆጠረ እንደሆነ፣

– የመንፈስ ቅዱስ እገዛ እንዳላቸውና ለሚጠየቁት ነገር ምን መመለስ እንዳለባቸው እንዳይጨነቁ ነገራቸው፡፡

– የእርሱንም የሁልጊዜ አብሮነት በማቴዎስ ወንጌል 28 ላይ ሠጥቶአቸዋል፡፡

እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያለው ሰው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነትና አክብሮት የሚያገኝ ደግሞም በሁሉም የሚወደድ ይመስለናል፡፡

 

የደቄ መዛሙርነት/ክርስቲና ተግዳሮቶች

ጌታ ኢየሱስ ግን ደቄ መዛሙርነት/ክርስቲና መልካም ነገር ያለበት መሆኑን ካሳዬ በኃላ ተግዳሮቶችም ያሉበት መሆኑን ግልጽ አድርጎ ተናገረ፡፡

ክርስቲና ለሕወትና ለጥሪ የሚንኖርበት ሕይወት እንጂ የምቾት ሕይወት ብቻ አይደለም፡፡ ያ ማለት ደግሞ ክርስቲያኖች ፈጽሞ የምቾት ሕይወት አያስፈልጋቸውም፣ ወይም በምቾት መኖር አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ደስታ፣ ሠላም፣ በረከት፣ አብሮነትና መንፈስ የደስታቸውና የምቾታቸው መሠረት ነውና፡፡

–ጌታ ኢየሱስ “በምድር ላይ…ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም” ብሎ ሲናገር፣ እናንቴ ሰይፍ ይዛችሁ ውጡ ወይም ሰዎችን ግደሉ ማለቱ ሳይሆን፣

  1. ስለተቀበላችሁት እውነትና ሕይወት ስዴት ሊመጣባቸው እንዳለ፡፡
  2. እናንቴ ስለሚትሰብኩት ወንጌል ደግሞ በምድር ላይ የሚከሰት ቀውስ አለ ማለቱም ነው፡፡

ዓለማዊ ዜጎችን በወንጌሉ ቃል የሰማያዊ ዜጎች የማድረግ ሥራ ውስጥ የመንፈሳዊው ድንበር ጥሰት መዘዞች አሉበት፡፡ ይህ ደግሞ መገለጫው በቤተሰዎች መካከል፣ በዘመዶች መካከል፣ በወዳጆች መካከል፣ በህብረተሰብ መካከል የሚመጡ አለመግባባቶች፣ አለመስማማቶችና በተለይም ስለቃሉ በሚነሱት ስዴቶች ናቸው፡፡

ታዲያ እንዴት መኖር ይገባናል?

በመጨረሻም በዚህ አይነቱ ቀውስና ተግዳሮቶች መካከል እንዴት መኖር ይገባናል ለሚለው መልስ ተሰጥቶአል፡፡

  1. ቁ. 37 እኔን ከሁሉም ማስበለጥ መቻላችሁን አረጋግጡ፡፡ “ከእኔ ይልቅ ‹ሌሎችን› …የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም”፡፡ “እግዚአብሄር አምላክህን በፊጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ … ውደደው ” የሚል ከመጀመሪያው ጀምሮ የመጽሓፍ ቅዱስ አስተምህሮት ነው፡፡

ገላ 5፡11 “ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እስከ አሁን መገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛል? እንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል።” ችግርን የሚያመጣው የስብከታችን ይዘትና የኑሮአችን ጣዕም ነው፡፡

  1. ቁ. 38 የገዛ መስቀላችሁን ይዛችሁ ተከተሉኝ፡፡ ስለወንጌል የሚመጣባችውን መከራ ሸሽታችሁ ወደ ኋላችሁ አትመለሱ፡፡ ይልቁንስ መስቀላችሁን እለት እለት ተሸከሙና እኔን የመከተል ተግባራችሁን ፈጽሙ
  2. ቁ39 የገዛ ነፍሳችን የማግኘት ዘዴው ስለእኔ ነፍሳችሁን መስጠት ነው፡፡ ራሳችሁን ያዳናችሁ መስሎአችሁ ከወንጌሉ ከሸሻችሁ በእውነት ነፍሳችን እያጠፋችሁ መሆኑን ተገንዘቡ፡፡ ክርስቲና ትልቁ ዓላማው የራስንና የሌሎችን ነፍስን ማዳን ነውና፡፡ ሕይወት የምንለው እርሱን ነው፡፡
  3. ቁ.40-42 የወንጌል ተልእኮ ፈጻሚዎች “ሰባኪዎቹ” ፣ “ነቢያቱ” ወይም አንድ የታወቀ የአገልግሎት ቢሮ ይዘው የሚቀወጡ ሰዎች ብቻ ሳይሆን እነርሱንም የሚቀበሉአቸው፣ የሚያግዙአቸው፣ አገልግሎታቸውንም የሚደግፉ ሰዎችም ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ በመለኮታዊውና የሰማይ አመዛዘን ሰባኪውና የስብከቱ ደጋፊዎች እኩል ዋጋ አላቸው፡፡ ሁለቱም ከእግዝአብሔር ጋር በመተባበር ነፍሳት ይድኑ ዘንድ በሰይጣንና በመንግስቱ ላይ ጦርነትን አውጀዋልና፡፡

ጌታ እንደ ፈቃዱ እንድንኖር በጸጋው ይርዳን፡፡

ስለዚህ እነዚህ የሚላኩ ሰዎች ወይም ደቀ መዛሙርት በተለያዬ መንገድ የሚደግፉአቸውን ከእነርሱ በታች አድርገው መቁጠር አይገባቸውም፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ሁለቱም እኩል ዋጋ አላቸውና፡፡

ከዚህ ክፍል ለራሳችን ምን እንማራለን?

– የጌታን ድምጽ መስማትና ጌታ እንድናደርግ የሚፈልገውን በግላችን ከእርሱ መቀበል ያስፈልገባል፡፡ ወንጌል ላልደረሳቸው ወይም ከወንጌል እምነት ለወደቁት “የመመለስ መልእክት ይዞ መሄድ” ጥሪያችን ነው፡፡

– እግዚአብሄርን ከሁሉም አብልጦ የመውደድ ነገር በውስጣችን እንዲያድግ መጣር አለብን፡፡ ምክንያቱም ሌሎች “ወዳጆቻችን” ከአግዚአብር ጋር በጠላትነት ሊያመላልሱን ይችላሉና፡፡ “ዓለምን የሚወድ የእግዚብሄር ጠላት ነው” የሚል ተጽፎ አለ፡፡

– መከራዎቻችና ችግሮቻችን ፈጽመው ከእግዚብሄርና ከተልኮዎቻችን ሊነጥሉን አይገባም፡፡ መስቀላችንን ተሸክመን ለመከተል ተመክረናልና፡፡

ክርስቲና ስለ ሕይወት ነው ፡፡

ጌታ በጸጋው ይርዳን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *